በእኖር ወረዳ ጉስባጃይ ከተማ የህብረተሰቡን የዘመናት የመናኸሪያ አገልግሎት ጥያቄ ምላሽ በማግኘት የግንባታ ስራ በይፋ መጀመሩን የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አስታወቀ።

መጋቢት 16/2017 ዓ.ም
=================በእኖር ወረዳ ጉስባጃይ ከተማ የህብረተሰቡን የዘመናት የመናኸሪያ አገልግሎት ጥያቄ ምላሽ በማግኘት የግንባታ ስራ በይፋ መጀመሩን የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አስታወቀ።
የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ታምራት ጠንክር በማስጀመርያ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው እንደገለጹት በእኖር ወረዳ ጉስባጃይ ከተማ የህብረተሰቡን የዘመናት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የቆየውን የመናኸሪያ አገልግሎት ምላሽ በማግኘት የግንባታ ስራ በይፋ መጀመሩን ገልፀዋል።
መናኸሪያው በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቆጣጠር ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
የመናኸሪያ ግንባታው ከ4 መቶ 51 ሺ ብር በላይ ለልማት ተነሺዎች ካሳ በመክፈል መሬቱ ከይገባኛል ነፃ የተደረገ መሆኑን ያነሱት አቶ ታምራት ለዚህም 1.5 ሄ/ር መሬት ለኮንተራክተሩ ማስረከብ መቻሉንም አስረድተዋል።
ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲያስችል እና ለስራው ውጤታማት ወረዳው አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አንስተው ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ መጨናነቆችን በእጅጉ እንደሚቀንስም ነው ያመላከቱት።
የመናኸሪያው ግንባታ በቅርቡ ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም አክለው ገልፀዋል።
በአሁን ወቅት በጉስባጃይ ከተማ መንግስትና ህዝብ በመቀናጀት የተለያዩ የመሠረተ ልማት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
በዚህም ከተማው ለማልማት በማዘጋጃ ቤቱና በማህበረሰብ ተሳትፎ 1.12 ኪ.ሜ የመንገድ ጠረጋና ከፈታ፣360 ሺ ብር ወጪ በማድረግ ወደ ጊዶሳይ መሻገርያ(ዲፓራይ) የትቦ ቀበራና የስላቭ ስራ የተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
አቶ ታምራት አክለውም የኑሮ ውድነት ጫና የሚቀንስና ሸማቹ እና አምራቹን በቀጥታ የሚያገናኝ የሰንበት ገበያ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ ማስረከባቸውን ተናግረው አሁን ላይ በከተማው ማህበር በማደራጀት በሊዝ ተጫርተው መሬት ያገኙ አካላትም የማልማት ስራ ከመስራት አኳያ አበረታች መሆኑንም አስታውቀዋል።
በቀጣይም በከተማው ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለማከናወን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ሀላፊው አሳስበዋል።
የከተማው ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ስራጅ ብርጉ እንዳሉት ከተማው ለማልማት የሰፈር፣የጣቢያ እና የመንደር አደረጃጀቶችን በማጠናከር ወደ ስራ የተገባ ሲሆን ለዚህም ማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ ሁለቱም መንደር ላይ(ላቃ እና ላይ ጉስባጃይ) የትራንስፎርመር ግዢ ለመፈፀም ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን አስገንዝበዋል።
እንደ አቶ ስራጅ ገለፃ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል 9.1 ሄ/ር መሬት ለማልማት በታቀደው መሠረት 11.24 ሄ/ር መሬት ማልማት መቻሉንም ጠቁመዋል።
በማዘጋጃ ቤቱ 2.5 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 3 ሚሊየን 598 ሺ 423 ብር መሰብሰብ ተችላል ብለዋል
 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *