የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ

 አቶ ጅላሉ ጀማል

 

በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  ማህበራዊ ሚዲያ 

                መግቢያ
መንግስት ልማትና ዴሞክራሲን ለማስፈን እና የሀገራችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማፋጠን ከተዘረጉ በርካታ ተቋማት የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሴክተር በመንግስት የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ስርዓት ውስጥ ጉልህ ሚና በመጫወት በመንግስትና በህብረተሰቡ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የኢንፎርሜሽን ፍሰት እንዲኖር በማድረግ በዋና ዋና ወረዳዊ፣ዞናዊ፣ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሄራዊ መግባባት በመፍጠርና በጎ ገጽታን በመገንባት ረገድ ጉልህ ሚናን የመጫወት ተልዕኮን አንግቦ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነዉ፡፡

 

 

 

የጽ/ቤቱ አመሰራረት

የወረዳው የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ከተመሰረተበት ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ስያሜ እየተጠራ ከ1996ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም በባህል ቱሪዝምና ማስታወቂያ ጽ/ቤት እንዲሁም ከ2010 ዓ.ም መጨረሻ እስከ 2011ዓ.ም ድረስ በአስተዳደር ጽ/ቤት ስር የህዝብ ግንኙነት ዩኒት በሚል አደረጃጀቱን እየተለዋወጠ ቆይቷል።

አንዲሁም ከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 180/2012 መሰረት የደቡብ ብሄር፣ብሄረሰቦችና ህዝቦችና ክልል መንግስት የእነሞርና ኤነር ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሚል የተደራጀ ሲሆን በ2014 ዓ.ም መጨረሻም የወረዳው ስያሜ ሲቀየር የእኖር የወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሚል ተቋቁሟል።

የተቋሙ ስያሜና አደረጃጀት በተደጋጋሚ ሲቀያየር የነበረ ቢሆንም የተሰጡትን ኃላፊነቶች ለመወጣት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች በመንደፍና ዕቅዶችን በማዘጋጀት የተለያዩ ወረዳዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በርካታ የተግባቦት ስራዎች ተሰርቷል፤እየተሰራም ይገኛል።

በተለይም በመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ዘርፉ ውስጥ ሚዲያ የሰላም፣የልማትና የዲሞክራሲ ትልሞች ዕውን በማድረግ ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚገቡ ወረዳዊ ትልሞችን በማሳወቅና በማስተማር ረገድ መጠነ ሰፊ ስራዎች ተሰርቷል።

እነዚህ የሚተላለፉ መረጃዎች በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረቱና ለሀገርና ለሕዝብ ግንባታ አወንታዊ አስተዋፅኦ ያላቸው መሆኑን በመገንዘብ ተገቢነታቸውን በጥልቀት ተገምግሟል።

ተቋሙ እነዚህ መረጃዎች ከሕዝብ ወደ መንግስትና ከመንግስት ወደ ሕዝብ ከሚያስተላልፍባቸው የሚዲያ ዘርፎች ውስጥ የህትመት፣ የኤሌክትሮኒክስና የፊት ለፊት አማራጮች በዋናነት ይጠቀሳሉ።

አንድ ሚዲያ ከላይ የተጠቀሱ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ሁሉ የራሱ ህግና ስርዓትን አክብሮ ካልተንቀሳቀሰም በሁለንተናዊ የዕድገትና የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዓላማዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል በመረዳት የተለያዩ የሚዲያ ሞኒተሪንግ ስራዎች በመካሄድ ላይ ነው።

በየደረጃው ሕዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለይቶ በማመላከት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር እንዲፈቱም ተቋሙ እየሰራ ይገኛል።

 

 

የጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

የተቋሙ ራዕይ
በ2025 ዓ.ም የወረዳችን ህዝቦች በላቀ መረጃ በልጽገው የጋራ ውሳኔ ሰጪነታቸው ተረጋግጦ በመካከላቸው እኩልነት፣ አንድነትና ወንድማማችነት ተጠናክሮ ማየት፣

የተቋሙ ተልዕኮ
ሁሉ አቀፍና አዳዲስ የኮሚዩኒኬሽን መገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶችን እንዲሁም የኢንቨስትመንት መረጃዎችን የሚሰጥ በጥናትና ምርምር የታገዘ አካታች የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ምቹ አካባቢ መፍጠር ነው፡፡

ዓላማ ፦

የመንግስት ህጎችና ፖሊሲዎችን የሚያውቅ፣ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያለው፣ በልማት ተሳታፊና ተጠቃሚ የሆነ (በመረጃ የበለጸገ )ህብረተሰብ መፍጠር ነው፡፡

☞እሴቶች
>የላቀ አገልግሎት መስጠት
>የፈጠራና የሃሳብ አመንጪነት አቅምን ማዳበር
>አክብሮትና አንድነት
>በሃሳብ አሸናፊነት ማመን
>ትብብርና የቡድን ስራ
>ኃላፊነትን መውሰድ

☞በተቋሙ ውስጥ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች፦
★የሚዲያና ኮሚኒኬሽን አገልግሎት
★የሚዲያ ሞኒተሪንግና የህዝብ አስተያየት አገልግሎት
★የመረጃ ማዕከልና ዲጅታል ሚዲያ አስተዳደር አገልግሎት

ከዚህ በታች ያሉ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊናሁሌም አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙ

ዩቲዩብ=
https://www.youtube.com/@EnorworedaGovernCommunication

ኢሜይል = Enorworedacommunica1@gmail.com

ፌስ ቡክ=https://www.facebook.com/profile.php?id=100066847094169&mibextid=ZbWKwL

ቴሌግራም=https://t.me/EnorWoredaGovernmentCommunica1