የእኖር ወረዳ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ
አቶ አማረ ዘርጋ
መግቢያ
የልማትና ዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን በማፋጠን ከድህነትና ኋላቀርነት ለመላቀቅ፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የዜጎችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ዕቅድ ማዘጋጀትና ዕቅዱን መሠረት አድርጎ በመምራት ተግባራዊ በማድረግ ያለ ሲሆን
የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የወረዳው ህዝቦች የሰላም እሴቶችን በመገንባት፣ በወረዳው በተለያዩ መንስኤዎች ግጭቶች ተከስተዉ በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ሳያደርሱ አስቀድሞ የመከላከልና የተከሰቱትንም በሰላማዊ መንገድ የመፍታት፣ በሀገሪቱም ሆነ በዞኑ ሕገ-መንግስት የተደነገጉ የሃይማኖት ነፃነትና እኩልነት መርሆዎች በሃይማኖት አክራሪነትና ጽንፈኝነት አመለካከትና ድርጊቶች እንዳይሸራረፉ የመከላከልና በወዳው የህግ የበላይነትና ሰላምና ፀጥታ እንዲረጋገጥ እና የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታዉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
የእኖር ወረዳ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት በስሩ ከሚገኙ ተጠሪ ተቋማት ማለትም ፖሊስ እና ሚሊሻ ጽ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራትን ትኩረት ያደረገ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡-
- በአካባቢው ሰላምና ደህንነት
- በአካባቢው የሰላም እሴት ግንባታ ሽፋን ማሳደግ
- በግጭት መከላከልና መፍታት
- የጸጥታ ስጋት አመላካች መረጃ አሰባሰብ አሰተዳደርና በግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን በየደረጃው ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥባቸው የማድረግ አገልግሎት
- የሃይማኖትና እምነት መቻቻልና መከባበር እሴት ግንባታሽፋንን የማሳደግ ተግባር
- የዜጎችፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ተደራሽነትን የማሳደግ
- በማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል እና የኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ተግባራትን በማጠናከር ህገ- ወጥነትን መከላከል
- ማህበረሰቡ በተደራጀ መንገድ የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እንዲችል ከህብረተሰቡ የተውጣጣ የሚሊሻ አባላትን በመመልመልና በማሰልጠን ተደራሽነትን ማሳደግ
- ለሉአላዊት ኢትዮጵያ መጠበቅ የመጨረሻ ምሽግ ለሆነው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ምልምል ወታደሮችን ከማሰለፍ ባሻገር የክብር ተመላሽ ሰራዊቶችንም በመቀበል ለአካባቢው ሰላም ተጨማሪ ሚናቸውን እንዲወጡ የማድረግ ተግባራትን ይሰራል
- የመንግስት የልማት ድርጅቶችን፣ የህዝብና የመንግስት ሃብትና ንብረት፣ የኢንቨስትመንት ሃብቶችን ደህንነት ከምዝበራና ዝርፊያ የማስጠበቅ ተግባራት በዋናነት የሚሰራ ሲሆን
- በዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራትን ተፈጻሚነት ለማሳደግ ከወረዳ ማእከል ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ 40 የገጠር እና 3 የከተማ ቀበሌዎች
የቀበሌ የሰላም ኮሚቴ
የፀጥታ ምክር ቤት
የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የወሳኝ ኩነት ምክር ቤት
በትምህርት ቤቶች የሰላም ክበባትን እና መሰል የሰላም እሴት ግንባታውን የሚያጠናክሩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የሚከሰቱ አለመግባባቶችን የመፍታየማስጠበቅ ስራ ያለው ሰላም ወዳድ ማህበረሰብ ያለበት የሰላም ቀጠና ነው::
ተልዕኮ/Mission/
- አሰራርና አደረጃጀትን ዘመናዊ በማድረግ፣ ጠንካራ የፀጥታ መረጃ ሥርዓት በመፍጠር፣ በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚታገዝና ብቃት ያለው የፀጥታ ኃይል በማፍራት ግጭትንና በሃይማኖት ወይም እምነት ሽፋን የሚፈጸም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አመለካከትን በብቃት በመመከትና በመከላከል የወረዳው ፀጥታ፣ ሠላምና ደህንነት መጠበቅና ህገ-መንግሥቱን በማስከበር የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣
- ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የኩነቶች መረጃ በብቃትና በጥራት በመሰብሰብ ለፖሊሲ ቀረጻ ለክልላዊና አገራዊ ስትራቴጂ አቅጣጫ እና ለማህበራዊ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ፡፡
- ለተገልጋዮች የወሣኝ ኩነት መረጃዎችን በመስጠት የአገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ፡፡
ተልዕኮ/Mission/
- አሰራርና አደረጃጀትን ዘመናዊ በማድረግ፣ ጠንካራ የፀጥታ መረጃ ሥርዓት በመፍጠር፣ በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ የሚታገዝና ብቃት ያለው የፀጥታ ኃይል በማፍራት ግጭትንና በሃይማኖት ወይም እምነት ሽፋን የሚፈጸም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አመለካከትን በብቃት በመመከትና በመከላከል የወረዳው ፀጥታ፣ ሠላምና ደህንነት መጠበቅና ህገ-መንግሥቱን በማስከበር የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ፣
- ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የኩነቶች መረጃ በብቃትና በጥራት በመሰብሰብ ለፖሊሲ ቀረጻ ለክልላዊና አገራዊ ስትራቴጂ አቅጣጫ እና ለማህበራዊ አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ፡፡
- ለተገልጋዮች የወሣኝ ኩነት መረጃዎችን በመስጠት የአገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ፡፡
ዕሴቶች የሴክተሩ ሠራተኞችና የሥራ አመራሩ የሚመሩባቸውና ወደፊትም በጋራ ሊከተሏቸው የሚገቡ የግልና የተቋም የአሰራር ፍልስፍናዎች ሲሆኑ የሴክተሩ እሴቶችም፡-
- ለህገ-መንግሥቱ ታማኝ መሆን፣
- የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማረጋገጥ፣
- ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣
- የሕዝብ አገልጋይነት፣
- ብዝሃነት መቀበልና ማክበር፣
- ፍትሃዊነትና ሰብአዊነትን መላበስ፣
- ራስን ማብቃት፣ አዳዲስ አሠራሮችን ማወቅና መጠቀም፣
- ሙያዊሥነ-ምግባርመላበስ፣
- ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ትኩረት መስጠት እና
- ኃላፊነትንመወጣት የሚሉት ናቸው፡
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834