የመማር ማስተማር ስራዎችን በማጠናከር የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን የእኖር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

መጋቢት 18/2017 ዓ.ም
================
የመማር ማስተማር ስራዎችን በማጠናከር የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን የእኖር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጽ/ቤቱ ይህንን ተግባር የበለጠ ለማጠናከር በዛሬው እለት ለ2ተኛ ደረጃ ሀገር አቀፍ ፈተና አስፈታኝ ትምህርት ቤት መምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ላይ የተገኙት የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሽኩረታ አ/ከሪም እንደገለጹት የትምህርት ስራው ጤታማነት ሂደት፣ግብዓትና ውጤት የሚፈልግ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም የትምህርት ዋንኛ ባለድርሻ የሆኑት አካላት በነዚህ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት ያለባቸው መሆኑን አስገንዝበዋል።
መምህራን የሚሰጡት የማጠናከሪያ ትምህርት ውጤታማ በሚያደርግ የትምህርት ስነ ዘዴ ሊሰጡ እንደሚገባ ያመላከቱት ኃላፊው ለተማሪዎች ተዘጋጅተው እየተሠጡ ያሉ መልመጃዎች እና ተከታታይ ምዘናዎች ለቀጣይ ፈተናዎች የሚያዘጋጅ ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስቧል።
እንደ አቶ ሽኩረታ ገለጻ ከዚህ በተጨማሪም አገልግሎት ሰጪ ክፍሎች ማለትም ቤተ መጽሀፍት፣ ቤተ ሙከራና የትምህርት መረጃ መሳሪያዎችን በተገቢው ለመማር ማስተማር ስራ አገልግሎት ማዋል ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙት የጽ/ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ በሰአቱ ብርጉ በበኩላቸው ለተማሪዎች የመልመጃ ጥያቄዎች እየተሰጣቸው ራሳቸውን ለሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጁ ለማድረግ የመምህራን፣የርዕሰ መምህራንና የሱፐርቫይዘሮች የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ሊጠናከር ይገባል።
በቀጣይ የትምህርት ግዜያት መምህራንና የትምህርት አመራሮች በተቻላቸው መጠን ሁሉ የመማር ማስተማር ስራ ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ እንዲደረጉም አጽንኦት ሰጥቷል።
በስልጠናው የተገኙ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑና ለታሰበው የተማሪዎች ዉጤት ማሻሻል አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል።
በስልጠናው ከየትምህርት ቤቱ የተመረጡ ሞዴል መምህራን፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የጽቤቱ ሙያተኞችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *