የጉራጌ ማህበረሰብ በዘመናት መስተጋብሩ ካፈራቸው ማህበራዊ እሴቶች አንዱ “ድረድግ” በሚል የሚታወቀው የህይወት ፍልስፍና ነው፡፡

መጋቢት 18/2017ዓ.ም
===========የጉራጌ ማህበረሰብ በዘመናት መስተጋብሩ ካፈራቸው ማህበራዊ እሴቶች አንዱ “ድረድግ” በሚል የሚታወቀው የህይወት ፍልስፍና ነው፡፡
“ድረድግ” የሚለው ቃል በጉራጌ ማህበረሰብ ውስጥ ከትንሽ እስከ ትልቅ በሁሉም አእምሮ ፈጥኖ የሚመዘዝ ቃል ሲሆን ቃሉ የማህበራዊ ህይወት ግንኙነት መልህቅ ፣የስብዕና የሰባዓዊነት መልህቅ ፣የባህላዊ የደንነት ወይም የማህበራዊ ፍትህ ሚዛናዊነት መልህቅ እና ማህበረሰቡ የሞራል ህግ መልህቅ በመሆን ዘመን ተሸግሮ ዛሬም ዘልቋል።
እያንዳንዱ የጉራጌ ማህበረሰብ በህገ- ልቦናው ወይም በህሊናው የሚከብደው አሊያም የሚሰቀጥጠው ነገር ሲገጥመው ፈጥኖ ከአእምሮ የሚመነጨውና ከአንደበቱ ሚወጣው “ድረድግ” የሚል በአራት ፊደል የተዋቀረ ቃል ነው።
ቃሉ ከማህበረሰቡ ፍልስፍናና እሳቤ አንፃር በጣም ሰፊና ጥልቅ ማህበራዊ ሂወት ትርጉም እንዳለው ይታወቃል፡፡ ባህላዊ ሸንጎ ከመመስረቱ በፊት ማህበረሰቡ ይመራ የነበረው በሃይለኞችና በጉልበተኞች ስለነበረ ብዙ እንግልት በደልና ግፍ ይደርስበት እንደነበር የማህሰረሰቡ አንጋፎች ይገልፃሉ ፡፡
ያኔ የነበረ ግፍና በደል ያገሸገሻቸው ጥቂት የመረራቸው በየ አደባባዩ የመውጣት የሚያመልኩ አምላክ ጩኻታቸው ሲያሰሙ አምላካቸውን ደርሶ እንዲታደጋቸው በተለይ የማህበረሰቡ ውስጥ ጥበብና እውቀት ያላቸው ይሁንታ የሰጣቸው በደልን የሚጠየፉና ለፍትህ የሚቆሙ አባቶች የመሰረቱት ባህላዊ ሸንጎ አስተዳደር ሲተካካም ዛሬን በመዝለቅ በተሸለ አደረጃጀት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
በደልና ግፍ ይጠየፉ የነበረው የማህበራዊ ሸንጎ አባላት በማህበረሰቡ ውስጥ በአይናቸው የሚያዩትን በጆሮዋቸው የሚሰሙት ክፉ ነገር እየቆየ እንደ ተስቦ በማሰራጨት የማህበረሰቡ መፃዒ ሂወት ሊያጠለሽ እንደሚችል ቀድሞ በመገንዘብ ሸንጎ በተቀመጠበት ሁሉ ማህበረሰቡ እየሰማ ምንም አይነት ዳኝነት ሆነ ሃሳብ ከመለዋወጣችን በፊት ቀድመው “ድረድግ” ይላሉ ፡፡
የሸንጎ አባላት ስለተሰበሰቡበት ጉዳይ አንስተው ከመጣላቸው በፊት ድረድግ ማለታቸው ስንመለከት የሚናገርም የሚያዳምጥው ክፉ ኢ-ሰብዓዊ ኢ- ሞራላዊ ተግባር በፈጣሪ እንዲጠበቅ ለመማፀን ነው፡፡
የሆነ ሰው አንድን ቤት ቢያቃጥል ድንበር ቢነቀንቅ(ቢገፋ)፣ ሴት ልጅ ብትደፈር ፣የአንዱ ሂወት በሰው እጅ ሲያልፍ፣ ልጅ በአባቱ /በእናቱ ላይ እጅ ቢሰነዝር ፣ያልታሰበ ነገር ድንገት ቢከሰትና ጥፋት ቢያጋጥም ያየም የሰማም ምንም ከማለቱ በፊት አስቀድሞ ድረድግ በማለት ያየውና ለሌላ ማውራት ይጀምራል፡፡
ትልልቅ እናቶችም ሆነ አባቶች ድረድግ ብቻ ሳይሆን 7 ጊዜ ድረድግ ይላሉ፡፡
ይህንን 7 ዘራቸው ሁሉ በጆሮዋቸው ከሰሙትና ባይናቸው ካዩት ክፉ ነገር እንዲጠበቅ በማሳሰብ ነው ፡፡የተለያዩ ማህረሰቡን በሚመለከት ከተፃፉ መፅሐፍት የተወሰደ
  

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *