የእ/ወ/ወ/ስ/ ጽ/ቤት ሀላፊ
አቶ ቸሩ ተካ
መግቢያ
ከሃገራችንም ሆነ ከክልላችን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ውስጥ ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከ15 እስከ 29 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች እንደሆኑ የተለያዩ መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆን ከ30 ዓመት በታች ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙት ቁጥራቸው ከ70 በመቶ በላይ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እነዚህ ከአጠቃላይ ክልላችን የህዝብ ብዛት ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት ታዳጊዎችና ወጣቶች እምቅ አቅም፣ ብሩህ አእምሮና የምርምርና ፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው አምራች ሃይል ናቸው፡፡ በመሆኑም ታዳጊዎችና ወጣቶች አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠርና የመመራመር ብቃታቸውን በመጠቀም ለሃገር እድገትና ብልፅግና የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ የላቀ ነው፡፡ ነገር ግን ለወጣቶች በቂ ትኩረት በመስጠትና ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ስብዕናቸውን በተገቢ ሁኔታ መቅረጽ ካልተቻለ በቀላሉ ለችግር በመጋላጥ፣ ወደ ጥፋትና አፍራሽ ነገሮች የመግባት እድላቸው የሰፋ ነው፡፡
ስለሆነም ወጣቶች አገር ተረካቢና የአገሪቱን መፃኢ እድል የሚወስኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውን በመገንዘብ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና እውቀታቸውን በመጠቀም በትምህርት ተቋማት እና በወጣት አደረጃጅቶች አማካኝነት በአሉታዊ መጤ ባህሎች የንቅናቄና ግንዛቤ ስራዎችን በባለቤትነት ማከናወን ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም መልካም ስብዕና ተላብሰው የአገራቸውንና የክልላቸውንና የዞናቸው ብሎም የወረዳቸወ ባህልና እሴት ጠንቅቀው ከማወቅና ከመጠበቅ አንፃር በሀገሪቱ ሰላም ልማትና ዲሞክራሲ ላይ የሚኖራቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ኃላፊነታቸውን በሚገባ አውቀው እንዲወጡ ለማስቻል የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ በባለፉት10 ዓመታት የትራንስፎርሜሽን እቅድ ወጣቱ በፖለቲካው በኢኮኖሚና በማህበራዊ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ፓኬጆች ተቀርጸው ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ ለአብነት የወጣቱ የስራ አጥንት ለመቀነስ ለወጣቱ ሪቮልቪንግ ፈንድ በመመደብ መስሪያና መሸጫ ቦታዎች በማመቻቸት የገበያ ትስስር በመፈጥር ወጣቱ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማና አምራች ዜጋን በመፍጠር በተሰማራበት የሙያ ዘርፍ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ ስፖርት በኢኮኖሚ ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚኖረውን ሚና እንዲወጣ ለማስቻል፣ እንዲሁም ከአጠቃላይ የህብረተሰብ ተሳትፎ በመነሳት ምርጥ ስፖርተኞችን በማፍራት በዓለም አቀፍ ውድድር መድረክ ተፎካካሪና ተወዳዳሪ በመሆንና ውጤት በማስመዝገብ በሀገር ገጽታ ግንባታ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በመሳተፈ የማህበረሰቡን ችግር በመረዳት በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ዘርፎች ማህበረሰቡ በመደገፍና የበጎ አገልግሎት ባህልን ዕሴት በተገቢ እዲረዳ እና እንዲገነዘብ የተለያዩ ስራዎች ተሰርቷል፡፡
የጽ/ቤቱ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣እሴቶች፣
ራዕይ
“በ2022 የወረዳዉ ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና፣ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ጤናማ ህብረተሰብ፣ መልካም ስብዕና ያለው ወጣት፣ ተወዳዳሪና ውጤታማ የሆኑ ስፖርተኞች ተፈጥረው ማየት፡፡
ተልዕኮ
የወረዳችን ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና ህዝባዊ መሰረት ያለውን ስፖርት በማስፋፋት የዜጎችን አካላዊና አእምሮአዊ ብቃት በመገንባት የወረዳችን እና የዞናችንና እንዲሁም የሀገርን ብልፅግና ማረጋገጥ፣
እሴቶች
- አሳታፊነትና ፍትኃዊነት፣
- ግልጽነትና ተጠያቂነት፣
- ፈጠራን ማበረታታት፣
- ቅልጥፍናና ውጤታማነት፣
- የአገልግሎት ጥራት፣
- ለለውጥ ዝግጁነት፣
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834