ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የዜጎቻችንን ጊዜያዊ ችግሮች ከማቃለልና ከመፍታት ባሻገር የአብሮነት፣የመተሳሰብ እና የመቻቻል አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን ተገለፀ።

መጋቢት 10/2017 ዓ.ም
=================ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የዜጎቻችንን ጊዜያዊ ችግሮች ከማቃለልና ከመፍታት ባሻገር የአብሮነት፣የመተሳሰብ እና የመቻቻል አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን ተገለፀ።
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በተደመረ እውቀት፣ጉልበትና ክህሎት ሀገርን መገንባት እንደሆነም ተጠቁሟል።
በእኖር ወረዳ እየተካሄደ ባለው የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት የበርካታ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን የመኖርያ ቤት ችግር እየቀረፈ ይገኛል።
በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችም በዛሬው ዕለት በወረዳዉ መቃና ቀበሌ በከፍተኛ የመጠለያ ችግር ውስጥ የነበሩ የወ/ሮ ጊዜ ተረዳ ቤት መገንባት ችለዋል።
የእኖር ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ እና የበጎ ስራ አስተባባሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የዜጎቻችንን ጊዜያዊ ችግሮች ከማቃለልና ከመፍታት ባሻገር የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እና የመቻቻል አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ሞሸዲን አክለውን ተጋላጮችን በተገቢው እየተለየ ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ በተለይም ባለሀብቶችና በኢንቨስትንት የተሰማሩትን በማስተባበር ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል።
የፓርቲያችን ዕሳቤ የሆነውን ሰው ተኮር ማህበራዊ መስተጋብር ቀጣዩን ትውልድ በነባሩ የመተሳሰብና የአብሮነት ዕሴት ላይ ለመገንባት ጉልህ ሚናም እንዳለው አውስተዋል።
በወረዳው የሚከናወኑ የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችም የህብረተሰቡ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን እያቃለለ ስለመሆኑም አንስተው በጎ ፍቃድ የማህበረሰቡ ባህል ሆኖ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ስኬታማ ለማድረግና በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ቅንጅታዊ አሰራሮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቸሩ ተካ አስታውቀዋል።
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በተደመረ እውቀት፣ጉልበትና ክህሎት ሀገርን መገንባት እንደሆነም በመጠቆም።
የድጋፉ ተጠቃሚ በወረዳው የመቃና ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ወ/ሮ ጊዜ ተረዳ ይባላሉ ምንም አይነት ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው በመሆኑ ለዘመናት ሊፈርስ በደረሰ ፀሀይና ዝናብ መቋቋም በማይችል ደሳሳ ጎጆ ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበርም ተናግረዋል።
ሆኖም በአሁን ሰዓት በወረዳው መንግስትና በአካባቢው ማህበረሰብ ቅንጅት የቤት ባለቤት መሆናቸውን አብራርተዋል።
የዚህ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ላገዙት ወ/ሮ ጊዜ ከልብ አመስግነዋል፣መርቀዋልም።
በዚህ መልካም ተግባር የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ፣የወጣ/ስ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ባሙያዎችን ጨምሮ የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳተፊ መሆናቸውን ተገለጸ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *