የእኖር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ጠቅላላ የወረዳው ካብኒ አመራር በተገኙበት የ1ኛ ሩብ አመት የመልካም አስተዳደር ተግባር አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ አመራሩ በየሴክተር መስሪያ ቤቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ሲያቅድ መጀመሪያ ከተቋሙ ውስጥ እና አጠገቡ ካለው አገልግሎት አሰጣጥ ችግር ከመፍታት መነሳት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪው አክለው የተቋም የመልካም አስተዳደር እቅድና ሪፖርት መረጃ በጥራትና በጊዜ ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብሏል፡፡
እንደዋና አስተዳዳሪው ገለጻ ተቋማት የመልካም አስተዳደር ችግሮች የውስጥና የውጭ የሆኑት ከተቋሙ ባህርይ አንፃር በተገቢው ለይቶ አቅዶ የማህበረሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለይቶ ለመፍታት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪው እንደወረዳ የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የተጠቃለለ ሪፖርት በአስተዳደር ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደርና አካባቢ ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ በአቶ ይምራን ዘኪ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመድረኩ የተገኙት አመራር አካላት በሰጡት አስተያየት መድረኩ የወረዳው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ችግሮች በደረጃ ለይቶ የጋራ በማድረግ በቅንጅት የሚፈቱ የመልካም አስዳደር ችግሮች መፍታት ያስፈልጋል ብሏል፡፡
ሌላው በመድረኩ የተነሳው በወረዳው የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተቋም ማኔጅመንት በመገምገም እና ያልተፈቱ ችግሮች በቀጣይ የእቅድ አካል አርጎ መስራት እንደሚገባ ተመላክተዋል

