በእኖር ወረዳ ተርሆኘ ቀበሌ በዶሮ እርባታ የተደራጁ ወጣቶች ውጤታማ መሆናቸው ገለጹ።
ወጣቶቹ በአሁን ወቅት ቆጠበው ከአለም አቀፍ የሄይፈር ኘሮጀክት 1ሺ 3መቶ 73 የአንድ ቀን ጫጩት ተረክበው በትኩረት እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተርሆኘ ቀበሌ የሁቲሂር ማህበር ሰብሳቢ የሆነው ወጣት መንግስቱ ደምስስ እንደገለጸው ቀድሞ በመቆጠብ ከፕሮጀክቱ የወሰድዋቸውን የአንድ ቀን ጫጩቶች ላይ ወጤታማ በመሆን ለሌሎች አርሶአደሮች እያከፋፈሉ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት የወሰዱዋቸው የአንድ ቀን ጫጩቶች በ60 ቀናቸው 2 መቶ 24 ዶሮዎች ለአርሶ አደሩ እንዲሰራጭም ነው ያቀረቡት።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ መስፍን ወንድሙና ድንድር በረዳ
በጋራ በሰጡት አስተያየት ወጣቶች ፕሮግራሙን እንደ እድል ወስደው በዘርፉ በተገቢው እንዲጠቀሙ መክረዋል።
በኘሮጀክቱ በወረዳው በ8 ቀበሌዎች በሚገኙ 136 አርሶአደሮች ላይሆን የሌማት ቱሩፋት መሰረት ባደረገ መልኩ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ፕሮግራሙ የማህበረስቡን የምገግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለመቅረፍ፣ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ወስጥ ምርት ለመተካትና የስራ እድል በመፍጠር የወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የፕሮግራሙ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ለገሰ ሎዳሞ በበኩላቸው ፕሮግራሙ ለአርሶአደሮችና ለወጣቶች እንዲሁም ለሴቶች የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባሻገር ዘላቂ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በአሁን ወቅተ በዶሮ እርባታ ዘርፍ እየሰራ ቢሆንም በቀጣይ በተለያዩ የግብርና
ዘርፎች ለመሰራት ማቀዱንም አመላክተዋል።
እስካሁን አንደ ሀገር በሶስት ክልል ይሰራል ያሉት አስተባባሪው በተለይ በማአከላዊ፣ በሲዳማና በአማራ ክልል በሚገኙ 9 ወረዳዎች መሆኑን አብራርተዋል።በዚህም በእኖር ወረዳም በአንድ የተደራጀ ማህበር የሚደገፉ አርሶ አደሮች 136 መሆናቸውን ጠቁሟል።
አርሶአደሮች በዛሬው እለት የወሰዱዋቸው ዶሮዎች ተገቢውን ጥቅም እንዲሰጡ በቂ እንክብካቤና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
