የእኖር ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ጽ/ቤት ሀላፊ
አቶ ኤልያስ ሙራድ
መግቢያ
በሀገር አቀፍ ደረጃ መንግስት ለከተሞች ልዩ ትኩረት በመስጠት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ የልማት ስራዎች እንቅስቃሴ እንደሀገር በርካታ ስራዎች እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡ በተመሳሰዩ በወረዳችን ባሉ ከተሞች በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በጽዳትና በአረንጓዴ ልማት፣ በመሬት አቅርቦት፣ ከተሞች በፕላን እንዲመሩ በማድረግ እና በቤት አቅርቦት በባለፋት ሦስት የዕቅድ ዓመታት አቅም በፈቀደ ሲከናወኑ ቆይቷል፡፡ በተጨማሪም በ2016 በጀት ዓመት ሴክቶሪያል ዕቅድ በማቀድ በተዋረድ ለታችኛው መዋቅር በማውረድ በመተግባር ላይ ይገኛል፡፡
ከዚህ አንጻር ዘላቂነት ያለው የከተማ ፕላንና ልማት አዋጭነት፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው የመሬት አቅርቦትና ማኔጅመንት፤ ህብረተሰቡንና የግል ዘርፉን ያሳተፈ የቤት ልማትና አቅርቦት፤ በጥራት፣በተመጣጣኝ ወጪ፣ በወቅቱና የማስፈጸም አቅም በመገንባት የመልካም አስተዳደር መርሆዎችን ለማሳካት በአተገባበር ሂዳት ያገጠሙ ችግሮችን እልባት በመስጠት መስራትን ይጠይቃል፡፡
የልማት ሥራችን ከተሞች እንደ ማዕከላቱ ልዩ ሚናና የማደግ አቅም ተቃኝተው የኢንዱስትሪ፣ የገበያና የአገልግሎት ማዕከልነት ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በማስቻል፣ከአካባቢ ከተሞች እንዲሁም ከገጠሩ ጋር በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚዊና ከባቢያዊ ጉዳዮች መስተጋብር በመፍጠር ተመጋጋቢና የተቀናጁ ሆነው እንዲለሙ በሚያስችል ደረጃ ሲተገበር ቆይቷል፡፡
ይህንኑ ለማሳካት ቀደም ሲል ተግባራት በንቅናቄ እየተፈጸመ የቆየ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ የታየበት ነው፡፡ ይህንኑ ጅምር እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ ለመቀጠል ተግባራትን በንቅናቄ መምራት አስፈልጓል፡፡
- የእኖር ወረዳ በ 3 ማዘጋጃና በ21ጥንስ ከተሞች በስሩ የሚገኙ ሲሆን በዋነነት ማዘጋጃ ቤቶች.
ጉስባጃ ማዘጋጃ ፡-የተመሰረተዉ በ2011 ሲሆን የህዝብ ብዛቱ ወ1773 ሴ 1943 ድ,3716 የቆዳ ስፋቱ ደግሞ 501.9 ሔ/ር ላይ ነዉ የተመሰረተዉ፡፡
ጋንዛቸ ማዘጋጃ፡-የተመሰረተዉ በ2007 ሲሆን የህዝብ ብዛቱ ወ1200 ሴ 1261 ድ,1461 የቆዳ ስፋቱ ደግሞ 140.29 ሔ/ር ላይ ነዉ የተመሰረተዉ፡፡
እገዜ ማዘጋጃ፡-የተመሰረተዉ በ2006 ሲሆን የህዝብ ብዛቱ ወ1110 ሴ 1111 ድ,2220 የቆዳ ስፋቱ ደግሞ 198.76 ሔ/ር ላይ ነዉ የተመሰረተዉ፡፡
የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት
የመሬት ልማትና ማኔጅመንትን በከተሞች የመሬት ሊዝ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ የተለያዩ ለመሬት ልማትና አስተዳደር ሊያገለግሉ የሚችሉ የህግ ማዕቀፎችን ተግባራዊ በማድረግ ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ እንዲሁም መሬትን በቁጠባ እና ለላቀ ልማትና ፍትሀዊ የሀብት አጠቃቀም እንዲዉል የባለፉት ዓመታት ርብርብ ሲደረግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
በ ሶስቱም(3) ማዘጋጃ ቤት በአስሩ የመሬት አጠቃቀም መሰረት መሬቱ በካርታ ፕላን መሰረት እየተመራና በማዘጋጃ ቤቶች ያላቸዉ መሬት ሀብት ፤–
ጉስባጃ
1 ለመኖረያ 108.2ሄ/ር 2 ለንግድና ኢንቨሰትመት 17.32ሄ/ር 3.ለአገልግሎት ሰጪ 20.83ሄ/ር 4.ለአሰተደር 2.76ሄ/ር 5.ለጥቃቅንና ለአነስተኛ ኢንተር ፕራዝ 22.75ሄ/ር
6 .ለመንገድና ለመንገድ ግንባታ58.72 ሄ/ር 7 ለመዝናኛ ቦታዎች 12.72 ሄ/ር 8.የከተማ የግብር ቦታዎች 19ሄ/ር 9 ለጫካማ ቦታዎች 44ሄ/ር 10. መጠባበቂያ ቦታዎች 40.99ሄ/ር
እገዜ
1 ለመኖረያ 70.92ሄ/ር
2 ለንግድና ኢንቨሰትመት 11.49ሄ/ር
3.ለአገልግሎት ሰጪ 13.635ሄ/ር
4.ለአሰተደር 1.79ሄ/ር 5.ለጥቃቅንና ለአነስተኛ ኢንተር ፕራዝ 14.89ሄ/ር
6 .ለመንገድና ለመንገድ ግንባታ38.46 ሄ/ር
7ለመዝናኛ ቦታዎች 8.33 ሄ/ር
8.የከተማ የግብር ቦታዎች 12.44ሄ/ር 9ለጫካማ ቦታዎች 10. መጠባበቂያ ቦታዎች 26.85ሄ/ር፤–
ጋንዛቸ
1 ለመኖረያ 50.06ሄ/ር 2 ለንግድና ኢንቨሰትመት 8.11ሄ/ር 3.ለአገልግሎት ሰጪ 9.62ሄ/ር 4.ለአሰተደር 1.26ሄ/ር 5.ለጥቃቅንና ለአነስተኛ ኢንተር ፕራዝ 10.51ሄ/ር 6 .ለመንገድና ለመንገድ ግንባታ27.15 ሄ/ር 7ለመዝናኛ ቦታዎች 5.88 ሄ/ር 8.የከተማ የግብር ቦታዎች 8.78ሄ/ር 9ለጫካማ ቦታዎች /ር 10. መጠባበቂያ ቦታዎች 18.95ሄ/ርበአጠቃላይ በወዳዉ ማዘጋጃ ቤቶች 642.39ሄ/ር መሬት ይገኛል፡፡
ጽ/ቤት ከሚተገብራቸዉ ተግባራት ዉስጥ
የከተሞች ማስፈጸም አቅም ግንባታና መሰረተ-ልማት ዘርፍ
የመሰረተ ልማት መስፋፋት ለከተሞች ማህበራዊ ልማት እና ለኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የሚታመን ሲሆን በከተሞች ልማትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ወሳኝ ሚና ያላቸው፣ የኮብልስቶን መንገድ፣ የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ፣ ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ዝርጋታ፣ የመንገድ ዳር መብራት እና የንጹህ መጠጥ ውሃ መስመር ዝርጋታ ከማቅረብ አንጻር በርካታ ስራ ተሰርቷል፡፡ በተጨማሪም የመሠረተ ልማት ጥገናና የማስተዳደር ሥራዎች እንዲሁም የከተሞችን የማስፈፀም ዓቅም ማጎልበት የሚያስችሉ ሥራዎች ተከናውኗል፡፡
ይሁን እንጂ የከተማ መሰረተ-ልማት አቅርቦታችንና አመራር ሥራዎች ከህብረተሰቡ አዳጊ የልማት ፍላጎት አንጻር ሲታይ ጉድለት ያለበት በመሰረታዊነት የጥራት፣ የፍትሀዊ ተደራሽነት እና የጥገናዎች ወቅታዊነት ጉዳይ ጎልተው የሚስተዋሉ ችግሮች መሆናቸው ታይቷል፡፡
ከተሞችን ጽዱ፣ ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭና ተስማሚ ማድረግ አንዱ የከተማ ዘርፍ ስራ ነው፡፡ ስለሆነም ባለፉት ዓመታት አመራሩን፣ ፈጻሚውን፣ ባለድርሻ አካላትንና የከተሞች ነዋሪዎችን በማሳተፍ በከተማ ፅዳትና አረንጓዴ ልማት ዘርፍ የሚታዩ መልካም ጥረቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲቻል ከመላው ህብረተሰብ ጋር በግልፅ መወያየትና ለዘላቂነቱም ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ ርብርብ ሲደርግ ቆይቷል፡፡ የከተሞች ጽዳት እና አረንጋዴ ልማት ሽፋን ከከተሞች የእድገት ደረጃ እና አዳጊ ፍላጎት አንፃር ሰፊ ጉድለቶች የሚታይ በመሆኑ የቀጣይ የትኩረት መስክ ይሆናል፡፡
በከተሞች ለዜጎች ቀልጣፋና ውጤታማ ማ/ቤታዊ አገልግሎት በግልፅነትና በተጠያቂነት እንዲቀርብና በዘርፉ የሚታየውን ብልሹ አሰራር በመታገል መልካም አስተዳደር ማስፈን ይገባል፡፡ ከዚህ አንጻር በፌደራል ደረጃ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ የወጣላቸውን አገልግሎቶች በከተሞች መተግበር የተጀመረ ሲሆን ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አቅርቦት ረገድ የዜጎችን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት በከተሞች እንዲዘረጋ ተደርጓል፡፡ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ ከፍተኛ ዉስንነት ያለበት መሆኑ ተለይቷል፡፡ በመሆኑም በማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ የነዋሪዎች የእርካታ ደረጃ በሚፈለገዉ ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ መረባረብ የሚጠይቅ ይሆናል፡፡
የህብረተሰቡ ተሳትፎ ፈጣን ልማት ለማምጣት፣የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሥርዓትን ለመገንባትና ለማጠናከር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ዜጎች በልማት፣ በዲሞክራሲና በመልካም አስተዳደር የሚኖራቸውን ምትክ የማይገኝለት ተሳትፎ ለማሳደግና ለማጠናከር የተለያዩ እርምጃዎችን ተወስዷል፡፡ በሴክተሩ ባለፉት ዓመታት ህብረተሰብ በአካባቢው ልማት ላይ የሚሳተፍበትና ባለቤት የሚሆንበት የልማት ተሳትፎ አደረጃጀት የመፍጠርና የማጎልበት ተግባር በመከናወኑ 21ቱን የመልካም አስተዳደር አጀንዳዎችን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡ ለልማቱ በገንዘብ፣ በጉልበቱና በቁሣቁስ የሚያደርገው ሰፊ ድጋፍ አበረታች ሥራዎች ፡፡በአጠቃላይ ህብረተሰቡ በአካባቢው ልማት ላይ የሚያደርገው ተሳትፎ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም ከነባራዊ ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር አሁንም ብዙ መስራትን የሚጠይቅ ነው፡፡
የእኖር ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት
አላማ
በወረዳ ተወዳሪና ብቁ የሆነ የኮንሰትራክሽ ኢንድሰትሪ ለመፈጠር ፡በከተሞች ለአካባቢ ልማትን በማፋጠን፡-የከተማ-የከተማና የከተማ -ገጠር ትስስርን በማጠናከር ለከተማ ልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ከተሜነትን ማሳደግናዘላቂ የሆነ ማህበራዊ ፡ኢኮኖሚዊ ልማት ማረጋገጥ ነዉ፡፡
ተልዕኮ
በወረዳ የሚገነቡ ግንባታወች ወጪ ቆጣቢና ጥራቱን የተጠበቀ ፤ከተሞች በፕላን በመምራት ፤ የመሬት አቅርቦት እና አስተዳደርን ግልጽ ቀልጣፋና ፍትሀዊ በማድረግ፤ የቤትና መሰረተ ልማት አቅርቦት በማሳደግ ፤አረን¹ዴ ልማት በማረጋገጥ ከተሜነትን በማስፋፋት ክፍለ ኢኮኖሚዉን ማሳደግ ነዉ፡፡
ራዕይ
በ2022 በወረዳ ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመገንባት ከተሞች ምርታማና የብልጽግና ማዕከል ሆነዉ ማየት ነዉ፡፡
እሴት
የመንግስት ፖሊስና ስትራቴጂ የዕቅዶቻችን መርሆዎች ናቸዉ፤የሰዉ ሐይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ትልቅ ሀብታችን ነዉ፤ በማያkርጥ ለዉጥና መሻሻል እናምናለን፤ተገልጋያችን የህልዉናችን መሰረት ናቸዉ፡፡
የተቋሙ ስልክ ቁጥሮች
0111 3320498
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834