የተቀናጀ ግብርና ለፈጣን ኢኮኖሚ እድገትና የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ቁልፍ ሚና እንዳለው የእኖር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።

የተቀናጀ ግብርና ለፈጣን ኢኮኖሚ እድገትና የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ቁልፍ ሚና እንዳለው የእኖር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጽ/ቤቱ በምግብ ስርዓት ማሻሻያና ማጠናከሪያ (FSRP) ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ በተቀናጀ የግብርና ተግባራት ዙርያ ይህም በሆርቲካልቸርና በአዝርዕት ሰብሎች፣በሰብል ጥበቃ በተለይም(በጤፍ፣በስንዴና በገብስ ሰብሎች)፣እንደዚሁም በአግሮሚናል ሰብል ጥበቃ፣በመስኖ ዉሃ አጠቃቀም እና በመሳሰሉት ላይ ለግብርና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
የተቀናጀ የግብርና ስራ በማጠናከር እና የምርታማነት መለያየት በማቀራረብ የምግብ ሉአላዊነት ያረጋገጠ ቤተሠብ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተጠቁሟል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የእኖር ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብድልመጅድ ጀማል እንደገለፁት የተቀናጀ ግብርና ለፈጣን ኢኮኖሚ እድገትና የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ቁልፍ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።
በምርት ዘመኑ የታቀደውን የምርታማነት ግብ ለማሳካት በተቀናጀ የሰብል ጥበቃ ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል።
የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣የገቢ ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት፣የውጪ ምርቶች በጥራትም በብዛትም ማሳደግ፣ለወጣቶችና ለአርሶ አደሩ የስራ ዕድል መፍጠር እና የመሳሰሉት 6ቱ የግብርና ምሰሶዎች ከድህነት መውጫ መንገዶች ናቸው ያሉት ሀላፊው በባለሙያው ቁርጠኝነት የግብርና ሴክተር ዓላማ ማሳካት እንደሚገባ አብራርተዋል።
እንደ አቶ አብድልመጅድ ገለፃ በግብርናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ፈተናዎች በጽናት ለማለፍ በተቻለ መጠን የጤፍ በሽታ ለመከላከል ኬሚካል መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።
ለምርታማነት እድገት ቁልፍ የሆነው የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እንዳለበት አንስተው ይህም በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ አበርክቶው ከፍ ያለ ስለመሆኑንም ጠቁመዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበሩ ኢኒሼቲቮች የላቀ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ናቸው ሲሉም ሀላፊው አስረድተዋል።
የጽ/ቤቱ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ አቶ መስፍን ወንድሙ እንዳሉት ለማምረት የሰጠነውን ያክል ትኩረት ለሰብል ጥበቃም የሰጠነው ቢሆን ኖሮ ከዚህ የተሻለ ምርታማነትን ማስመዝገብ እንችል ነበር ያሉ ሲሆን የሰብል ተባይና በሽታ ክስተቶችን በየቀኑ አሰሳና ክትትል በማድረግ የአርሶአደሩን ምርታማነት ለማረጋገጥ ሁሉም በሀላፊነት መስራት አለበት።
በወረዳው የግብርና ልማት በሁሉም ዘርፎች የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የመስኖ ልማት ስራ ሀገራዊ ኢንሼቲቭ መሆኑን በመጥቀስ ለሥራው ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መተግበር እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።
የወረዳው የምግብ ስርዓት ማሻሻያና ማጠናከሪያ (FSRP) ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ጌቱ ኮራ በበኩላቸው ፕሮግራሙ 4 ዋና ክፍሎችና 12 ንዑስ ክፍሎች ያሉት ሲሆን በዋናነት የስርዓተ ምግብ ስርዓቱን ጥንካሬው እንዲጨምርና በምግብ እራስን አለመቻል መከላከል ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።
የግብርናው አገልግሎትና ፈጠራን ማሸጋገር፣አነስተኛ የመስኖ ውሃ ተቋማት ማጠናከርና ማስተዳደር፣ስርዓተ ምግብ ማጠናከርና ፕሮግራሙን ለማስፈጸም ምቹና አስቻይ ሁኔታዎች ማሻሻል የሚሉትን የፕሮግራሙ ዋና ዋና ክፍሎች መሆናቸውንም አቶ ጌቱ ጠቅሰዋል።
በየዘርፉ እየተስተዋሉ የሚገኙ ክፍተቶችን ለአብነት አንስተው ያመላከቱት አስተባባሪው ችግሮቹ እንዲታረሙ በማድረግ ረገድ የባለሙያው ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ስልጠናው በጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።
ከሰልጣኞች መካከል አንዳንድቹ በሰጡት አስተያየት ስልጠናው ወቅታዊና የግብርና ስራዎች አቀናጅቶ ለመፈፀምና ለችግሮች ከወዲሁ መፍትሔ በማስቀመጥ ወደ ተግባር ለመግባት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።በመድረኩ ላይ የቀበሌ የሁሉም ዘርፍ የልማት ጣበያ ሰራተኞችና የቢሮ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *