ሁለተኛ ዙር ሞዴል የሴቶች ልማት ህብረት የምረቃ ፕሮግራም በአሞገራ ቀበሌ በድምቀት መካሄዱ የእኖር ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ገለጸ።

ሁለተኛ ዙር ሞዴል የሴቶች ልማት ህብረት የምረቃ ፕሮግራም በአሞገራ ቀበሌ በድምቀት መካሄዱ የእኖር ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ገለጸ።
በምረቃ በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የእኖር ወረዳ የመንግስት ረዳት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ መልስ እንደገለጹት መንግስት ሴቶችን እንደ ሀገር በሁሉም ዘርፍ በማሳተፍ ተጠቃሚና በሀገር እድገትና ብልጽግና ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ አቶ ፍቅሬ ገለጻ ሴቶች በግብርና ምርታማነት፣በጤና፣በትምህርት፣
በቁጠባና በሌሎችም ዘርፎች ውጤታማ ለማድረግ የሴቶች ልማት ህብረት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
አደረጃጀቱን በተገቢው በመጠቀም የሴቶች ተጠቃሚነት በተጨባጭ ለማረጋገጥና ችግር ፈቺ ለማድረግ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የወረዳው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ እና የቀበሌው ደጋፊ አመራር ክቡር አቶ መህዲ አህባብ እንደገለጹት ቀበሌው ቀድሞም የተሻለና ሞዴል የሴቶች አደረጃጀት የነበረበት መሆኑን ገልጸው ይህንንም አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።
የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፋንቱ ደምስስ እንደተናገሩት በአሁን ወቅት እንደ ወረዳ የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተስራ መሆኑን አስረድቷል።
በመሆኑም እንደ ወረዳ 788 ልማት ህብረት 2ሺ 3መቶ 61 አንድ ለ10 አደረጃጀት እና 23 ሺ 8 መቶ 44 አባላት ያሉ መሆኑን ጠቁመዋል።
ኃላፊዋ አክለውም እንደ ተቋም በየ3 ወሩ ሁለት ሞዴል ቀበሌዎችን ለማስመረቅ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ዛሬ የዚሁ አካል የሆነው ሁለተኛ ዙር ሞዴል ልማት ህብረት ማስመረቅ መቻሉን አመላክተዋል።
ፕሮግራሙ በቀበሌው ሞዴል እና የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው ልማት ህብረት ቡድኖች እውቅና በመስጠትና ለተሞክሮ ይሆን ዘንድ የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተጠናቋል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *