የእኖር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት  ሀላፊ   

አቶ ሽኩረታ /ከሪም

መግቢያ፡

የመደበኛ ት/ት በኢትዮጵያ ለማስፋፋት አንድ አብይ ክስተት የሞቆጠረው ድርጊት በዳግማዊ ምኒሊክ ዘመን የተከናወኑ በንጉስ ነገስቱ ስም የሚታወቀው ት/ቤት በ1900 ዓ.ም መከፈቱ ነው፡፡

የዘመናዊ ት/ት ፍላጎት እያደገ መምጣት የጀመረው የ19ኛው መቶ ኣመት መሆኑን ከዳግማዊ ድል በኋላ ኢትዮጵያ ከአውሮፓና ከአውሮፓውያን ጋር ያላት ግንኙነት እየተጠናከረ ሲሄድ ዘመናዊ ት/ት ለማስፋፋት አመቺ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት ያመለክታሉ፡፡ይሁን እንጂ ነባሩ የኢትዮጵያ ት/ት ሥርዓት የሚጀምረው ግን በዘመነ አክሱም ከአራተኛው መቶ ዘመን ጀምሮ መሆኑም ይገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ ት/ት በተማከለ ወይም ባልተማከለ መልኩ በተለያዩ አካላትና ተቋማት አስተዳደር ስር እስከ 20ኛው መቶ ኣመት መባቻ ድረስ መከናወኑም ይጠቀሳል፡፡በወቅቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውጪ ሀገራት ጋር የፈጠራቸው ግንኙነት የበለጠ በማጠናከሩና ዘመናዊነትንም በሆስፒታል፣በባቡር፣በባንክና መኪና ወዘተ በኢትዮጵያ መከሰትን ተከትሎ የዘመናዊ ት/ቤቶች መስፋፋትም ተምሳሌት ቢሆንም ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡

ከሀገራችን ማእከል የተጀመረው ዘመናዊ ት/ት እንዲህ እንዲህ እያለ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መስፋፋቱ የሚታወስ ሲሆን በወረዳችን የዘመናዊ ት/ት የበለጠ መስፋፋት ፈር ቀዳጅ ት/በት አዋስር ት/ቤት ሲሆን ት/ቤቱ 1953 ዓ.ም ማስተማር የጀመረ ሲሆን በወቅቱም ለመማር ፍላጎት እያለው ግን ደግሞ ት/ቤት ካለመኖር ብቻ የመማር እድል ያላገኙ ብዙ የማ/ሰብ ክፍል ይህን እድል በመጠቀም በት/ቤቱ ገብቶ መማር እንደጀመረ ታሪኮች ያወሳሉ፡፡ት/ቤቱም ስራ ሲጀምር በጠቅላላው 17 ተማሪ ሆኖ በየዓመቱ የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር እያደገ መጥቷል፡፡ እንዲህ እንዲህ እየተባለ አዋስር ት/ቤት ተከትሎ ጉንችሬ ቁ1 እና ጡማነ ት/ቤቶች ተከፍተው ማስተማር ጀመሩ፡፡ በነዚህ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተምረው ያጠናቀቁ ተማሪዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸው ለማስቀጠል በወረዳው የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ካለመኖሩ የተነሳ አቋርጠው ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች  ለንግድ ስራ ሲሄዱ እንደነበር ሲጠቀስ ነገር ግን ጥቂት ቤተሰቦቻቸው በኢኮኖሚ የተሻሉ ተማሪዎች ለብዙ ዘመናት እምድብር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሄደው የሚማሩበት አግባብ ነበር በጊዜ ቆይታ የት/ት ተደራሽነት ለማስፋፋት በተሰራው ስራ በወረዳችን የመጀመሪያ የሆነው የጉንችሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 1980ዓ.ም ተከፍቶ ማስተማር ጀመረ፡፡ እንዲህ እንዲህ ብሎ  የጀመረው የወረዳችን የት/ት አጀማመር ታሪክ አሁን ላይ በ45 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶችና በ7 የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እድሜው ለት/ት የደረሰ ህጻን በሙሉ ወደ ት/ቤት ገብቶ በየአቅራቢያው ተገቢውን ት/ት ማግኘት የሚችሉበት ዘመን ላይ ደርሷል፡፡ የሀገራችንም የወረዳችንም የት/ት ታሪክ ሲወሳ ዘርፈ ብዙ የፍትሀዊነት ችግር የነበረበተ ሲሆን ከዚህም ጋር በከተማና በገጠር ደረጃ የሚጠቀስ ት/ቤቶች በአቅራቢያ አለመኖር ማለትም በከተማዎች ት/ቤት በቅርበት የሚገኝ ሲሆን በገጠር ደረጃ ት/ቤት ለማግኘት እጅግ ብዙ ኪ/ሜትር አቋርጠው የመጓዝ ሌላኛው የፍሀዊነት ችግር የወንድና የሴት የት/ት እድል ለማግኘት ልዩነቶች ሲሆን መማር ለወንድ ብቻ የተፈቀደ በሚመስል መልኩ ሴት ልጅ ለመማር እድል አለማግኘት የኢኮኖሚ ብሎም የማንነት ጉዳዮች መነሻ በማድረግ እኩል የመማር እድል አለማግኘት በታሪክ የሚጠቀሱ የት/ት ፍትሀዊነት ችግሮች ሆነው ቆተው ነገር ግን በተለያ ስርዓቶች በተወሰዱ እርምጃዎች አብዛኞቹ የት/ት ፍትሀዊነት  ችግሮች አገር ላይ መቅረፍ ተችሏል፡፡

በ2016ዓ.ም ከ1-12ኛ ክፍል ለመማር የተመዘገቡ ተማሪዎች ወ 11433 ሴ10081 ድ 21514

የወረዳው የት/ት ሽፋን በተመለከተ ፡-

በወረዳው የት/ት ሽፋን ተደራሽነት አንጻር ስራዎች የተሰሩ ሲሆን የቅ/መ ት/ቤቶች ሽፋን 2013ዓ.ም ከነበረበት 130 በ2016ዓ.ም 137 በማድረስ 1.05% እድገት አሳይቷል፡፡ በሌላ በኩል የመደበኛ ት/ቤቶቻችን ተደራሽነትና ሽፋን አንጻር በ1ኛ ደረጃ ሙሉ ለሙሉ ሽፋኑን ማዳረስ የተቻለ ሲሆን የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሽፋን 2013ዓ.ም 5 ከነበረበት በ2016ዓ.ም 7 በማድረስ የ14% እድገት አሳይቷል፡፡ የቅ/መደበኛ ጥቅል ተሳትፎ በ2013ዓ.ም 79 ከነበረበተ በ2016ዓ.ም 92 ማድረስ ተችሏል ንጥር ተሳትፎ ደግሞ 53 ከነበረበት 83 ማድረስ ተችሏል፡፡

የመደበኛ ተማሪዎች የ1ኛ ደረጃ ጥቅል ተሳትፎ በ2013ዓ.ም 84.2 ከነበረበት በ2016ዓ.ም 94.3 ማድረስ ተችሏል ንትር ተሳተትፎ ደግሞ 81 ከነበረበት 89 ማድረስ ተችሏል፡፡

በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጥቅል ተሳትፎ ከ22 ወደ 78 ማድረስ መቻል ንጥር ተሳትፎ ደግሞ 60.5 ከነበረበት ወደ 69 ማድረስ ተችሏል፡፡

አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላት

በወረዳው የት/ቤቶች ደረጃ ከማሻሻል ጋር የወረዳችን የት/ቱ ማ/ሰብ ጉልህ ሚና የሚጫወት ሲሆን በየዓመቱ ከ30-40 ሚሊየን ብር በማሰባሰብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩል በወረዳችን ብሎም በዞናችን በት/ት ስራ ላይ ሁሌም አሻራቸው የማይጠፋ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋው በየዓመቱ ት/ቤት በመገንባት ፣በመጠገንእና ተማሪዎእ በመርዳት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡

ወርልድ ቪዥን ፣ካቶሊክ ድርጅት፣ዋንዋሽ፣አቶ አሰፋ አይጎዳ ፣አቶ ማይክል የወረዳችን ተወላጅ የከተማ ባለሀብቶቻችን ብሎም በት/ት ስራ ላይ ተመድበው እያገለገሉ ያሉ የት/ቤት መ/ራን ፣ር/መ/ራን ፣ ሱ/ሮች አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

ኢ/ለርኒንግ የሚጠቀሙ ት/ቤቶች ብዛትና ዝርዝር

ኢ/ለርኒንግ የሚጠቀሙ ት/ቤቶች ብዛት 30 ሲሆን እነዚህም ጋርባዶ 2ኛ ፣ኧገዜ 2ኛ፣ ኢፋቦሩ ፣ሸብራበር 2ኛ፣ጋዛንቸ 2ኛ ፣ጎምሸ 2ኛ፣ተርሆኘ 2ኛ፣ተርሆኘ 1ኛ ፣ ሻፏሞ ፣ ወርቃት 1ኛ ፣ ጃቱ ፣ አጋሬ ፣ ጎ/ቤቴ ፣ ጋርዳሼ ፣ ሰንዲቃይ ፣ ኧገዜ 1ኛ ፣ ጡማነ ፣ ወ/ዘውያር ፣ አዋስር ፣ ካናስ አዲስ ፣ ካናስ 1ኛ ፣ አጋታ ፣ ጋሳውዴ ፣ እገበኘ ፣ ካሳይ ፣ ሸብራበር 1ኛ ፣ ጎምሸ 1ኛ ፣ ደንበር 1ኛ እና አቦጋዴ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

 

                     

በ2016 ዓ.ም የትምህርት ልማት ግቦች ማሳካት ሲሆን ዝርዝር ዓላማዎችም፣

በትምህርቱ ሴክተር ጠንካራ የትምህርት ልማት ሠራዊት በመፍጠር፣ በተደራጀ አኳኋን በመምራትና በማንቀሳቀስ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጁን ሙሉ በሙሉ በመተግበር የተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግባር እንዲሻሻል ማድረግ፣

የትምህርት ጥራት ተደራሽነት እና  ፍትሃዊነት  ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን

በየደረጃው የሚታየውን የአመለካከት፣ የክህሎትና የግብአት አቅርቦት ማነቆዎችን መፍታት፣

ሦስቱን የክትትልና የድጋፍ መስተጋብሮችን (በሪፖርት፣ በአካል በመገኘትና ግብረ መልስ በመስጠት) በመጠቀም ተከታታይነት ያለው የክትትልና ድጋፍ እና የግብረ መልስ ስርዓት በመዘርጋትና ተግባራዊ በማድረግ የትምህርት ስራችንን ውጤታማ ለማድረግ ናቸው፡፡

አሁን ላይ በወረዳችን በ90 የተ/ተ/ተጎ/ት/ት ጣቢያዎች 5704 ተማሪዎች በመማር ላይ ይገኛሉ፡፡ሌላው መደበኛ ት/ቤቶቻችን 1ኛ ደረጃ 45 ት/ቤቶች 2ኛ ደረጃ 7 ት/ቤቶች እና 14 የክላስተር ማእከላት ያሉን ሲሆን በጠቅላላው ወ105909605  ድ 20195 ተማሪዎች ት/ታቸው ይከታተላሉእነዚህም ት/ቤቶችና ተማሪዎች በጠቅላላው 920 መ/ራን 52 ር/መ/ራን 14 ዙ/ሮች ተመድበው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ከላይ የተጠቀሱ ት/ቤቶቻችን አጠቃላይ ካላቸው ተማሪዎች ጋር ተያይዞ የተለያዩ የት/ት ጥምርታዎቻቸው ስናይ፡

የመ/ር ተማሪ ጥምርታ በ1ኛ ደረጃ 1ለ57 በ2ኛ ደረጃ 1ለ59

የተማሪ የመማሪያ ክፍል ትምርታ በ1ኛ ደረጃ 1ለ53 በ2ኛ ደረጃ 1ለ55

የተማሪ ወንበር ጥምርታ በ1ኛ ደረጃም በ2ኛ ደረጃም 1ለ3

የተማሪ መጽሐፍት ጥምርታ በ1ኛ ደረጃ 1ለ4 በ2ኛ ደረጃ 1ለ2 ጥምርታዎች ይጠቀሳሉ

ከት/ት ተቋማት ደረጃ ማሻሻል አንጻር፡- በወረዳው እስከ አሁን በተጠቃላይ የደረጃ ፍርጃ አንጻር በ1ኛ ደረጃ ካሉን 45ቱ ት/ቤቶች ደረጃ 3 በመግባት ለደረጃ ብቁ የሆኑ ት/ቤቶች 18 /34%/ሲሆኑ ቀሪዎቹ በደረጃ 2 የሚገኙ ናቸው በ2ኛ ደረጃ ከተገመገሙ 5 ት/ቤቶች 5ቱ ደረጃ 3 ላይ የተቀመጡ ሲሆነረ ቀሪዎቹ 2ቱ ሸብራበር 2ኛ እና ኢፋቦሩ 2ኛ ት/ቤቶች ቀድመው ቅድመ እውቅና ላይ የነበሩ አዲስ ት/ቤቶች በመሆናቸው የደረጃ ፍርጃ አልተካሄደላቸውም፡፡ በጥቅሉ የወረዳችን የት/ቤት ደረጃ መሻሻል ጋር ሁሉም ባለድርሻ ያሳተፈ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መከናወናቸው የሚጠቀስ ሲሆን በ2014ዓ.ም እና በ2015ዓ.ም ከነበረበት በ2016ዓ.ም 34%ማድረስ ተችሏል፡፡

የት/ቤቶች አድራሻ በተመለከተ

የት/ቤቱ ስም

የሚገኝበት ቀበሌ

ጋሃራድ

ጋሃራድ

ወ/ዘዉያር

ወሸ ዘዉያር

ወሻ አዋስር

ወሸአዋስር

ጋዛንቸ

ጋዛንቸ

ጎንደረጨ

ጎንደረጨ

ገረንቦ

ገረንቦ

ጋንቦ

አጫወደ

እገዜ 1ኛ

ኸገዜ

ጡማነ

ጡማነ

የት/ቤቱ ስም

የሚገኝበት ቀበሌ

ካናስ 1ኛ

ካናስ

ካናስ አዲስ

ካናስ

አጋታ

አጋታ

አቦጋዴ

አቦጋዴ

ኩነበር

ኩነበር

አዶሸ

አጋታ

ተርሆኘ

ተርሆኘ

ጠረደ

ጠረደ

ሻፋሞ

ሻፋሞ

ወርቃት

ወርቃት

የት/ቤቱ ስም

የሚገኝበት ቀበሌ

ጋሳዉዴ

ጋሳዉዴ

ሻንቃ

ሻንቃ

አሞገራ

አሞገራ

ከረቤድ

ከረቤድ

ደንበር

ደንበር

ሸብራበር

ማቃና

ጎምሸ 1ኛ

ጎምሸ

ማቃና

ማቃና

ወንጨ

ወንጨ

ኸሰኸር

ኸሰኸር

ሁረድ

ሁረድ

ኢባራኘ

ኢባራኘ

ዳአምር

ዳአምር

እገበኝ

እገበኝ

ካሳይ

ካሳይ

ጎ/ቤቴ

ጎ/ቤቴ

ሆ/ዚዞ

ሆ/ዚዞ

አጋሬ

አጋሬ

ጃቱ

ጃቱ

የት/ቤቱ ስም

የሚገኝበት ቀበሌ

ሰንዲቃይ

ሰንዲቃይ

ጉስባጃይ

ጉስባጃይ

ጓንታና

ጓንታና

ጋርዳሼ

ጋርዳሼ

አንዳሆረ

አንዳሆረ

እናንገራ

እናንገራ

ኮስድ

ኮስድ

ተርሆኘ 2ኛ  ደረጃ

ተርሆኘ

ጋዛንቸ  2ኛ

ጋዛንቸ 01

ጎምሸ 2ኛ ደረጃ

ጎምሸ

ሸብራበር 2ኛ

ማቃና

ጉስባጃይ ኢፋቦሩ 2ኛ

ጉስባጃይ 01

ኸገዜ 2ኛ

ኸገዜ 

ጋርባዶ 2ኛ

አጋታ

  
  
  
  
  

የት/ት ተቋም ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማና ዕሴቶች

ራዕይ

 በት/ት ሴክተር ፍትሓዊና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርትና ስልጠና በማዳረስ በዕውቀት፣በክህሎትና በአመለካከት የተስተካከለና የተሸሻለ የተማሪ ውጤት ለልማት፣ለፍትሕ፣ለሰላምና ለሀይማኖት እኩልነት ግንባታ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ትውልድ ተፈጥሮ ማየት

ተልዕኮ

ጥራቱና ብቃቱ የተረጋገጠ ፍትሓዊና ተገቢነት ያለው የትምህርት አገልግሎት ለህብረተሰቡ በመስጠት ልማትና እድገት አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሁለንተናዊ  ስብዕናው ያለው ትውልድ በመፍጠር የተፋጠነና ቀጣይነት ያለው ዕድገትና ልማት እንዲመጣ፣መደበኛና መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ፕሮግራም በመጠቀም ትምህርትን  በጥናትና ምርምር በማስደገፍ፣ህብረተሰቡን  በባለቤትነት  በማሳተፍና  አጋር ድርጅቶችና ባለሀብቶች  በማስተባበር የተገኘውን ሃብት በአግባቡ በመጠቀም ጠንክሮ መስራት

እሴቶች

ለለውጥ መስራት

የህዝብ አገልጋይነት

ታማኝነትና ቅንነት

ግልጸኝነትና ተጠያቂነት

ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር

ሁሌም መማር

በጋራ መስራት

ዓላማ፡-

የት/ት ጥራቱን፣ ሽፋኑን፣ ፍትሀዊነቱን እና ብቃቱን ቀጣይነት ባለው መልኩ ተግባራዊ በማድረግ በሁለንተናዊ ስብእና የታነጸ ትውልድ በመፍጠር በወረዳው ዘላቂነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ ተገቢውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው፡፡ 

 

የእኖር ወረዳ የተማሪዎች ኦንላይን መመዝገብያ ፎርም