እኖር
ወረዳ
እኖር ወረዳ
እኖር ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙት ወረዳዎች አንዱ ሲሆን በ40 የገጠር ቀበሌዎች እና በ3 የገጠር ከተማ የተዋቀረ ነው፡፡ የእኖር ወረዳ ከሰሜን ከቸሃ ወረዳ ከምስራቅ ጌቶ ወረዳ ከደቡብ እኖር ኤነር መገር ወረዳ እንዲሁም በስተደቡብ የም ልዩ ዞን በምእራብ ኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል፡፡፡፡ ማህበረሰቡ በአብዛኛው የሚተዳደረው በእንስሳት እርባታና በእርሻ ነው፡፡
የወረዳው ዋና ከተማ ጉንችሬ ሲሆን ስያሜውን ያገኘው በከተማው ከሚገኘው የተጎመደ ጉንችር ከሚባል የዝግባ እንጨት እንደሆነ የታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ከተማው ከአዲስ አበባ በ185 ኪ.ሜ ከዞኑ ርእሰ ከተማ ከወልቂጤ ደግሞ በ42 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የወረዳው የአየር ንብረት ወይናደጋ 57.22% ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ(1500-2300ሜ)፣ቆላ 26.25% ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ(801-1500ሜ) እና 16.23% ደጋ ሲሆን ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ (2300-3400ሜ) እንደሚሆን ይገመታል፡፡
የወረዳው ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ
እኖር ወረዳ ከጉራጌ ዞን ርዕሰ ከተማ ወልቂጤ 42 ኪ/ሜ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር መቀመጫ ከሆነችው ሆሳዕና 135 ኪ.ሜ ከአጣጥ-ማዞሪያ እምድብር ሆሳና እና ከመዲናችን አዲሰ አበባ 197 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የእኖር ወረዳ ከሰሜን ከቸሃ ወረዳ ከምስራቅ ጌቶ ወረዳ ከደቡብ እኖር ኤነር ወረዳ እንዲሁም በስተደቡብ የም ልዩ ዞን በምእራብ ኦሮሚያ ክልል ያዋስኑታል፡፡
የወረዳው የቆዳ ስፋትና አስተዳደራዊ አወቃቀር
ከGIS በተገኘው መረጃ መሰረት የእኖር ወረዳ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 113,467 ሄ/ር እንደሆነ ይገመታል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለአመታዊ ሰብል 15767 ሄ/ር ፣በቋሚ ሰብል የተያዘ 57364ሄ/ር፣ ወደፊት ሊለማ የሚችል 10,882 ሄ/ር፣ ለግጦሽ መሬት 7500ሄ/ር፣ የተፈጥሮ ደን 1307ሄ/ር፣ በሰውሰራሽ ደን የተሸፈነ መሬት 7388ሄ/ር፣ የተጎዳ መሬት 1636ሄ/ር፣ በውሀ የተሸፈነ መሬት 2120ሄ/ር፣ በመኖሪያ ቤት ግቢ የተሸፈነ መሬት 5000ሄ/ር፣ በመንግስት ተቋማት የተያዘ መሬት 2139ሄ/ር፣ በሌሎች ልዩ ልዩ ይዞታዎች የተሸፈነ መሬት 2364ሄ/ር ነው፡፡ የወረዳው አወቃቀር በ40 የገጠር ቀበሌዎችና በ3 የከተማ ቀበሌዎች የተወቀረ ነው፡፡
የወረዳው ስም ስያሜ
የእነሞርና ኤነር ወረዳ ምክር ቤት ግንቦት 2 / 2014 ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር 8ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ጉባኤ ወረዳው ቀደም ብሎ እነሞርና ኤነር ተብሎ ሲጠራበት የነበረው ስያሜ በመቀየር <<እኖር>> ወረዳ በሚል ሰየመ ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው የእነሞርና ኤነር ወረዳ ይጠራበት የነበረውን ስያሜ በመቀየር እኖር ወረዳ በሚል አንዲሰየም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል ፡፡ ነባሩ የእነሞርና ኤነር ወረዳ በተሰጡ የህዝቡ የአደረጃጀት ጥያቄዎች ምላሽ ምክንያት በስሩ ሲተዳደሩ ከነበሩ አካባቢዎች ራሳቸውን ችለው በወረዳና ከተማ አስተዳደር የተደራጁ በመኖሩ ምክንያት በቀረው ወረዳ ስር ያሉ ህዝቦችን ሊገልጽና አንድ ሊያደርግ የሚችል ስያሜ መስጠት በማስፈለጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የቀድሞ እነሞርና ኤነር ወረዳ ስያሜውን በመያዝ 40 የገጠርና 3 የከተማ በድምሩ 43 ቀበሌዎች በስሩ ይዞ የዞኑ አንድ ወረዳ በመሆን ተግባራትን በመምራት ላይ ይገኝ ነበር ፡፡ የወረዳው አመሰራረትና ስያሜ በተመለከተ ከወረዳውና ከጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ወረዳውን ከዚህ ቀደም ሲያገለግሉ ከነበሩ አባቶች ጋር ውይይት መደረጉን የጠቆሙት አቶ ትዛዙ ወጥ የሆነ ትርጉም ባይኖረውም ወረዳው ከ1967 ዓ.ም በፊት << እኖር>> ተብሎ ሲጠራ እንደነበር ከተደረጉ ውይይቶች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታል ብለዋል፡፡ በሂደትም በ1967 ዓ.ም በወቅቱ የነበረው አመራር ከህዝቡ ጋር ውይይት ሳይደረግ እኖር የሚለውን ስያሜ በመቀየር እነሞርና ኤነር በሚል የተጠራ መሆኑን አባቶች እንደሚናገሩ በጥናቱ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ወረዳዎቹ በአዲስ ከመደራጀታቸው የተነሳ የወረዳዉን ጥቅም በማያሳጣና ህዝቦችን ሊወክልና ሊያስማማ የሚችል ስያሜ እንዲሰጥ ሀሳብ ማንሳታቸው በሰነዱ ተመላክቷል፡፡በዚህም መሰረት የወረዳው ስያሜ <<እኖር>> ሊባል እንደሚገባ ማመላከታቸውን ተብራርቷል፡፡ ወረዳውን በተመለከተ የተጻፉ መጽሃፍት/ጎጎት/ እንደሚያስረዱት እኖር በተወላጆችና በአጎራባች ወይም በተቀረው የጉራጌ ህ/ሰብ ዘንድ እኖር በሚል ስያሜ ሲጠራና በዚህ ስያሜ ሲታወቅ ቆይቶ የአጼ ሚኒሊክ ሃይል ጉራጌን ከተቆጣጠረ ወዲህ በነበሩ ሁኔታዎች አማካኝነት አማርኛ በእኖር ቋንቋ ጣልቃ በመግባት ባሳደረው ተፅዕኖ ምክንያት<< እኖር>> የሚለውን ስያሜ << እነሞር>> በሚለው እንዲለወጥ መደረጉን ያስረዳሉ፡፡ በተለይም ከስያሜ ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የአመለካከትና የግንዛቤ ጥያቄዎች በሚመለከት በመድረኩ በሰፊው ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያዕቆብ እንደተናገሩት በተደረጉ የአደረጃጀት ለውጦች ምክንያት ሚቄ ማእከል ያደረገው ወረዳ ስያሜውን << እኖር ኤነር>> በሚል ከተሰየመ በኅላ በሚኖሩ የተለያዩ ውይይቶችም ሆነ የስራ እንቅስቃሴዎች እኖር ኤነር እና እነሞር ኤነር በሚሉ ስሞች ምክንያት የሚቸገሩ አካላት በግልጽ መኖራቸውን አስረድተዋል ፡፡ አቶ ያዕቆብ አክለውም ምንም እንኳ ለዘመናት በወንድማማችነትና በአንድነት