የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ የ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

መጋቢት 20/2017ዓ.ም
=============
የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ የ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አስመልክቶ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ዋና አስተዳዳሪው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በጉጉት ከሚጠበቁትና በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የዒድ አልፈጥር በዓል አንዱ መሆኑን የገለጹት አስተዳዳሪው ህዝበ ሙስሊሙ ዒድን የሚያከብረው ወሩን በፆምና በስግደት በማሳለፍ ይበልጥ ወደ ፈጣሪው በመቃረብ እንደሆነም አመልክተዋል።
አቶ መብራቴ አክለውም ምዕመኑ በፆም ወቅት ያሳየው መልካም ተግባር በቀጣይ ጊዜያት በማስቀጠል በተለይም እርስ በርስ በመተዛዘን፣ አብሮነትን በማጠናከርና የእምነቱ አስተምሮችን በተገቢው በመፈፀም ላይ ሊሆን እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አልፈጥር በዓል ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅና መሰል መልካም ተግባራትን በመፈፀም መሆን እንዳለበትም ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነትና የአብሮነት እንዲሆንም ዋና አስተዳዳሪው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *