በእኖር ወረዳ እየተሰራ ያለው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የብዙ ተጋላጭ ወገኖችን ተስፋ እያለመለመ መሆኑን ተገለጸ።

ጥር 16/2018 ዓ.ም
በእኖር ወረዳ እየተሰራ ያለው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የብዙ ተጋላጭ ወገኖችን ተስፋ እያለመለመ መሆኑን ተገለጸ። ወ/ሮ ዚያዳ ሟረታ በወረዳው ካሳይ ቀበሌ ስርጥ መንደር ነዋሪና የሶስት ህጻናት ልጆች እናትና ምንም አይነት ደጋፊ የሌላቸው ናቸው።
መኖሪያ ቤታቸው አርጅቶ ቢፈርስም ከሰው ጋር ተዳብሎ ከመኖር ዝናብና ፀሀይ እየተፈራረቀባቸው በራሱ ይኖሩ እንደነበረም ገልጸዋል።  ወ/ሮ ዚያዳ ሟረታ ይህንኑ የተገነዘቡት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተባብረው የግንባታ ቁሳቁስ በመግዛት በዛሬው ዕለት የወ/ሮ ዚያዳ መኖሪያ ቤት ገንብተዋል። በስራው ላይ የተገኙት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አ/መጅድ ጀማል እንደገለጹት በወረዳው በመንግስትና በደጋግ ልቦች ፍቃደኝነት እየተካሔደ ያለው በጎ ተግባር ለብዙ ችግር ውስጥ ለነበሩ ወገኖችን እንባ እያበሰ መሆኑን ገልጸዋል። አንድ ተቋም ለአንድ ተጋላጭ ወገን ለመደገፍ እንደወረዳ የተቀመጠውን አቅጣጫ በመከተል የጽ/ቤቱ ሐላፊዎችና ባለሙያዎች የግንባታ የቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ በግንባታው ላይ በንቃት መሳተፋቸውንም አቶ አ/መጅድ አብራርቷል። የጽ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ መስፍን ወንድሙ በበኩላቸው በወረዳው መንግስት እየተሰራ ያለው ሰው ተኮር የበጎ ፍቃድ ስራ ለብዙ ተጋላጭ ወገኖችን ችግር እየፈታ መሆኑን አመላክተዋል። የወረዳው ግብርና ተቋም ይህንን በመከተል በጎነት ለራስ ነው በሚል ሀሳብ የአንዲት እናት የመኖሪያ ቤት ችግር መፍታት መቻሉን ገልጸው። ወ/ሮ ዚያዳ በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸው እገዛ ላደረጉ አካላት በሙሉ መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማቸው በመመረቅ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *