የእኖር ወረዳ  ትራንሰፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት  ሀላፊ

አቶ ተመስገን ኑርጋ

የዋናው የአስፓልት ታሪክ

 መንገዱ የሚተዳደረው በፌድራል መንገዶች ባለስልጣን ስር ሲሆን ከጠጠር ጥርጊያ መንገድ ወደ ኮንክሪት አስፓልት ለመገንባት በ2010ዓ.ም በኢራ አማክኝነት ወደ ስራ የተገባ ሲሆን  የፕሮጀክቱም ስም አጣጥ ማዞሪያ ቆሴ-ሌራ በመባል ይጠራል፡፡የመንገዱ ርዝመት 81 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን በእኖር ወረዳ የሚገነባው 20 ኪ.ሜ ያክል ሽፋን ሲኖረው ከወርቃት እስከ ጉስባጃይ ደርኬ ወንዝ ድረስ የሚሸፍን ሲሆን አሁን ላይ መንገዱ በግንባታ ሂደት ላይ ይገኝል፡፡እስካሁን ከ50%በላይ የተሰራ ሲሆን በ2017 ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ይደረጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡

 

ከዋናው አስፓልት የተገናኙ መንገዶች

  • ከወርቃት-ኢባራኝ መንገድ 12 ኪ.ሜ
  • ጉስባጃይ-ጎራ መንገድ 7.5 ኪ.ሜ
  • ጉስባጃይ-አጋሬ መንገድ 9 ኪ.ሜ
  • ጉስባጃይ-ላቃ መንገድ 4.5ኪ.ሜ
  • ጉንችሬ-ኮሰድ መንገድ 8.5 ኪ.ሜ
  • ተርሆኘ-ጋዛንቸ ገረንቦ-ሆርበት መንገድ 39 ኪ.ሜ
  • ጉስባጃይ-እገዜ መንገድ 14ኪ.ሜ
  • ሸብራበር-ከረቤድ መንገድ 7.3ኪ.ሜ
  • ጉንችሬ-እስኩት መንገድ 28ኪ.ሜ
  • ጠረደ-ዳእምር መንገድ 9ኪ.ሜ
  • አሮደ-ካሳይ መንገድ 8.5ኪ.ሜ
  • አሮደ-ደንበር መንገድ 7.5ኪ.ሜ
  • ጠረደ-ጎንደሬጨ መንገድ 9ኪ.ሜ
  • ጉንችሬ-ማዞሪያ-ጎንቸቤቴ

ድልድዮች በተመለከተ

  • ከኮሰድ – አዘከረ መንገድ ላይ የእርሰ ሀራም ድልድይ
  • ከአሞገራ-ካናስ መንገድ የጎጓረ ወንዝ ላይ የቁረጨናየጢቆ ወንዝ ድልድይ ይገኛል
  • ከጋርዳሼ-ከረቤድ መንገድ ላይ የጎጓረ ወንዝ ድልድይ ይገኛል
  • ከከረቤድ – ጎምሸ መንገድ ላይ የናኳብ ወንዝ ድልድይ ይገኛል
  • ከሻፋሞ- ወርደነ መንገድ ላይ የወንቄ ወንዝ ድልድይ ይገኛል
  • ጋዛንቸ-ዊንቄ ድልድይ
  • ጋዛንቸ-ገረንቦ መንገድ ላይ ትልቁ ሀራም ወንዝ ድልድይ ይገኛል
  • ከገረንቦ-ሆርበት ዚዞ መንገድ ላይ የትንሹ ሀራም ወንዝ ድልድይ ይገኛል
  • ጉስባጃይ-እሰኸር መንገድ ላይ ጎጋረ ወንዝ ድልድይ ይገኛል
  • ዋናው መንገድ ላይ የወንቆ ወንዝ ድልድይ፤ትልቁ ሀራም ድልድይ-ትንሹሀራም፤ጎጓረ እና ደርኬ ወንዝ ድልድይ ይገኛሉ፡፡
  • ጉንችሬ-አውቃቅር የእርስ ሀራም ድልድይ ናቸው፡፡

 

በዩራፕ የተሰሩ መንገዶች

  • ከመቀረጥ-አዘከረ 6ኪ.ሜ
  • ጉንችሬ-ኮሰድ 8.5ኪ.ሜ
  • ወርቃት-እገበኝ 12ኪ.ሜ
  • ጉስባጃይ-አጋሬ 9ኪ.ሜ

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገዶች ባለስልጠን ከ25 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው በእኖር ወረዳ ሻፋሞ ሴባደን መንደር በኩል ወደ ወርደነ አጣጥ ሆስፒታል የሚያሻግረው የዊንቀ ወንዝ ድልዲይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት እየተደረገ ይገኛል።

ተልዕኮ

በወረዳችን ህ/ሰብ የተቀናጀ ልማት ለማልማት የሚያስችሉ የተለያዩ ደረጃ ያለቸው መንገዶች በማጠናከር የአሽከርካሪዎችንና የተሸከርካሪዎችን ብቃት በማረጋገጥ እና የህ/ሰቡን የመንገድ

አጠቃቀምና ትራፊክ ደህንነት ግንዛቤ በማሳደግ የትራንስፖርት ተጠቃሚነትና ደህንነትን እውን ማድረግና መላውን ህዝብ በማደራጀትና በማነቃነቅ በሴክተሩ ዕቅድ ዝግጅት አፈፃፀምና ውጤት ላይ ማድረስ መቻል ፡፡

አላማ

የዚህ ዕቅድ ክንውን አላማ ሴክተሩን የተሠጠውን ኃላፊነትንና ተግባር በስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ ለመምራት በሁሉም ደረጃ በሉ ፈፃሚዎች መካከል ተግባቦትን ፈጥኖ የላቀ ውጤት ለማስመዘገብ እና ውጠየቱንም መከታተል መለከትና የማስተካከያ ርምጃ መውሰድ እንዲያስችለው ለማድረግ ነው ፡፡

ራዕይ

በሚቀጥለው አመታት ህብረተሰብ ወደ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ አስተማማኝ የመንገድ አውታርና የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኖ ማየት

እሴቶች

  • ጥራት ግልጽነት ተጠያቂነትና ፍትሃዊነት የሴክተር መለያ እናደርጋለን
  • ቀልጣፋ አገልግሎትና ውጤታማነትን ሚረጋገጥ የተግባራችን ስኬት ዋና መለኪያ ናቸው
  • ህ/ሰቡን ያሳተፈ ልማት ላይ እናተኩራለን
  • ሀብትን በአግባቡ በቁጠባ እንጠቀማለን
  • በጋራ እንሠራልን ስኬቱም የጋራችን ነው
  • የመያ ስነ-ምግባር መጠበቅ መለያችን ነው
  • ሙስና እንፅየፋለን
  • ለደንበኞቻችን እርካታ ቅድሚያ እንሠጣለን ፡፡
  • ውጤት ያሸልሚል

የተቋሙ ስልክ ቁጥር 011 332 08 18