የእኖር ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ

 አቶ አብደላ በደዊ ያሲን

                     

መግቢያ

የሚሊሻ ጽ/ቤት ቀደም ባሉት ግዜያት የዘረፍ አደረጃጃት፣የጽ/ቤት አደረጃጀትና የስራ ሂደት መዋቅራዊ አደረጃጀቶች ውስጥ በማለፍ የአካባቢ ፀጥታ ጥበቃ ተልዕኮውን በመወጣት የቆየ ሲሆን የደቡብብሔሮች፣ብሔረሰቦች፣ሕዝቦች ክልል መንግሥት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅቁጥር 161/2008 አንቀጽ 31 በተሠጠው ስልጣን የሚሊሻ ኃ/መ/ማ/ማ/ማ ዋና ስራ ሂደትን በደንብ ቁጥር 143/2008 ዓ.ም በአዲስ መልኩ በጽ/ቤት ደረጃ እንዲቋቋም ተወስኗል፡፡ 

ጽ/ቤቱ በ2008 ዓ.ም በደንብ ሲቋቋም ሁለት ዋና ስራ ሂደቶች እንዲሁም 3 ደጋፊ ስራ ሂደቶች የያዘ ሲሆን ይኸውም የምልመላ፣ ስልጠንና አደረጃጀት የስራ ሂደት እና የስምሪት፣አስተዳደር ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ስራ ሂደት ናቸው፡፡

የሚሊሻ የጽ/ቤት ዋናው ተልዕኮ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚሊሻ አባላት መልምሎ በማሰልጠን ያሰማራል፣ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውን ይከታተላል ይቆጣጠራል፣የተፈጥሮና ሰውሰራሽ አደጋ በተከሰተ ወቅት በአካባቢው ፈጥኖ በመድረስ ከሚመለከተው አካላት ጋር በመሆን የህይወት ማዳንና የንብረት ጥበቃ ያደርጋል፣ የሚሊሽ ኃይልን አቅም በመገንባት የህብረተሰቡን ሰላም ፀጥታና ደህንነት እንዲጠበቅ ያደርጋል፣የቀበሌ ሚሊሻን ለፀጥታ ጥበቃ ማስከበር በሚያስችል አኳኋን ያደራጃል እንደአስፈላጊነቱ ከህዝቡና ከሌሎች የፀጥታኃይሎች ጋር በቅንጅት ይሰራል፣ሚሊሻው ለረጅም ጊዜ ከምርት ሥራው ሳይነጠል ከህረተሰቡ ጋር በመሆን በፀጥታና በወንጀል መከላከል እና ሌሎች መሰል ሥራዎች ላይ እንዲሰማራ ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፣የክተት አዋጅ በሚታወጅበት ጊዜ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጐን የሚሰለፉ የሚሊሻ አባላትን ስልጠና በመስጠት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፡፡

የሚሊሻ ጽ/ቤት ስር የምልመላና ስልጠና አቅም ግንባታና ስምሪት ሎጂስቲክ የስራ ሂደቶች በአዋጅና በደንብ የተሰጣቸውን ተግባርና ተልዕኮ የሚሊሻ ሀይልን በህብረተሰብ ሙሉ ተሳትፎ በመልመል የተለያዩ አቅም ግንባታ በቀበሌ፣ወረዳ እንዲሁም በዞን ደረጃ በሚዘጋጅ መድረክ መስጠት፣ለአካባቢ ፀጥታ ጥበቃ በማሰማራት የህብረተሰቡን ደህንነት መጠበቅና በመንግስት የተቀረፁ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን፣ ህገ-መንግሥቱን መሠረት አድርገው የወጡ ሕጎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በመፈጸምና በማስፈጸም እንዲሁም የተጠናከረ የአካባቢ ፀጥታ መረጃ የማሰባሰብ ስራና ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ተደራሽ በማድረግ ስራ ላይ በማዋል ህብረተሰቡ የሚጠቀምባቸውን ባህላዊ የመቻቻል፣ መከባበርና አብሮነት እሴቶችን በመገንባት፣የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችና ፀጥታን በማስከበር ላይ ይገኛል፡፡

ከላይ በተገለጸው አሰራር መሰረት በወረዳችን የሚሊሻ ጽ/ቤት የተገልጋዬችን ፍላጐት ለማሟላት በሚያስችል መልኩ በ43ቱም ቀበሌ 984 የሚሊሻ ኃይል በጥራትና በብቃት በህብረተሰቡ ተሣትፎ በመመልመል አሰልጥኖ በማደራጀትና በማስማራት በወረዳችን ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ብጥብጥ ወንጀልና ስርዓተ- አልበኝነት ተወግዶ ዜጐች በህገ-መንግቱ የተረጋገጠላቸው ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠቀሙና በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ማድረግ የተቀመጠላቸው ተቀዳሚ ዓላማና ተግባር ሲሆን ይህንኑ ዓላማ እውን ለማድረግና ከዳር ለማድረስ የድርሻውን ሚና እየተወጣ ይገኛል፡፡ የቀበሌ የሚሊሻ ኃይሉ በወረዳው የህግ የበላይነትና ሰላምና ፀጥታን አንዲረጋገጥና የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ተጠናክሮ አንዲቀጥል እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ባለበት ቀበሌ ከባለድርሻ ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ እየተደረገ ይገኛል፡፡

 

 

በተጨማሪ የእኖር ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት በ2008 መጀመሪያ ከስራ ሂደት ወደ ጽ/ቤተ አድጎ ከመጣ ጅምሮ በወረዳው ዘላቂ ሠላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ በህዝብና በመንግስት  የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት በሚደረገው እንቅስቃሴ በየደረጃው የሚሊሻ አደረጃጅቶችን በማቋቋምና በማጠናከር በርካታ ተግባራትን  በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም በወረዳው መንግስት የተጀመረውን  የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የወረዳው ህዝብ በሙሉ አቅሙ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተገልጋዩ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ከመንግስት የሚሰጠው አገልግሎት ውጤታማ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ እንዲሆንለት ህዝቡን/ተገልጋዩን/ የእቅዱ አካል/ባለቤት በማድረግ አቅዶ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ጽ/ቤቱ የወረዳውን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሥራ ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ተገልጋይ ተኮር ለማድረግ በመሠረታዊ ሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት መሰረት ዕቅዱ የተሟላ ሆኖ እንዲተገበር በመንግስት በድርጅትና በህዝብ ክንፉ የተለያዩ አደረጃጅቶችን በማቋቋምና በታቀደው እቅድ መሰረት ድጋፍና ክትትል በማድረግ ተግባሩ በተያዘለት የጊዜ ገደብ/እስታንዳርድ/ ከጊዜ፣ከመጠንና ከጥራት እንዲሁም ከበጀት አንፃር ውጤታማ እንዲሆን በአሰራርና መመሪያው መሰረት ሁሉም አደረጃጀት በባለቤትነት ተግባሩን እየተፈጸመ ይገኛል ::

 

 

 

 የሚሊሻ ጽ/ቤት ባለድርሻ አካላት በተመለከተ፡-

  • የወረዳ አስተዳር እና በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላት፤
  • በየደረጃው የሚገኙ የህዝብ ምክር ቤትና የመስተዳደር ምክር ቤቶች፤
  • የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ፤
  • የፖሊስ ጽ/ቤት
  • የወረዳ ሚዲያ ተቋማት፤
  • የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት፤
  • የህዝብ ክንፎች፤
  • መከላከያ ላይዘን ፅ/ቤት፤
  • ገቢዎች ባለስልጣን፤
  • ፍትህ ጽ/ቤትና
  • ፍርድ ቤት ናቸው

 

 

ተልዕኮ:-

በህብረተሰቡ ተሳትፎ ብቃት ያለው የሚሊሻ ኃይል በመመልመል፣ በማሰልጠን፣ በማደራጀት፣ በማሰማራት፣ በማጥራትና ሎጅስቲክስ በማቅረብና የሚሊሻ ኃይል በማፍራትና ተደራሽነቱን በማረጋገጥ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን መከላከል፣ የአካባቢ ፀጥታን ማስከበርና የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት መጠበቅ፤

ራዕይ:-                               

 የህግ የበላይነት የተከበረበት፣ የአካባቢና የህብረተሰቡ ፀጥታና ሠላም የተረጋገጠበት ወረዳ ተፈጥሮ ማየት፤

ዕሴት:-

 ዕሴቶች የሴክተሩ ሠራተኞችና የሥራ አመራሩ የሚመሩባቸውና ወደፊትም በጋራ ሊከተሏቸው የሚገቡ የግልና የተቋም የአሰራር ፍልስፍናዎች ሲሆኑ ሴክተሩ፡-

  • ለህገ-መንግሥቱ ታማኝ መሆን፤
  • የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማረጋገጥ፤
  • ሰሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፤
  • የሕዝብ አገልጋይነት፤
  • ብዝኃነት መቀበልና ማክበር፤
  • ፍትሃዊነትና ሰብአዊነትን መላበስ፤
  • ራስን ማብቃት፣ አዳዲስ አሠራሮችን ማወቅና መጠቀም፤
  • ሙያዊ ሥነ-ምግባር መላበስ፤
  • ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ትኩረት መስጠት እና
  • ኃላፊነትን በተገቢው መወጣት ናቸው፡፡

                         

ዓላማ

 

  የጽ/ቤቱ ስትራቴጂያዊ መሠረቶችንና የትኩረት መስኮችን አንጥሮ መለየትና በቀጣይም በየደረጃው የሚገኙ የሚሊሻ አደረጃጀት በማጠናከርበስነ ምግባርና በስልጠና የዳበረ በቂ የሰው ሀይል በማፍራትየወረዳችን ህዝብ የልማትና እድገት በማስቀጠል የተሸለና ምቹና ሰላማዊ አካባቢ መፍጠር ነው::