የአካባቢ እና የደን ልማት ጥበቃ ጽ/ ቤት ሀላፊ
አቶ በቀለ በዙ
መግቢያ
የአየር ንብረትለውጥ ችግሮች የአለማችን ስጋት ከሆነ ውሎ አድሯል ፡፡ የችግሩ ስፋት አገሮች የአየር ንብረት ለውጡን ለማማቋቋም ካላቸው አቅም አኳያ ይለያያል አንጂ ሀብታም እና ድሀን አይለይም ፡፡በዚህም የተነሳ አገራት የተናጠልና የጋራ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ ፡፡ሀገራችንም ለአየር ንብረትለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ቀረጻ ለመተግበር በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች ፡፡በዚሁ መነሻ የወረዳው መንግስት የጉዳዩን አሳቢነት በመረዳት እና በ2017ዓ/ም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ከማድረግ አኳያ ለአከባቢ ጥበቃና ደን ልማት ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት የወረዳው የአስፈጻሚ አካላትን ባለስልጣን እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ጽ/ቤቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማውጣት እንዳስችለው በወረዳችን ለሚተገበረው ለሶስተኛው የእድገት አናትራንስፎርሜሽን “”እቅድ (ዕትዕ) የ2015 ዓ/ም/ የአከባቢ ጥበቃና ደን ልማት ሥራን በአግባቡ ለማስፈጸም ቀደም ሲል የታዩ ክፍተቶችን በመለየት በየደረጃው ህብረተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዘላቂነት ያለው አመታዊ የተግባር ዕቅድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል ፡፡ በጽ/ቤቱ የወረዳችንን የደን ልማት በማስፋፋት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሥነ-ምህደር እንዲጠበቅ በማድርግ በሀገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ የራሱን ድርሻ ያበረክታል ፡፡እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሰውን የድርቅ አደጋ በአስተማማኝ ደረጃ ለመቋቋም የደን ሀብታችንን ተንከባክቦ የተፈጥሮ ስርአተ-ምህዳሩ ሳይዛባ ለትውልድ ለማቆየት ፣ የተራቆቱ አከባቢዎች እንዲያገግሙ ማድረግ ፣ እየተመናመኑ እና እየጠፉ ያሉትን የብዝሀ -ህይወት ሀብቶች እንዲጠበቁ ማድረግ ፣ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው የደን ዛፎች እንዲተከሉና የወረዳው የደን ሽፋን ማሳደግ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡
ስለዚህ የሚጠበቀውን ፈጣንና ቀጣይት ያለውን ኢኮኖሚ እድገት በአካባቢ ላይ ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት የሚሹ ተግባራትን በመለየት ከባለ ድርሻና ተባባሪ አካላት ጋር ሊኖር የሚገባውን ትስስርና ቅንጅት በማጠናከር የደን ልማት ፣የአካባቢ ጥበቃ የብዝሀ-ህይወትና ልማትና ጥበቃ አጠቃቀም ስራዎችን የ2016 በጀት አመት እቅድ ከሶስተኛው የዕትዕ መነሻነት ተዘጋጅቷል ፡፡ ወረዳው ካለፈው አመት አፈጻጸም በመነሳት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የተመረጡ ግቦች ፣ዋና ዋና ተግባራትና የድርጊት መርሀ-ግብር ያካተተ የ2016 ዓ.ም የአመቱ የፊዚካል ስራዎች እቅድ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የተቋሙ ስልክ ቁጥር
ስልክ 0113320500
የጽ/ቤቱ ራዕይ ፤ ተልዕኮና ዕሴቶች
ራዕይ
በ2015 ዓ.ም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በወረዳው ተገንብቶ ለኑሮና ለስራ ምቹ አካባቢ ተፈጥሮ ማየት፤
ተልዕኮ
የአካባቢ፣ ብዝሀ-ሕይወትና የደን ሃብት አያያዝ፣ ልማትና አጠቃቀም ለዛላቂ ልማትና ለድህነት ቅነሣ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ሥርዓትን የማዘጋጀትና ተፈፃሚነቱን የማረጋገጥ፣ ምርምርና የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ሽግግርን የማስተባበርና የማካሄድ፣ ትምህርትና ግንዛቤን የማስፋፋት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ትግበራን የማስተባበር፣ የተግባሪዎችን አቅም የመገንባት፣ የደን ኢንቨስትመንትንና ግብይትን የማስፋፋት፣ ሀገሪቷ የተፈራረመችባቸውን ዓለም አቀፍ የአካባቢ፣ የደንና የብዝሀ-ህይወት ስምምነቶችን መተግበር እና ወቅታዊ የአካባቢ እና የደን ልማትና አየር ንብረት ለውጥ ተግባራትን ማከናወን፤
ዓላማ
- በወረዳ ደረጃ እየመጣ ያለው ፈጣን እና ፍትሐዊ ልማት ዘላቂና አካባቢያዊ ደህንነትን ያረጋገጠ እንዲሆን ማስቻል፣
- በ2015 ሀገሪቱ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ በምታደርገው እንቅስቃሴ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ስልት ትግበራ በዞን ደረጃ የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ ማበርከት፤
- የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀምን በማሻሻል ከደን ሀብት የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ምህዳራዊ አስተዋጽኦ ማሳደግ፤
- የብዝሀ ሕይወት ሀብት የሚጠበቅበት፣ የሚለማበት፣ በአግባቡ ጥቅም ላይ የሚውልበትና ፍትሀዊ የጥቅም ተጋሪነት የሚኖርበት ሁኔታ ማመቻቸት፣
መግቢያ
ፕላን ኮሚሽን የክልሉን አሰፈፃሚ አከላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ በቁጥር 180/2012 የተቋቋመ መሆኑን ይታወቃል። የኮሚሽኑን መቋቋም ተከትሎ የሴክተሩ የቀጣይ አስር ዓመት ማለትም ከ 2015—2022 ዕቅድ አቅዶ ወደ ተግባር መግባት እንዳለበት ይታመናል። በመሆኑም ይህ የፕላን ኮሚሽን የቀጣይ አስር ዓመት መሪ የዕቅድ ሰነድ አምስት ክፍሎች ሲኖሩት ክፍል አንድ አጠቃላይ ሁኔታዎችን እና የወረዳዉን አጠቃላይ ገጽታ የሚዳስስ ሲሆን ክፍል ሁለት የ3 ዓመቱ ዋና ዋና ግቦችና የትኩረት መስክሲያካትት፤ክፍል ሶስት ግብና የአፈጻጸም ትንተናናበአፈጻጸም ወቅት ያገጠሙ ችግሮችና መፍትሄዎቹን ያካተተ ሲሆን አራተኛው ክፍል በአፈጻጸም ሰንጠረዥ (የየዓመቱ ዝርዝር አፈጻጸም) የተመላከተበት ሲሆን በመጨረሻም የቀጣይ ሰባት ዓመታት የትኩረት አቅጣጫ በሁሉም ዋናዋና የስራ ሂደቶች ከሚጣሉ ዋና ዋና ግቦች አሁን የደረስንበት አፈፃፀም መነሻ በማድረግ የቀጣይ ሰባት ዓመታት ዕቅድ ማቀድ ነው።
አጠቃላይ ሁኔታ
የእ/ወ/ፕ/ል/ ጽ/ቤት ባለፉት ዓመታት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሴክተር ውስጥ ሲቪል ሰርቪሱ ለመልካም አስተዳደር፣ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፤ ለልማት እና የለውጥ አጋዥ ኃይል ብሎም ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን በሁሉም የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መዋቅር በመተግበር ተቋማዊ ለውጥ እንዲያመጣና ሴክተሩ ዘመናዊ፤ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ እንዲፈጠርበርካታ ተግባራትንሲያከናውን ቆይቷል። እስካሁን ባለው የለውጥ ሂደት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን ማየት የተቻለ ቢሆንም ቀደም ሲል በተበጣጠሰ መልኩ ሲከናወኑ የነበሩ ተግባራት በቀጣይ በተደራጀ እና ሁሉ አቀፍ በሆነ መልኩ መከወን እንዲችል ራሱን አስችሎ በክልል ደረጃ እንዲሁም በወረዳናበከተማ አስ/ደረጃ በጽ/ቤት መቋቋምእንዳለበትክልሉ በአዋጅ ደንግጓል።በዚህም መሠረት ወደ ተግባር ለመግባት እንዲያስችል የቀጣይ ሰባት ዓመታት ዕቅድ ማቀድ ቅድሚያ የምሰጠው ተግባር ነው።
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834









