የእኖር ወረዳ ምክር ቤት

ዋና አፈጉባኤ

የተከበሩ  አቶ መህዲ አህባብ

 

መግቢያ

በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ውስጥ መልካም አስተዳደር ማስፈን ዘላቂ ልማትና ሰላም ከፍተኛ ግምት የሚሠጠው ጉዳይ ነው፡፡ የዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብና ሉዓላዊነት የመንግስት ባለስልጠና ወይም የሌላ ማንኛውም አካል መብት ሳይሆን የህዝብ መብት ነው ህዝብና መንግስት ዕለት ተዕለት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ የሚኖራቸው ግንኙነት የወካይና የተወካይ ግንኙነት ነው፡፡ በዚህ መሠረት በሀገራችን የህዝብ ውክልና የሚረጋገጠው ከቀበሌ ም/ቤት ጀምሮ እስከ ፈደራል ድረስ በህገ-መንግስቱ በተቀመጠው መሰረት  ተወካይ በነፃና በቀጥተኛ ተሣትፎ በመምረጥ እና ተወካይነት ያላቸው የአስፈጻሚና የዳኝነት አካላት በማቋቋም የህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆኑን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡ በተመሣሣይ መልኩም የእኖር ወረዳ ም/ቤት የህዝብ ውክልና ከሚረጋግጥባቸው ተቋማት አንዱ ሲሆን በውስጡ 40 የገጠርና 3 የከተማ የቀበሌ ም/ቤቶች ተቋቁሞ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመቅረፍ፤ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲጐለብት፤ ልማትን ከማፋጠን አንፃር ጉልህ ሚናው ሲወጣ ቆይቷል፡፡

የእኖር ወረዳ ምክር ቤት ማብራሪያ

  • የእኖር ወረዳ ምክር ቤት ቀደም ሲል እ/ኤነር ወረዳ በነበረበት ወቅት በተሻሻለው የቀደሞ ደቡብ ህገ-መንግስት 1994 የምሰረት ጉባኤ በማድረግ

    ም/ቤቱ ተመሰረተ፡፡

  • የቀድሞ ነባሩ እነሞርና ኤነር ወረዳ እኖር ኤነር መገር ወረዳና ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ተካፍሎ ከወጡ በኃላ አሁን እኖር ወረዳ 40 የገጠር ቀበሌና 3 የከተማ ማዘጋጃ  በድምሩ ቀበሌ ምክር ቤቶች አሉት
  • የእኖር ወረዳ ምክር ቤት ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን 4 ዙር የአካባቢ ምርጫ የተደረገ ሲሆን 4ኛ ዙር ምርጫ በ2005 ዓ.ም ከተደረገ ወዲህ 38 መደበኛ ጉባኤ ተደርጓል፡፡

የተገኙ መልካም አጋጣሚዎች

የእኖር ወረዳ ምክር ቤት ከዞኑ ካሉ ወረዳ ምክር ቤቶች ግንባር ቀደም ሞዴል ምክር ቤት ሲሆን ም/ቤቱ የተሟላ አደረጃጀት ፈጥሮ ለህዝቡን ውክልና ለመውጣት እስከ ታችኛው ቀበሌ ም/ቤት በክልል ደረጃ ተሸላሚ የሆኑ ቀበሌ ምክር ቤቶች የፈጠረ ሲሆን የወረዳው ምክር ቤት ወርዶ በመደገፍ ከ12 ሞዴል ቀበሌዎች በመፍጠር በዞንና በክልል ደረጃ ተሸላሚ የሆኑ ቀበሌ ምክር ቤቶች የፈጠረ ሲሆን የወረዳው ምክር ቤት ለ10 ተከታታይ አመታት ከዞኑ 1ኛ በመውጣት እውቅና አግኝቷል፡፡ በርካታ ምርጥ ተሞክሮ ተቀምሮ እንዲሰፍን ከማድረግ ባሻገር ለበርካታ ወረዳ ምክር ቤቶች ልምድ በማካፈል ልምድ የሕዝብ ለህዝብ ግንኙነት እያጠናከረ ይገኛል፡፡

የእኖር ወረዳ ምክር ቤት ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች

ተልእኮ / Misión /

የምክር ቤቱን አሰራር በማሻሻል፣ በህብረተሰብ የነቃ ተሣትፎ ለወረዳው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና እና ፖለቲካዊ እድገት መፋጠን ፋይዳ ያላቸውን ህጎች በማውጣት፣አፈጻጸማቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር እና ቁርጠኛ የመንግስት አካላትን በማደራጀት የህዝብ የሥልጣን ባለቤትነት እንዲረጋገጥ፣ የግልፀኝነትና ተጠያቂነት ሥርዓት እንዲሰፍን እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድጎለብት ማድረግ ነው፡፡

ራእይ/ Vision /

በ2023ዓ.ም በወረዳው ውስጥ የህግ የበላይነት ሰፍኖ፣የመልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ዕውን ሆኖ፣ሁሉን አቀፍ የህዝብ ተሳትፎ ጎልብቶ፣ሰላም ፈጣንና ዘላቂ ልማት ተረጋግጦ ወረዳው ከዞኑ ሞዴል ሆኖ ማየት፡፡

 

እሴቶች/ Values /

  • ፍትሀዊነት መርሀችን ነው፡፡
  • ህዝብን በቅንነት ማገልገል መታወቂያችን ነው፡፡
  • የአሰራር ግልጸኝነትና ተጠያቂነት መለያችን ነው፡፡
  • ለህግ የበላይነት መከበር እንቆማለን/ እንሰራለን
  • ልዩነታችን አንድነታችን፣አንድነታችን ውበታችን ነው፡፡
  • አሳታፊነትና ቅንጅታዊ አሰራር መርሀችን ነው፡፡
  • ባህላዊ ዳኝነትን0 እናከብራለን፡፡
  • በስራ ክቡርነት በማመን ቁጠባን ባህል እናደርጋለን፡፡
  • ውጤታማነትንና መደጋገፍን እናተጋለን፡፡

              እሴት

  • ስራዎችን የጋራ አመለካክትን ከመፍጠር ይጀምራሉ;
  • በእቅድ እንመራለን;
  • ፍትሀዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነዉ
  • ጊዜ እና የሰዉ ሀይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶች ናቸዉ
  • ክራይ ሰብሳቢነት እንፀየፋለን
  • መረጃን ለልማት እናዉላለን
  • ወጤት ያሸልማል
  • ተገልጋዮቻችን የህልዉናችን መሰረት ናቸዉ
  • ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸዉ
  • የሴቶች የወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ እናረጋግጣለን;;
የተቋሙ ስልክ ቁጥሮች

  0113320125