መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
===============በእኖር ወረዳ ጉስባጃይ ከተማ የኑሮ ውድነትን ጫና የሚቀንስ እና ሸማቹና አምራቹን በቀጥታ የሚያገናኝ ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያ በዛሬው ዕለት በይፋ ተቋቋመ።
የእኖር ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ነጃ አብድልባሲጥ የተቋቋመው የሰንበት ገበያ በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት የሰንበት ገበያ ሸማቹና አምራቹን በቀጥታ የሚያገናኝ እንደዚሁም ህገ ወጥ ነጋዴዎችን የሚያስቀር መሆኑን ገልፀዋል።
ሸማቹና ነጋዴው ማህበረሰብ የሚያገናኝ በወረዳው ጉስባጃይ ከተማ የገበያ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ
በዛሬው ዕለት ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያ በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።
ዛሬ የተቋቋመውን የሰንበት ገበያ በከተማዋ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋምና ገበያውን ለማረጋጋት ጉልህ ሚና እንዳለው ያነሱት አቶ ነጃ የመንግስት ሰራተኛው እና የአካባቢው ነዋሪዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችልም ተናግረዋል።
ሀላፊው አክለውም ምርቶቹም በወረዳው ውስጥ በተደራጁ ወጣቶች አማካኝነት ይህም እንቁላል ጋንዛቸ ከተማ ከሪሃና ዲነካ፣ሽንኩርት አጋሬ ቀበሌ በተደራጁ ማህበራት እንደዚሁም ቲማቲም ደግሞ ጎምሸ ቀበሌ በተደራጁ ወጣቶች የቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም በዛሬው ዕለት ሽንኩርት=በኪሎ 50 ብር
ቲማቲም=በኪሎ 25 ብር
እንቁላል=በፍሬ 12 ብር በመሸጥ ላይ ውሏል ብለዋል።
በዚሁ ወቅት የሰንበት ገበያዎችን ማስፋፋትና ማጠናከር ያልተገባ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠርና ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው ጨምረው ገልፀዋል።
የሸማቹ ማህበረሰብ ፍላጎት ለማሟላት በጥራትና በብዛት እንደሚቀርብ ተናግረው ሰንበት ገበያ ላይ የሚሸጡ ምርቶች በጣም ቅናሽ እንደሆነም ሀላፊው አመላክተዋል።
ለንግድ ስርዓቱ ጠንካራ መሠረት ለመጣል የወረዳው መንግስት፣የወረዳው አመራር፣ነጋዴ ማህበረሰብ ክፍሎች እና የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እያደሩጉት ያለውን አስተዋጽዖ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
ሲሸምቱ ያገኘናቸው አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት መንግስት የሌማት ትሩፋት ፕሮግራም በማውጣት የህብረተሰቡ ችግሮችን ለመፍታትና ፍላጎቶችን ለማሟላት እየሰራ ያለው ስራ በእጅጉ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
ከሰንበት እስከ ሰንበት የተለያዩ ምርቶች የሚሸምቱበት ገበያ ስለተመቻቸላዉ ደስተኛ መሆናቸዉም አስታውቀው በቀጣይም ምርቶችን በብዛት በማስገባት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
በማስጀመርያ መርሃ-ግብሩ ላይ የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ነጃ አብድልባሲጥ፣የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እና የጉስባጃይ ከተማ ሸማች ማህበረሰብ ተገኝቷል

