የእኖር ወረዳ ሴ/ህ/ጉ  ጽ/ቤት ሀላፊ

 ወ/ሮ ፋንቱ ደምስ

 

መግቢያ

የሴቶችና ህጻናት ተቋም አመሰራረት ፤-

ቀደም ባሉት ዘመናት እስከ 1995ዓ.ም ድረስ በግብርና ሚኒሰቴር በግብርና ልማት ጽ/ቤት ስር ቀድሞ ኑሮ ዘዴ ከጊዜ በኋላ በግብርና ኤክስቴንሽን ቡድን ስር በገጠር ሴቶች ጉዳይ በሚሉ ስያሜዎች የሚጠራ የስራ ሂደት ስር፤

  1. በቤተሰብ ጤና እንክብካቤ
  2. በገቢ ምንጭ ማስገኛዎች (ቁጠባና ብድር በጓሮ አትክልት ልማት)
  3. በቤተስብ መምሪያ በቤሰብ ምጣኔ ስራዎች
  4. በበሴቶች መብትና አጠባበቅ እና በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን
  5. በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና ስርጭት
  6. በምግብን ስርአተ ምግብ ዋና ዋና ስራዎች
  7. በሴቶች የዉሳኔ ሰጪነት ሚና ለሴቶች ግንዛቤ በመፍጠር ስልጠና በመስጠት የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት እንዲተቀሙ አመጋገባቸዉን አሻሽለዉ መብታቸዉን የተከበረ በኢኮኖሚ ከወንዶች እኩል እንዲሆኑ የሰራ ነበር፡፡

በተጨማሪ ለብቻቸዉ የሴቶች ማህበር ቀድሞ ከደርግ ጀምሮ እስካሁንም እንዳለዉ በሚሰራዉ አላማና ግብ እንዳለ ሆኖ ከላይ ከተጠቀሱት 1995 ዓ.ም ጀምሮ በግብርና መ/ቤት ስር ባለዉ አንድ ቡድን (የስራ ሂደት)የገጠርዋን ሴት ሁለንተናዊ ችግር ለመፍታትና ለልማት ቀጥታ ተሳታፊ በማድረግ የሴቶችን አደረጃጀት ለማሻሻል ከላይ በሚኒስቴር ደረጃ ጀምሮ እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ ወርዶ ስራዉን የሚሰራና የሴቶች ከፍታ የሚጨምር መስሪያ ቤት ተደራጀ፡፡

  1. የሴቶችና ህጻናት ክብካቤ
  2. የቤተሰብ መምሪያ የቤተሰብ ምጣኔ ስራ
  3. ምግብና ስርአተ ምግብን ጨምሮ የጤና ስራ በጤና ጥበቃ መ/ቤት ተደራጅቶ የጤና ኤክስቴንሽን ስራ መዋቅር ተዘረጋ

-በሴቶች መብት አጠቃቀም

-በገቢ ምንጭ ማስገኛ ዘዴዎች (ቁጠባና ብድር፤በጓሮ አትክልት ልማት በግብርና ስራዎች የኢኮኖሚ አቅም ግንባታዎች ላይ ይሰራ እንደነበረ)

-የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ስርጭት ተመሳሳይ ስራዎች (በሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ) ስር እንዲደራጅ ተደረገ፡፡

-በሴቶች ዉሳኔ ሰጪነት ሚና ከዚያ የህጻናት መብት ጥበቃ ተካቶ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ በሚል ተደራጅቶ እየሰራ ነዉ፡፡

በአሁን ጊዜ ሴቶችና ህፃናት ሴክተር ከተቋቋመባቸው ዓላማዎች ዋና ዋናዎቹ የሴቶችና የህፃናት መብትና ጥቅሞችን በማስከበር የሴቶች ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን በማጎልበት ዙሪያ ግንዛቤና ንቅናቄ እንዲፈጠር ማድረግ፣

በእ/ወ/ያሉ ተጋላጭ ህፃናት  መረጃ

  • በወረዳችን ውስጥ ያሉ ተጋለጭ ህፃናት ብዛት 1180 ሲሆን ወ 558 ሴ 622 ድ 1180 ተጋላጭ ህፃናቶች ይገኛሉ፡፡
  • በወረዳችን ውስጥ ያሉን አጋር ድርጅቶች ፡-
  • ቅድሚያ ማህበር
  • ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ
  • ኮምፓሽን
  • ወህምያ
  • ተስፋ ድርጅት
  • FSRP(የስርአቴ-ምግብ ማሻሻያ ፕሮግራም)
  • CALM

ከላይ የተዘረዘሩት አጋር ድርጅቶች ሲሆኑ የሰሯቸውና እየሰሯቸው ያሉ ተግባራቶችም ፡-

  • በህፃናት ዘርፍ ፡-የት/ት ቁሳቁስ ድጋፍ፡የአልባሳትና የምግብ ድጋፍ ፡ የህክምና ድጋፍ፡ለማህበረሰቡ በህፃናት ጎጅ ልማዳዊ ድርጊት ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ፡ተጥለው የተገኙ ጫቅላ ህፃናትን አንስቶ ማሳደግና ለጉዲፍቻ መስጠት(በቅድሚያ ማህበር)
  • በሴቶች ዘርፍ፡-ኢኮኖሚካሊ እራሳቸውን ለማስቻል ሴቶችን በማደራጀት የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በንግድ ስራ ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፤
  • ሴቶች በግብርና ስራ ላይ ተደራጅተው እየሰሩ ላሉ ሴቶችን በግባአት የማገዝ ስራ መስራት ተችሏል፡፡ እንዲሁም በእርባታ ስራ ላይ በንብ ማነብ ስራ ላይ እንዲሰሩ የቁሳቁስ ድጋፍ(ዘመናዊ ቀፎ) መስጠት ተችሏል፡፡
  • ከዚህ በፊት በወረዳችን ዉስጥ የነበሩ የሴቶች አደረጃጀት በተመለከተ የልማት ቡድኖች ብዛት 516 የ1ለ5 አደረጃጀት ብዛት 2687 የአባላት ብዛት 15523 ሲሆን በ2016 በጀት ዓመት የሴቶች አደረጃጀቶች በማሻሻል ወደ ልማት ህብረት ተቀይሮ በሁሉም ቀበሌዎች ንቅናቄ ተፈጥሮ 748 ልማት ህብረት 2226 የ1ለ10 ትስስር እና 21950 አባላት የማደራጀት ስራ በመስራት እናዚህ የሴቶች አደረጃጀቶች በተለያዮ ተግባራት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በወረዳ ደረጃ ከሴክተር መ/ቤቶች የተዋቀሩ የሴቶች ልማት ህብረት ቴክኒ ኮሚቴና ስትሪንግ ኮሚቴዎች እና በቀበሌ ደረጃ የቀበሌዎች የሴቶች ልማት ህብረት ስትሪንግ ኮሚቴዎች የማቋቋም ስራ ተሰርቷል፡፡
  • በወረዳችን ሊጠፉ ያልቻሉ የሴቶችና ህጻናት ጥቃት፤-አስገድዶ መድፈር፤የሴት ልጅ ግርዛት፤የህጻናት ድብደባ እና ህገወጥ ዝዉዉር የሚከሰትባቸዉን ምክንያ ለሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርስባቸዉ ጥቃት አስከፊነት ወላጆች በተጋጋሚ ግንዛቤ ቢፈጠርላቸዉም ችላ የማለት ነገር መኖር በማስረጃ እጦት ምክንያት ጥቃት አድራሾች ላይ አስተማሪ የሆነ የህግ ቅጣት አለመቀጣታቸዉ፡፡

የሴክተሩ  ራዕይ፣ተልእኮና እሴቶች

 ራዕይ

“በ2022 ሴቶች በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና በባህል መስኮች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባት፣የህፃናት መብትና ደህንነት የተከበረባት፤ የህፃናት መልካም ስብዕና የጎለበተባት እና የስርአተ- ጾታ እኩልነት የሰፈነባት ወረዳ ማየት”፡፡

 

የሴክተሩ ተልዕኮ

የሴቶችን በልማት፣በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፤ የህፃናትን መብትና ደህንነት ማስጠበቅና የፆታ ዕኩልነትን ማስፈን፡፡

እሴት 

  • አሳታፊነትና ፍትሃዊነት፣
  • ግልጽነትና ተጠያቂነት፣
  • ፈጠራ፣
  • ቅልጥፍናና ውጤታማነት፣
  • የአገልግሎት ጥራት፣
  • የቡድን ስራ፣

              እሴት

  • ስራዎችን የጋራ አመለካክትን ከመፍጠር ይጀምራሉ;
  • በእቅድ እንመራለን;
  • ፍትሀዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነዉ
  • ጊዜ እና የሰዉ ሀይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶች ናቸዉ
  • ክራይ ሰብሳቢነት እንፀየፋለን
  • መረጃን ለልማት እናዉላለን
  • ወጤት ያሸልማል
  • ተገልጋዮቻችን የህልዉናችን መሰረት ናቸዉ
  • ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸዉ
  • የሴቶች የወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ እናረጋግጣለን;;