የዘለቁ ቢሆኑም <<እኖር>> እና <<ኤነር>> በተለያየ አካባቢ የሚኖሩና የኤነር አካባቢ ህዝቦች ሙሉ በሙሉ በአዲሱ እኖር ኤነር መገር ወረዳ ስር በመካለላቸው የወረዳው ስያሜ ማስተካከል እንደሚገባ ጥናቱ መነሻ በማድረግ አስገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም ከምክር ቤት አባላት መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት የስያሜ ለዉጥ መደረጉ ተገቢና ወቅቱን ያገናዘበ በመሆኑ የስም ለውጥ መደረጉ አስፈላጊ መሆኑ ጠቁመዋል ሲል የዘገበው የወረዳው የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው፡፡ የእነሞርና ኤነር ወረዳ ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ ዙር 8ኛ ዓመት 30ኛ መደበኛ ጉባኤ ወረዳው ቀደም ብሎ እነሞርና ኤነር ተብሎ ሲጠራበት የነበረው ስያሜ በመቀየር <<እኖር>> ወረዳ በሚል ሰየመ፡፡
የወረዳው መልክዓ ምድራዊ ገጽታ እና የአየር ፀባይ
የወረዳው መልካ ምድራዊ ገጽታ በአመዛኙ ሜዳማ ሲሆን የተቀረው ክፍል በተፈጥሮና ሰውሰራሽ ደን የተሸፈነ ተራራማና ገደላገደል ገጽ አለው፡፡ የወረዳው የአየር ንብረት ወይናደጋ 57.22% ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ(1500 – 2300ሜ)፣ ቆላ 26.25% ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ(801 – 1500ሜ)እና 16.23% ደጋ ሲሆን ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ(2300 – 3400ሜ)እንደሚሆን ይገመታል፡፡ የወረዳው አመታዊ የሙቀት መጠን ከፍተኛው 25°C ዝቅተኛው 13°C መሆኑን ይገመታል፡፡ አመታዊ የዝናብ መጠን ከፍተኛ 1400ሚ.ሜ ዝቅተኛ ደግሞ 801ሚ.ሜ ነው፡፡ በወረዳው ወንዞች ውስጥ ኑእሀራም፣ እንስሀራም፣ ጎጋረ፣ ዊንቐ፣ ናካም ወዘተ ሳይጠቀሱ ማይታለፉ የተፈጥሮ ፀጋዎቻችን ነቸው፡፡
የወረዳው ስነ-ህዝብ
የወረዳው የህዝብ መጠንና ዓመታዊ ዕድገት
የ1999ኙዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብና ቤቶች ቆጠራ መረጃ መሰረት በማድረግ እና የወረዳው ርዕሰ ከተማ አካል ሆነው የተካተቱ ቀበሌዎችና መንደሮችን በመለየት በ2015 ዓ.ም የእኖር ወረዳ ህዝብ ብዛት 170,631 ሲሆን ከዚህ ዉስጥ (48.73%) ወንድ እና (51.27%) የሚሆኑት ሴቶች ናቸዉ፡፡ ከጠቅላላዉ ህዝብ 93.91%የሚኖረዉ በገጠር ክፍል ሲሆን የከተማ ህዝብ ድርሻ 6.09%መሆኑ መረጃው ያመላክታል፡፡ የወረዳዉ ህዝብ አሰፋፈር በቀበሌያዊ ገፅታ ሲታይ በ40 የገጠር ቀበሌዎች እና በ3 የገጠር ከተማ እንደሚኖር መረጃው ያሳያል፡፡እንደ 1999ኙ ህዝብና ቤቶች ቆጠራ ስታትስቲክስ መሰረት ክልላዊ እስታንዳርድ በመጠቀም የወረዳዉ ህዝብ በ1999 ዓ.ም ከነበረበት በየዓመቱ በአማካኝ 2.8 በመቶ (የገጠር ህዝብ የእድገት ምጣኔ) እያደገ በመሄድ በ2015 ዓ.ም 170,631 እንደሚደርስ ይገመታል፡፡በሌላ በኩል ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ልማት እድገት ከህዝብ ቁጥር አንፃር ሲታይ አዝጋሚ መሆኑ ለፈጣን ህዝብ ቁጥር እድገት አሉታዊ ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ በሰፊዉ ይታመናል፡፡
የወረዳው የህዝብ ስብጥር በዕድሜ
ህዝብ በዕድሜ መቀናብር የሶሺዮ-ኢኮኖሚያዊ ትርጉም በሚሰጥ መልኩ በሁለት ዓይነት ይታያል፡፡ ይህም ጥገኛ(እድሜያቸዉ 14 ዓመት እና በታች ያሉ ለስራ ያልደረሱ ታዳጊ ህፃናት 66,048 እና ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸዉ ደግሞ አረጋዊያን 10,753 እና ጥገኛ ያልሆኑ እድሜያቸዉ ከ15-64 ዓመት የሆኑ በሥራ እድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶችና ጎልማሶች ደግሞ 93,830 ይሆናሉ ተብሎ ይታመናል፡፡በስራ ዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሰዎች የሚበዙበት ማህበረሰብ የማምረት፣ገቢ የማግኘትና የመዋዕለ-ንዋይ የማፍሰስ አቅም ከፍተኛ ሲሆን ህፃናትና ሽማግሌዎች የሚበዙበት (ጥገኛ) ህዝብ በፍጆታ ወይም ቀለብ እንጂ በምርት ላይ አስተዋፅዖው አነስተኛ በመሆኑ ኑሮዉ ደካማ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት የወረዳዉ ህዝብ ስብጥር ሲታይ በ2015 ዓ.ም ጥገኛ ከሆኑት መካከል እድሚያቸዉ ከ14 ዓመት በታች የሆኑ የወረዳዉ ህፃናትና ልጆች 38.70% ከ65 እና በላይ የሆኑ አረጋዊያን 6.31% በድምሩ 45.01%ሲሆን በምርታማ ስራ ላይ ሊሰማራ የሚችል (ጥገኛ ያልሆነ) ህዝብ ከ15-64 ዓመት 54.99% እንደሆነ ይገመታል፡፡
የእኖር ወረዳ ህዝብ ብዛት በፆታና በቀበሌ 2015ዓ/ም
የቀበሌውስም ወንድ ሴት ድምር
ጎንቸቤቴ 2279 2793 5072
ገረንቦ 1823 1353 3176
ጎንደሬጨ 1829 1629 3458
አጫወደ 1987 1957 3944
ሻፋሞ 2059 1967 4026
ወርቃት 2266 1988 4254
ኢባራኝ 1664 1665 3329
ተርሆኘ 2037 1694 3731
ጠረደ 2298 2220 4518
ሆ/ዚዞ 1743 1667 3410
ጃቱ 2206 2191 4397
ጎምሸ 2155 2128 4283
ደንበር 1626 1609 3235
ካሳይ 2268 2425 4693
ዳዓምር 1283 1225 2508
ኧገበኝ 2103 2100 4203
እናንገራ 1651 1708 3359
አንዳሆረ 1411 1497 2908
ሻንቃ 1815 1840 3655
ከረቤድ 2020 2256 4276
አጋሬ 1864 1882 3746
ጋርዳሼ 2797 2704 5501
ኧሰኸር 2127 2149 4276
ማቃና 2400 2449 4849
ሁረድ 1231 1345 2576
ጋሣውዴ 1182 1558 2740
ኮሰድ 1832 1912 3744
አሞገራ 2164 2828 4942
ጋሀራድ 2369 2451 4820
ወንጬ 1705 1680 3385
ሰንዲቃይ 1963 1864 3827
ጓንታና 1758 1695 3453
ጡማነ 1889 1794 3683
ወሸዘውያር 2080 2471 4551
አቡጋዴ 2191 2706 4897
ኩነበር 1350 1813 3163
አዋስር 1649 2224 3873
ኧገዜ 1291 1628 2919
ካናስ 2801 3531 6332
አጋታ 2825 3641 6466
ኧገዜከተማ 1261 1075 2336
ጋዛንቸከተማ 1089 1373 2462
ጉስባጃይ 2803 2802 5605
ድምር 83,144 87,487 170,63
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834



