የእ/ወ/ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሀላፊ

ወ/ሮ ሙሉ ሻፊ

መግቢያ

      ኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለአንድ ሀገር ልማት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን እሙን ነው፡፡ በተለይም በዘመኑ ግሎባላይዜሽን ሀገሮች እንዲሁም ህብረተሰቡ በአለም የተከናወነ ያለውን እንቅስቃሴ በደቂቃዎች መረጃ እንዲያገኝ ከማስቻሉም በላይ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ  መሳሪያዎች በመታገዝ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለገበያ መረጃ እና ሌሎችም የመረጃ ምንጭ አገልግሎት ይጠቀሙበታል፡፡ በሀገራችን ተጨበጭ ሁኔታ ስንመጣ መንግስት የተለያዩ የአይሲቲ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ዘርግቷል፡፡ ለመጥቀስ ያህል እስኩል ኔት፣ ወረዳ ኔት፣ አግሚስ፣ ኢስሚስ፣ ሄልዝኔት እና የመሳሰሉት በመዘርጋትና የሀገራችን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻል ህብረተሰቡ ግልጽ እና ፈጣን አገልግሎት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን የሰፈነበት ስርዓት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡በተለይም የሀገራችን 85% የሚሸፍነው የገጠር ማህበረሰብ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆኖ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የግብርና ስራን እንዲያከናውንና ገበያ መር የሆኑ ምርቶችን ለማምረት ራሱንና ሀገሩን ሊጠቅም የሚቻልበት ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ይህን ከላይ የተገለጸውን ሀሳብ መነሻ ባደረገና ይህም በደገፈ መልኩ የወረዳችን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የተቋቋመ ሲሆን ዋነኛ አላማው ወረዳው በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሚሰጠውን ድጋፍ ማሳደግ ነው፡፡ በመሆኑም ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን አስተዋጽኦ በማጎልበት ወረዳችን የፈጣን ልማትና እድገት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ በዚህኛው አመት በተቋሙ አቅም ዌብሳይት አበልጽጎ የወረዳው ማህበረሰብ እንዲገለገልበት ክፍት ማድረግ ችለናል፡፡ በመሆኑም ጽ/ቤቱ እስከ ቀበሌ ባሉ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚሰጠውን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈና የተደራጀ እንዲሆን አገልግሎት አሰጣጡ ዘመናዊ ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ እንዲሁም በየትኛውም የአለም ደረጃ ሆኖ ስለእኖር መረጃ ለፈለገ በሙሉጎግል ላይ ገብቶ እኖር ወረዳ ዌብሳይት ብሎ ቢፈልግ ስለየትኛውም ጉዳይ መሬት ነክ፣ አስተዳደር፣ ትምህርት፣ ጤና፣ግብርናና፣ ሌሎችም ጉዳዮች ወደ ወረዳው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ በዌብሳይት ማግኘትና የትኛውም ተቋም አስመልክቶ ቅሬታ ጭምር ካለ እዛው ላይ ማስፈር የሚቻልበት ሁኔታ በዚሁ ዌብሳይት ማስቀመጣችን ቴክኖሎጂያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደግንና ከዘመኑ ጋር አንድ እርምጃ ወደ ፊት መጓዛችን የሚያሳይ ሲሆን ይህንን ደረጃ ለማድረስ መሪ ሚና የተጫወተው የወረዳው ሳ/ኢ/ቴ ጽ/ቤት የሶፍትዌርና ድረገጽ ልማት ስራ ሂደት የተለየ ምስጋናዬ እያቀረብኩ ከዚህ ባለፈ መረጃ ሂወት ነውና ሁሉንም የወረዳችን ተቋማቶች ተገቢውን መረጃ እንድትመግቡ እያልኩ አበቃሁ፡፡   

በመጨረሻም አሁን በሀገራችን ከመጣው ለውጥ ጋር ተያይዞ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሆነው እንዲደራጁ በተቀመጠዉ አገራዊ አቅጣጫ መሰረት ከጥር 2013 ዓ.ም ጀምሮ የእ/ወ/ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በሚል የሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ነክ ኃላፊነቶች ተግባራቶች በበላይነት በመቀበል በጽ/ቤት እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

      ስለሆነም ዘርፉ አሁን ወቅቱ የሚፈልገው ትኩረት የሚሰጠውና ከሁሉም ተቋማት የሚያገናኝ በመሆኑ እራሱን ችሎ መውጣቱ የተሻለ ተግባር ለመፈጸምና በተሸለ ፍጥነትና ጥራት ለመላው ማህበረሰባችን አገልግሎት በመስጠት ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

      በመሆኑም ጽ/ቤቱ ከወረዳው እስከ ቀበሌ ባሉ መንግስታዊ ተቋማት ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈና የተደራጀ እንዲሆንና አገልግሎት አሰጣጡ ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የሃብት ብክነትን መቀነስ ነው፡፡

      በተጨማሪም በህብረተሰቡ ውስጥ ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና በማስፋፋት ህብረተሰባችን የግብርና፣ የገበያ፣ የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች መረጃዎችን በአቅራቢያው እንዲያገኙ በማድረግ በገጠርና በከተማው ህብረተሰብ መካከል ያለውን የዘመናዊ መረጃ ክፍተት ማጥበብ ነው፡፡

መግቢያ

ወረዳው በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ ለውጥ ውጤታማ፣ ዘላቂና ተቋማዊ ለማድረግ እንዲሁም ከደረስንበት የዕድገት ደረጃ አንጻር የሚኖረውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያስችል የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ፈትሾ ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ ታምኖበት ቀደም ሲል በእ/ኤ/ወ/አስተዳደር አይሲቲ ዋና ስ/ሂደት የነበረው እራሱን ችሎ እንደ ተቋም እንዲወጣ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ዘርፉ እስከ 2013 ዓ.ም በወረዳችን በአስተዳደር ጽ/ቤት ስር የአይሲቲ ዋና ስራ ሂደት ሆኖ ሲሰራበት ቆይቷል፡፡ በመሆኑም በወረዳችን ባለፉት አመታት ስ/ሂደቱ በአንድ አስተባባሪና ሁለት ፈጻሚዎች በሰው ኀይል ተደራጅቶ ባለው ውስን ግብዓቶች በወረዳችን በተለያዩ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ የማስተዋወቅ እና የመጠገን ስራ ሲሰራ ቆይተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዢ ሲፈጸም እስፔስፊኬሽን የማዘጋጀት፣ ጥራት ማረጋገጥ፣ በት/ቤቶች የኢኮቴ መርሀ ግብር እንዲተገበርና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ በማቋቋም የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች እንዲሰሩ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በተለይም በት/ቤቶች እስኩል ኔት እንዲሁም የወረዳ ኔት አገልግሎት እንዲኖር በተደረገ ስራ 2 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የVSAT የኢንተርኔት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በአጠቃላይ የኢኮቴ መርሀ ግብር የተመለከቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የማስተዋወቅ፣ የማላመድና የማልማት ስራ ባለው አቅም ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በመጨረሻም አሁን በሀገራችን ከመጣው ለውጥ ጋር ተያይዞ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ሆነው እንዲደራጁ በተቀመጠዉ አገራዊ አቅጣጫ መሰረት ከጥር 2013 ዓ.ም ጀምሮ የእ/ወ/ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በሚል የሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ነክ ኃላፊነቶች ተግባራቶች በበላይነት በመቀበል በጽ/ቤት እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡

      ስለሆነም ዘርፉ አሁን ወቅቱ የሚፈልገው ትኩረት የሚሰጠውና ከሁሉም ተቋማት የሚያገናኝ በመሆኑ እራሱን ችሎ መውጣቱ የተሻለ ተግባር ለመፈጸምና በተሸለ ፍጥነትና ጥራት ለመላው ማህበረሰባችን አገልግሎት በመስጠት ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

      በመሆኑም ጽ/ቤቱ ከወረዳው እስከ ቀበሌ ባሉ መንግስታዊ ተቋማት ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈና የተደራጀ እንዲሆንና አገልግሎት አሰጣጡ ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የሃብት ብክነትን መቀነስ ነው፡፡

      በተጨማሪም በህብረተሰቡ ውስጥ ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂን በመዘርጋትና በማስፋፋት ህብረተሰባችን የግብርና፣ የገበያ፣ የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች መረጃዎችን በአቅራቢያው እንዲያገኙ በማድረግ በገጠርና በከተማው ህብረተሰብ መካከል ያለውን የዘመናዊ መረጃ ክፍተት ማጥበብ ነው፡፡

በተጓዳኝም ጽ/ቤቱ ፈጣን እድገት ለማረጋገጥ የግሉ ዘርፍ ቴክኖሎጂውን ለማስፋፋት የሚጫወተውን ሚና ግምት ውስጥ በማስገባት በሂደት የሚጎለብትበትንና የሚስፋፋበትን መንገድ ማጠናከር ነው፡፡

ከኔትወርክ ተደራሽነት አንጻር፡- በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ተቋማት አንጻር 4 ተቋማት እስታንዳርዱን የጠበቀ ዝርጋታ በማከናወን የፋይበር ኔትወርክ የሚጠቀሙ ሲሆን ሌሎች 8ጸቋማት እስታንዳርዱን የጠበቀም ባይሆን የፋይበር ጠጠቃሚ ሲሆኑ 3 የግል ተቋማት ደግሞ የብሮድባንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ናቸው፡፡

በወረዳው ውስጥ 7 የወረዳ ኔቶች ያሉ ሲሆን ሄልዝኔት በአገር አቀፍ ደረጃ የተቋረጠበት አግባብ ሲኖር ሌሎቹ ለመጠቀም የወረዳ ኔታ መስመራችን 10.194.1.2

እስኩል ኔት የሚጠቀሙ ት/ቤት መረጃ በተመለከተ የተቋረጠበት አግባብ ያለ ሲሆን በ5ቱም ት/ቤት ላይ ቁሳቁሶች የነበሩ ሲሆን መረጃው እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ ክላውድ ኔት ላይ በማውረድ ይጠቀሙ ነበር::

የተቋሙ ስልክ ቁጥር

01133320288