መጋቢት 8/7/2017 ዓ.ም
=================
በእኖር ወረዳ የሁረድ ቀበሌ ተወላጅ የሆኑ የከተማ ነዋሪዎች ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት በአካባቢው ለተለያዩ የመኖሪያ ቤት ችግር ውስጥ ለነበሩ ወገኖች መጠለያ መገንባታቸውን ተገለጸ።
የእኖር ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪና የበጎ ስራ አስተባባሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ እንዳሉት በወረዳው እየተሰራ ያለው ሰው ተኮር የሆነው የበጎነት ተግባር በማህበረሰቡ ዘንድ ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቁመዋል።
አቶ ሞሸዲን አክለውም ወቅቱን የጾምና የጾሎት እንደመሆኑ መጠን ማህበረሰባችን የተለመደው የመረዳዳትና የመተሳሰብ አሴቱን አጉልቶ እንዲያሳይም ጥሪ አቅርቧል።
በቀበሌው ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ለመርዳት በሚደረገው ጥረት ከተማ የሚኖሩ የአካባቢ ተወላጆች ማህበር ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ በመሆኑም ምስጋና አቅርበዋል።
በዛሬው ዕለት ቤታቸው የተገነባላቸው የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ ዳረጌ ይርጋ ፣ወለቱ ሳጂና ንውድ ዘርጋ ለአመታት የመኖሪያ ቤት ችግር ውስጥ እንደነበሩ ተናግረዋል።
ከተረጂዎች መካከል አቶ ዳርጌ ይርጋ ምንም አይነት ጧሪና ደጋፊ የቤተሰብ አባል እንዲሁም ቤት ያልነበራቸው ከመሆኑ የተነሳ በአካባቢው እየተዟዟሩ ኑሮዋቸው ይገፉ እንደነበር ተናግሯል።
በሌላ በኩል መኖሪያ ቤታቸው በመፈራረሱ ምክንያት የክረምት ወቅት ሲመጣ ሀሳብ ይገባቸው እንደነበርም ወ/ሮ ንወድ ዘርጋ አመላክቷል።
ሌላኛዋ የበጎ ስራ ተጠቃሚ የሆኑት ወ/ሮ ወለቱ ሳጂን የሁረድ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው።
ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት ችግር ውስጥ የነበሩ መሆኑን ገልጿል።
ተረጂዎቹ በአሁን ወቅት ችግሩን የቀበሌ ተወላጅ በሆኑ የከተማ ነዋሪዎች ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀናጀት የተፈታላቸው በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸው ለዚህም ከልብ አመስግነዋል።
