የእኖር ወረዳ ኢ/ፕራዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ
አቶ ፈቂ ዲነካ
መግቢያ
የእኖር ወረዳ ኢ/ፕራዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ከጉራጌ ዞን እና ከተማ ወልቂጤ በ42 ኪ/ሜ ርቀት የሚገኝ በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በጉንችሬ ከተማ ከጉንችሬ ስፖርት ሜዳ አጠገብ ባለው ቁጥር 1አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በስተ ምእራብ የሚገኝ ሲሆን ጽ/ቤቱ ከወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በዘርፍ ከሚመራበት ብቻውን ችሎ የስራ እድል ፈጠራ እና የኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሆኖ በ2008 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን ጽ/ቤቱ በተለይ የስራ እጥ ወጣት ከመመልመል ግንዛቤዎችች በመፍጠር የሀገራችን ድህነት እንዲቀንስ እና የስራ እጥ ቁጥር እንዲቀንስ እና ወጣቶችን ግዜያቸው ጉልበታቸው እና ውስን ሀብት አጣጥሞ በመጠቀም የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሶስቱ የእድገት ተኮር ዘርፎች እንዲሰማሩ በማድረግ እርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡
ዝርዝር ስራዎች በተመለከተ
- እስከ አሁን ጽ/ቤቱ ከተመሰረተበት ጀምሮ በገጠርና በከተማ 15389 ወጣቶችን የስራ እድል እንዲፈጠጥርላቸው ተደርጎዋል፡፡
- እንደ ወረዳ በሶስቱ ከተሞች እና በ40 የገጠር ቀበሌዎች 21449 የስራ እጥ ወጣቶችን በመለየት የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጎዋል፡፡
- እንደ ወረዳ የስራ እጥ ወጣቶች ለማስጠቀም ያለ ምቹ ሁኔታዎች በተመለከተ
-ሰፋፊ ያልታረሱ ደግሞ የወል እና የግል መሬት መኖሩሰ
-በመስኖ ዘርፍ ወጣቶችን አደረጃጅቶ ለማስጠቀም አንድ የዘመናዊ መስኖ እና ከ23 በላይ የውሀ ማቆር እና የወንዝ የውሀ አማራጭ ስለመኖሩ
-መንግስቱ የብድር አማራጭ በማመቻቸት የብድር አቅርቦት ያመቻቸ ስለመሆኑ
-በርካታ ባለሀብቶች እና የኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ በመፈጠር የስራ እድል አማራጭ የሚሰጥ ሁኔታ መኖሩ
- እንደ ወረዳ አጋር ድርጅቶች በተለይ FSRP እና REED + ፕሮጀክት በተለይ ለስራ እጥ ወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ስራዎች እየሰሩ የሚገኙ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ለምሳሌ FSRP ለወጣቶች የግንዛቤ ስልጠና በመስጠት በዘር ብዜት ፤በንብ ማነብ፤በቅመማቅመም አደራጅቶ ወደ ስራ በማስገባት የግብርና መሳሪያዎች እና የዘር አቅርቦት ድጋፎችን በመስጠት ሰፊ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
- REED + ፕሮጀክት እንደዚሁም በደን ችግኝ ተከላ እና እንክብካቤ በድምሩ 189 የስራ እጥ ወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው በማድረግ እና በተጨማሪ ለሁለት ማህበራት በንብ ማነብ እና በበሬ ማድለብ በተፋሰስ በለሙ የወል መሬቶች ላይ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ማድረግ ተችሎዋል፡፡
- እንደ ወረዳ እስከ አሁን ድረስ በከተማ፤በገጠር ለሚገኙ ስራ እጥ ወጣቶች ስምሪት የሚያስፈልገው የብድር አቅርቦት በክልል ፤በዞን እና በወረዳ አስተዳደር ደረጃ ከሚመደቡት እንዲሁም ከብድር ተመላሽ ብር 3,1891165 ማሰራጨት ተችሎዋል፡፡
- በቀጣይ ለወጣቱ በጠቅላላ 54,258456 ብር የብድር አቅርቦት ለማመቻቸት በትኩረት ይሰራል፡፡
- ከብድር አመላለስ በተለይ ከ 2008-2016 ዓ.ም የሚሰራጩ ብድር ከማስመለስ አንጻር የተሸሻሉ ነገሮች ሲኖሩ በአብዛኛው ወጣት የተበደረው ብድር በወቅቱ ተጠቅሞ ለሌላ ወጣት እንዲሰራጭ ያለምንም ችግር የሚመለስበት አግባብ ያለ ሲሆን በተለይ ከቀድሞ የስራ እድል ፈጠራ የተሰራጨ ብሮች ከማስመለስ አንጻር አሁንም ጉለቶች ያለበት አግባብ አለ፡፡
ራዕይ
በ2020 አ.ም በአለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ የአምራች ኢንዱስትሪ ተፈጥሮና በወረዳችን የህብረተሰቡ ኢኮኖሚ እድገት ተረጋግቶ ማየት ነዉ;; እንደ ወረዳችን የስራ እጥ ቁጥር በእጅጉ እንዲቀንስ እና ምርትና ምርታማነትን እንዲጨምር ይደረጋል፡፡
አላማ
የጥቃቅንና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢነዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የሚደረገውን መዋቅራቂ ሽግግር ማፍጠን እንዲሁም ሰፊየስራ እድል እንዲፈጠር ማድረግ
በወረዳዉ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያሉ እምቅ አቅሞችን አሟጦ በመጠቀም ለከፍተኛ ኢንዱስትሪ ልማት ሰፊ መሰረት የሚጥሉ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክደቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ በማድረግ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ማረጋገጥ
የአነስተኘኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ተዎዳዳሪ ቀጣይነት ያለዉና ለኢንዱስትሪዉ ልማት
ጠንካራ መሰረት የሚጥል እንዲሆን ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን ማስተባበር
ወደ አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሚገቡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከሚመለከጻቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት መመልመል ወደ ዘርፍ የሚገቡትን ማደራጀት አዉቅና እንዲያገኘኙ ማድረግ
በወረዳዉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በማልማት ሰፊ የስራ እድል መፍጠር ሰፊ መሰረት ልማታዊ ባለሀብትና ኢንዱስትሪያሊስት እንዲስፋፉ ማድረግ;;
እሴት
- ስራዎችን የጋራ አመለካክትን ከመፍጠር ይጀምራሉ;
- በእቅድ እንመራለን;
- ፍትሀዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነዉ
- ጊዜ እና የሰዉ ሀይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶች ናቸዉ
- ክራይ ሰብሳቢነት እንፀየፋለን
- መረጃን ለልማት እናዉላለን
- ወጤት ያሸልማል
- ተገልጋዮቻችን የህልዉናችን መሰረት ናቸዉ
- ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸዉ
- የሴቶች የወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ እናረጋግጣለን;;
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834