የእኖር ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፊ
አቶ ተኸርቁ ይርጋ
መግቢያ
በእኖር ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የገቢ አሰባሰብ ውጤታማነትና ዘለቄታው ተጠብቆ ለማቆየት እንዲቻል በበጀት አመቱ ያስመዘገብናቸው የልማት፤ የዴሞክራሲና የመ/አስተዳደር ስራዎች ለማረጋገጥ ሊረዳ የሚችል ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት፣ በመቀመርና በማስፋት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የምንችልበት አቅጣጫ በመከተል ዕቅዶቻችን ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ በዚህ መሰረት የተጣሉ ግቦች ለማሳካት የመፈፀም አቅም በማጎልበት የተሻሻሉ አሰራሮችን በመጠቀም በመንግስት የተነደፉ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን ለመፈጸምና ለማስፈጸም እንዲረዱ የወጡ አዋጆች፣መመሪያዎችና ደንቦች በመተግበር እንዲሁም የተለያዩ የልማት ፕሮግራሞች ስኬታማ እንዲሆኑ በትግበራ ሂደት የተገኘ ምርጥ ተሞክሮ ማስፋት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም የገቢ አሰበሰብ ስርዓቱ በ10 ዓመቱ መሪ እቅድ መነሻ ያደረጉ ግቦች በመለየት ለህብረተሰቡ እሴት ሊጨምር ሚችል መልኩ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆኑ በየወቅቱ ደረጃውን የጠበቀ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እንዲሁም ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ስልቶችን በመቀየስ የንብረት አያያዝ ስራዎች አፈጻጸማቸው የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ የተኬደበት ርቀት የተሸለ በመሆኑ እንደ ምርጥ ተሞክሮ በመውሰድ ተቋማት ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል አቅም የመፍጠር ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ ለዚህም ይሆን ዘንድ ለምርጥ ተሞክሮ ቅመራ የተመረጠው በእኖር ወረዳ ገቢ ጽ/ቤት የገቢ አሰባስብ ስራዎች አፈጻጸም ውጤታማነት ላይ እንደ ምርጥ ተሞክሮነት ተወስዶዋል፡፡
የጽህፈት ቤቱ ገጽታ፤
ተቋሙ 1998 አ.ም ድረስ በወረዳው ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት የገቢ አሰባስብ እንደ አንድ ስራ ሂደት ሆኖ የቆየ ሲሆን ከ1998 አ.ም በሀምሌ ወር ታክስ አስተዳደር ጽ/ቤት ሆኖ እራሱ ችሎ ወጥቶዎል ፡፡ አሁን ወቅት ገቢዎች ጽህፈት ቤት በውስጡ 2 ዋና ስራ ሂደቶችን 3 ደጋፊ ስራ ሂደቶችን በድምሩ 5 ስራ ሂደቶችን የያዘ ተቋም ነው፡፡የእነሞርና ኤነር ወረዳ ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት በሚያደርገው እንቅስቃሴ በየደረጃው አደረጃጀቶችን በማቋቋምና በማጠናከር በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡በዚህም በወረዳው መንግስት የተጀመረውን የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የወረዳው ሕዝብ በሙሉ አቅሙ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተገልጋዩ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት ከመንግስት የሚሰጠው አገልግሎት ውጤታማ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሀዊ እና ተደራሽ እንዲሆንለት ሕዝቡን/ተገልጋዩን የእቅዱ አካል/ባለቤት በማድረግ በመሠረታዊ ግንባታ ስራ ሂደት ለውጥ ጥናት መሠረት እቅዱ የተሟላ ሆኖ እንዲተገበር በህዝብ ክንፍ 2 ቲም ቡድን 1፣በአንድ ኮማንድ ፖስትና 1 ማኔጅመንት በመደራጀትና በታቀደው እቅድ መሠረት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ተግባሩ በተያዘለት እስታንዳርድ መሠረት ከጊዜ፤ ከመጠንና ከጥራት አንጻር ውጤታማ እንዲሆን ተልዕኮ ማስፈጽሚያ በመመሪያው መሠረት ሁሉም አደረጃጀት በባለቤትነት ይዞ እየሰራ የሚገኝ ጽ/ቤት ነው፡፡የእኖር ወረዳ ገቦዎች ጽ/ቤት ተብሎ በሁለት ዋና ዋና ስራ ሂደቶች ማለትም የገቢ አሰባሰብ ዋና የስ/ሂደት፤ የምጣኔ ትናት የታክስ ትምህርት እና ቅሬታ አጣሪ ዋና የስ/ሂደት እና በሶስት ደጋፊ ስራ ሂደቶች ማለትም የል/ዕ/ዝ/ክ/ግማገማ ደ/የስ/ሂደት፣በሰ/ሀ/ስ/አመራር ደጋፊ ስ/ሂደት እና የስነ ምግባር መከታተያ ክፍል ተሿሚዎችን ጨምሮ 30 የሰራተኛ መዋቅር ያለው ሆኖ በመደራጀት የወረዳው የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎት እድገት ወደ ተሻለ ደረጃ ደርሶ የህዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሊረጋገጥ የሚችልበት ሁኔታ ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት ሲያርግ ቆይቶዋል፡፡
የእኖር/ወ/ገቢ/ጽ/ቤት የስሙ ስያሜ ያገኘው በአዋጅና በመመሪያ እንዲያስፈጽም ተብሎ ከተሰጠው ገቢ አሰባሰብ ላይ መሰረት በማድረግ ሲሆን ይህን ስያሜና ተልዕኮ ከተሰጠው ጊዜ ጀምሮ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት የወረዳውን ሁለንተናዊ የገቢ እድገት በማፋጠንና የተሳለጠ በማድረግ የህ/ሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጽ/ቤቱ በመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ መሰረት በ2 ዋና የስራ ሂደቶችና በ3 ደጋፊ የስራ ሂደቶች የተዋቀረና በየስራ ሂደቱም በግብዓትና በሰው ሀይል የተሟላ በመሆኑን ወ 17 ሴ 4 በድምሩ 21 የሰው ሀይል ያለው ሲሆን ይህም ከጠቅላላው 76 በመቶ በማድረስ በበቂ የሰው ሀይል ማደራጀት ተችሎዋል፡፡
የወረዳው የገቢ አማራጮች
ቀጥታ ታክስ ,ተጨማሪ እሴት ታክስ, ቀጥታ ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች በትንሽ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የወረዳው የገቢ ታሪኮች በተመለከተ በዚህ ላይ የተወሰነ ልዩነቶች አለበት እንደ ተቋሙ መረጃ የሚያሳየው ከ2000 ዓ.ም እስከ 2011 ድረስ ወረዳው ገቢ ሲሰበሰብ የነበረው በ72 የገጠር ቀበሌ እና በ5 የማዘጋጃ ከተሞች ነበር በ2011 ዓ.ም ጀምሮ አዳዲስ መዋቅሮች ተፈጥሮ ወረዳው ለ3 የተከፈለ በመሆኑ በአሁን ሰዓት ወረዳው ገቢ እየሰበሰበ ያለው በ40 ቀበሌ እና በ3 የማዘጋጃ ከተሞች ነው ስለዚህ ተቋሙ የገቢ እድገቱ በሁለቱም ዘርፎች ላይ የገቢ እድገቱ እያደገ የመጣበት ሁኔታ ላይ ነው፡፡
የማዘጋጃ ቤቶች የገቢ ታሪኮቸው ሲታይ አሁን ላይ ያሉት የማዘጋጅ ከተሞች የተመሰረተን 3ቱም 2006 አ.ም ሲሆን ካላቸው የእድሜ ደረጃ እና ከተማ ስያሜ ካገኑበት ጊዜ አንስቶ ያልተማከለ አገልግሎት በመስጠት እራሳቸው በራሳቸው እንደያስተዳድሩ ተዋቅሮዋል የገቢ ሁኔታቸው ሲታይ 2006 1 ሚሊየን ብር ከነበረበት በአሁኑ ሰአት 2016 አ.ም 3 ሚሊዬን ብር ወደ መሰብሰብ ደርሰዋል የገቢ አማራጫቸው ሲታይ ከገቢያ መደብ ከግብርና ምርት ዝውውር ከጣራና ግድግዳ ኪራይ እንዲሁም ከበረት አገልግሎት ከሊዝ ኪራይ ውል ገቢያቸው ይሰበስባሉ፡፡
የተሰበሰበ ገቢ በዋና ዋና አርዕስት | የተሰበሰበ 1998 | የተሰበሰበ 1999 | የተሰበሰበ 2000 | የተሰበሰበ 2001 | የተሰበሰበ 2002 | የተሰበሰበ 2003 | የተሰበሰበ 2004 | የተሰበሰበ 2005 | የተሰበሰበ 2006 |
የመደበኛ ገቢ ድምር | 8790674.67 | 14861663 | 9793340 | 12918088.55 | 13574000 | 17149103 | 18403493 | 22765942 | 27500674 |
የማዘጋጃ ገቢ ድምር |
|
|
| 1,230,000 | 2235133 | 2086223 | 2143841.7 | 2892755 | |
ጠቅላላ የተሰበሰበ ገቢ |
|
|
| 14,804,000 | 19384236 | 20489716 | 24909783 | 30393429 |
የተሰበሰበ ገቢ በዋና ዋና አርዕስት | የተሰበሰበ 2007 | የተሰበሰበ 2008 | የተሰበሰበ 2009 | የተሰበሰበ 2010 | የተሰበሰበ 2011 | የተሰበሰበ 2012 | የተሰበሰበ 2013 | የተሰበሰበ 2014 | የተሰበሰበ 2015 | የተሰበሰበ 2016 |
የመደበኛ ገቢ ድምር | 37305915 | 39811124 | 51163183 | 62660109.4 | 66654862 | 41891394 | 65234281 | 84207719 | 110771282 | 120058028 |
የማዘጋጃ ገቢ ድምር | 3953112 | 49582216 | 67729955 | 10720335 | 5693471 | 481581.1 | 893054 | 2194521 | 2302440 | 2546950 |
ጠቅላላ የተሰበሰበ ገቢ | 41259027 | 44769540 | 57893138 | 73380444.4 | 72346322 | 42372975 | 66127335 | 86402241 | 113073723 | 122604979 |
የተቋሙ ስልክ ቁጥሮች 01133200169/311/084/405/331
የጽ/ቤቱ ራዕይ /Vision/
በ2022 ዓ/ም የወረዳው የገቢ አስተዳደር ሥርዓት ዘመናዊና ፍትሐዊ ሆኖ ለልማት የሚውል አስተማማኝ ገቢ ተሰብስቦ ማየት፡፡
የጽ/ቤቱ ተልዕኮ /Mission/
የተቋሙን አቅም በመገንባት ዘመናዊ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የገቢ ሥርዓት በመፍጠር፣ የተገልጋዩን የግብር/ታክስ ግንዛቤ በማጐልበትና የግብር ግዴታውን በራሱ ተነሳሽነት እንዲወጣ በማስቻል ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ለወረዳው ልማት የሚውል አስተማማኝ ገቢ መሰብሰብ፣
የጽ/ቤቱ እሴቶች /Values/
- ተገልጋዮቻችንን በቅንነትና በትህትና ማገልገል ባህላችን ነው ፣
- ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው፣
- ሙያዊ ሥነ-ምግባር መላበስ መለያችን ነው፣
- ፍትሐዊነት ፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ማስፈን የተአማኒነታችን ማረጋገጫ ነው፣
- መልካም የሥራ ግንኙነት መፍጠር የጋራ አመለካከታችን ነው፣
- ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችንናአጋሮቻችን ናቸው፡፡
- በመማርና በመደገፍ መልካም የስራ ግንኝነት መመስረት የተቋማዊ ውጤታችን ምንጭ ነው
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834