የእኖር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት
የእኖር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አ/መጂድ ጀማል (ከ 2/ 2/2015ዓ.ም ጀምሮ – )
መግቢያ
የግብርና ጽ/ቤት የህበረተሰቡን/የአ/አደሩን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በሀገራችን እያካሄድን ላለዉ የፀረ ድህነት ትግል የበኩሉን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ የግብርና ጽ/ቤት ዋና ዓላማው ሰዎች ያላቸውን ሀብትና እውቀት በማሰባሰብ ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ በመጠቀም የአ/አደሩንና የሌሎች ህብረተሰብ ክፍሎች ኢኮኖሚያዊ አቅምን በማጎልበት ምርታማነታቸውንና ገቢያቸውን እንዲያድግ ማድረግ ነው፡፡ በዚሁ ረገድ ግብርና በሀገሪቱ እየተካሄደ ላለው ዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት እንቅስቃሴ መሳካት፤ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ልማትን በማረጋገጥ መላውን ህዝብ ከድህነት ለማላቀቅ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ጥረት እውን ለማድረግ በመላው የህዝብ ተሳትፎና ንቅናቄ በማቋቋም፣ በማንቀሳቀስና በማብቃት የአ/አደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ በተለያዩ ጥናቶች ተጠቁሟል፡፡
ስለሆነም በዚህ የኢንፎርሜሽን ዘመን ተቋማችን በርካታ ውስብስብና ፈታኝ ሁኔታዎችን በማለፍ ብቁ ተወዳዳሪና ተመራጭ በሆነ መልኩ ለተገልጋዮች ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ሌት ተቀን በንቃት መስራት ይጠይቃል፡፡ የግብርና ዘርፎች ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በቁጠባ ላይ የተመሠረተ የሀብት አጠቃቀም ባህል አዳብሮ የህዝቡ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ወደላቀ ደረጃ በማድረስ በተጨማሪ የህዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተጣጥሞ እንዲጓዝ ለማድግ የሚያስችሉ ስራዎች ከልማት አጋሮች ጋር ተባብሮ በመስራት ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማረጋገጥና የዕድገቱ ቀጣይነት ማስጥበቅ ዋነኛውና ቁልፉ ተልዕኮው ነው ፡፡
ነባራዊ ሁኔታ
የእኖር ወረዳ በዞኑ ካሉት ወረዳዎች አንዱ ሲሆን በሰሜን ቸሀ ወረዳ፤በደቡብ ኢኖር ኤነር መገር ወረዳ፣በምስራቅ ጌታ ወረዳ እንዲሁም በምእራብ ከጊቤ ሸለቆ ጋር ይዋሳናል፡፡
የአየር ንብረቱም በተለምዶአዊ ቀጠናዎች ክፍፍል ደጋ 15% ፣ ወይናደጋ 55%፣ ቆላ 30% እንደሚሽፍን ይታሰባል፡፡ከባህር ጠለል በላይ ከ1800 እስከ 2860 ሜትር እንደሚደርስና አመታዊ የዝናብ መጠኑም ከ1200 እስከ 1350 ሚ/ሜ እና አማካይ የሙቀት መጠኑ ከ190c እስከ ከ210c ይደርሳል፡፡ ወረዳችን በ40 የገጠር ቀበሌዎችና በ3 የማዘጋጃ ከተማ የተከፋፈለ ሲሆን የወረዳው ቆዳ ስፋት 113467 ሄ/ር ነው ፡፡ ከዚህም ውስጥ 23,768.5ሄ/ር በአመታዊ ሰብል ፣ 66,367ሄ/ር በቋሚ ሰብል ፣ 1837ሄ/ር በግጦሽ መሬት ፣9,918.5ሄ/ር በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ደን ፣ 2120ሄ/ር በውሃ የተሸፈነ ሲሆን 2364ሄ/ር በሌሎች ፣5456ሄ/ር ወደፊት ሊለማና ሊታረስ በሚችል፣ 1636ሄ/ርሊታረስና ሊለማ በማይችል የተያዘ ነው ፡፡ ወረዳችን ለግብርና ልማት አመች ሲሆን በዋነኝነት የሚበቅሉት ሰብሎች ጤፍ፣ገብስ፣ሰንዴ፣ድንች፣በቆሎ፣ ገብስ ፣ባቄላ ፣አተር፣ ኑግ ፣ ተልባ ፣ቦሎቄ እና የተለያዩ አትክልቶችና ፍራፍሬዎች እንዲሁም ቡና ፣ እንሰትና ጫት ናቸው ፡፡ ከእንሰሰታ ዘርፍ አንፃር ሁሉንም የእንሰሳት አይነቶች ለማርባት ወረዳው ምቹ ሲሆን በአጠቃላይ 638,262 የቀንድ ከብት ፣46,225 በግ ፣ 299,265 ፍየል ፣ 710,875 ዶሮ ፣ 18,950 ፈረስ ፣ 7,274 በቅሎና 19,108 አህያ በወረዳችን ውስጥ ይገኛሉ ፡፡ ከወረዳው አጠቃላይ ህዝብ ውስጥ በአምራች እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ (15-64)ያለው 53% ሲሆን አምራች ባልሆነ የእድሜ ክልል የሚገኙ (ከ15 በታች እና ከ64 አመት በላይ) የሆነው 47% ነው ፡፡
ግብርና ልማት ጽ/ቤት
የወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት የአርሶ አደሩን ሁሉ አቀፍ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዋናው ዓላማ ያደረገ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ከወረዳው ሕዝብ ብዛት 85.36% የሚሆነው የገጠር ነዋሪ እንደመሆኑ መጠን በአመዛኙ የሚተዳደረው በግብርና ነው፡፡ በወረዳዉ 41 የልማት ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን 166 የልማት ጣቢያ ሠራተኞች ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም 72000 የሚሆኑ አባወራ/እማወራ አርሶ አደሮች ይገኛሉ፡፡ የልማት ጣቢያ ሠራተኛ፣ ከአባወራና እማወራ ጥምርታ ጋር ሲታይ 1ለ 1618 ነው፡፡ በወረዳዉ ውስጥ በ2015 ዓ.ም የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ያገኙ አርሶ አደሮች ብዛት 1124 ደርሷል፡፡
ሰብል ልማት
በወረዳው ዉስጥ የሚመረቱ ዋና ዋና የግብርና ምርቶች በቋሚ ሰብልነት የሚጠቀሱ እንሰት፣ቡና፣ጫት እዲሁም የተለያዩ የፍራፍሬ ዘሮች ለምሳሌ አቮካዶ፣ማንጎ፣ብርትኳን፣ፓፓያ፣ሎሚ፣ሙዝእና ሌሎች የቅመማቅመም ሰብሎች ይገኛሉ፡፡በበልግ ወቅት በቆሎ፣ድንች፣የጓሮ አትክልት እንዲሁም በመኸር ስንዴ፣ጤፍ፣ገብስ፣ማሽላ፣ኑግ፣አተርና ባቄላ ናቸዉ፡፡በወረዳው ዉስጥ በዋነኛነት ለምግብነት የሚዉሉትገብስ፣ጤፍ፣በቆሎ፤ስንዴና እንሰት ሲሆኑ ገብስ፣ስንዴ፣ጤፍና ጫት በዋነኛነት ለገበያ የሚመረቱ ሰብሎች ናቸዉ፡፡
በወረዳው በ2015 የመኸርና የበልግ ወቅት ለምርት ማሳደጊያ 4679 ኩንታል NPS እና 1164 ኩንታል ዩሪያ እና ከምርጥ ዘር በቆሎ 156.5 ኩንታል፤ስንዴ 300 ኩንታል፤ጤፍ 30 ኩንታል፤እና ድንች1000 ኩ/ል ጥቅም ላይ መዋሉን ከግብርና ጽ/ቤት የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
የእኖር ወረዳ መሬት ነክ መረጃዎች በተመለከተ
- ጠቅላላ ስፋት 113467
- በአመታዊ ሰብል የተያዘ 15707 ሄ/ር 3%
- በቋሚ ሰብል የተያዘ 59304 ሄ/ር
- የግጦሽ መሬት 7500 ሄ/ር
- በደን የተሸፈነ =7954
- በውሀ የተሸፈነ መሬት= 2120
- በሎሌች የተያዘ መሬት= 3364
- ወደ ፊት ሊታረስና ሊለማ የሚችል = 10882
- ሊታረስን ሊለማ ማይችል= 6636
- መሬት በማስለካት ሰርተፍኬት ያላቸው አ/አደሮች፡-
- በአባወራ ደረጃ =38851
- በእማወራ ደረጃ =1769
- በሞግዚት ደረጃ= 4
በጥቅሉ= 40624
ስራው የተጠናቀቀለት የገበሬ ማሰልጠኛ ያላቸው ቀበሌዎች ብዛት/በ2015ዓ.ም
ወርቃት ወንጬ ተርሆኘ ወ/ዘውያር ጠረደ ኮሰድ ሻፋሞ እናገራ አጫወደ ጋሳውዴ ጎንደሬጨ አሞገራ ገረንቦ ገሀራድ ሆ/ዚዞ መቃና ጎንቸቤቴ ሁረድ ጃቱ ሰንዲቃይ ጎምሼ ጋርዳሼ ደንበር ኧሰኸር ኧገበኘ አጋታ ኢባራኝ ኩነበር ዳእምር ካናስ ካሳይ አዋሰር ሻንቃ ጡማነ አንዳሆረ



ኢንቨስትመንት

ቡና

እርሻ

በአቫር ኤፐዊ ሜና
እኖር መና ኢንቨስትመንት ተከትሎ እየለማ ያሉ የቅባት ሰብሎች የሱፍ ሰብል በከፊል ጎብኙ
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834