በእኖር ወረዳ ጉስባጃይ ከተማ የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የተጀመረው ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ገለጸ።

መጋቢት 13/2017 ዓ.ም
================
በእኖር ወረዳ ጉስባጃይ ከተማ የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለመቀነስ የተጀመረው ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያ ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ገለጸ።
ለገበያው እየቀረቡ ያሉ ምርቶቹም በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች ተደራጅተው በሚሰሩ ወጣቶች መሆኑንም ተጠቁሟል።
በዕለቱ የተገኙት የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጃ አብድልባሲጥ እንደገለጹት ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያ ሸማቹና አምራቹን በቀጥታ በማገናኘት የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና በመቀነስ ረገድ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል።
ይህ ተግባር በተለይ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሬ በማድረግ ማህበረሰቡን ጫና ውስጥ የሚያስገቡ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ያስችላልም ብለዋል።
አሁን ያለው ሁኔታ መነሻ በማድረግ በቀጣይ የሸማቹ ማህበረሰብ ፍላጎት ለማሟላት ምርት በጥራትና በብዛት እንደሚቀርብም አቶ ነጃ ጠቁመዋል።በመሆኑም የአካባቢው ማህበረሰብ መጥቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን እንዲሸምትም ጥሪ አቅርበዋል።
በዛሬው የገበያ ቅኝትም ሽንኩርት በኪሎ 50 ብር፣ቲማቲም በኪሎ 25 ብር እና እንቁላል በፍሬ 12 ብር በመሸጥ ላይ መሆኑን ግብይቱ ያስረዳል።
በዕለቱ ካነጋገርናቸው ሸማቾች መካከል በለጠች ሙራኒ፣ ሞሼ ዝሩጋና አብድራህማን ተጩ ይገኙበታል።
ሸማቾቹ በጋራ በሰጡት አስተያየት የተጀመረው የሰንበት ገበያ የማህበረሰቡ የኑሮ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ በመሆኑ የወረዳው መንግስት እያደረገ ያለው ድጋፍ በማመስገን ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አደራ ብለዋል
   

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *