በእኖር ወረዳ ጉስባጃይ ከተማ በብልሽት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የውሃ ፕሮጀክት ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተገለጸ።

መጋቢት 11/7/2017ዓ.ም
=================
በእኖር ወረዳ ጉስባጃይ ከተማ በብልሽት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የውሃ ፕሮጀክት ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተገለጸ።
ይህ ለአመታት ተቋርጦ የነበረው የውሃ አገልግሎት በከተማው በሚገኘው በኮፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጲያ 2 ሚሊዮን 9 መቶ 90ሺ 790 ብር ወጪ በማድረግ ጥገና ተደርጎለት መሆኑን ተጠቁሟል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ አበበ አገዘ እንደገለጹት በወረዳው የሚገኙ የተለያዩ ድርጅቶች መንግስት ያልደረሰላቸው የማህበረሰቡ የልማት ጥያቄዎች እየፈቱ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
ማህበረሰቡ ዛሬ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የውሃ ፕሮጀክትና ሌሎችም በወረዳው የሚገኙ የልማት ስራዎች ተገቢውና ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ በባለቤትነት መጠበቅና መንከባከብ እንዳለበትም አመላክቷል።
ይህ አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረውን የውሃ ፕሮጀክት በመጠገን ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ በመደረጉም አቶ አበበ በወረዳው መንግስት ስም ከልብ አመስግነዋል።
በጉስባጃይ ከተማ የሚገኙው የኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጲያ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ወልዴ በበኩላቸው የውሃው ብልሽት በኮፓሽኑ በታቀፉ ልጆችና በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ እንደነበር ገልጸዋል።
ኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጲያ ችግሩን በመረዳት ከ2 ሚሊዮን 9 መቶ 90ሺ 7መቶ 90 ብር ወጪ በማድረግ አገልግሎት እንዲሰጥ ማደረጉንም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
አቶ ሳሙኤል አክለውም ውሃው በኮምፓሽኑ ለታቀፉ 172 ልጆችና በአካባቢው ለሚገኙ ለ3ሺ200 ሰዎች አገልግሎት መስጠት እንደሚችልም ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ኮምፓሽኑ ውሃው አገልግሎት እንዲስጥ እያደረገው በነበረው ጥረት ከፍተኛ ድጋፍና እጋዛ ለደረገው ለወረዳው መንግስት፣ለወረዳው ውሃ ጽ/ቤትና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት አመስግኗል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *