በእኖር ወረዳ ልማት በህብረት በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው በመስራት ላየ የሚገኙ ሴቶች ተጠቃሚ መሆናቸው ገለጹ።

መጋቢት 22/2017 ዓ.ም
===============
በእኖር ወረዳ ልማት በህብረት በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው በመስራት ላየ የሚገኙ ሴቶች ተጠቃሚ መሆናቸው ገለጹ።
የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ፋንቱ ደምስስ እንደገለጹት የሀገራችን እድገትና ብልጽግና ለማፋጠን የሴቶች ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ ከፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በመሆኑም ተቋማቸው የሴቶች አደረጃጀትና ልማት በህብርት በማጠናከርና በመደገፍ የሴቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ሌላው የሴቶች ሁለንትናዊ ተሳትፎ በማሳደጉ ሂደት የወረዳው መንግስት ከመቼውንም ጊዜ በላይ እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
በወረዳው አጋታ ቀበሌ ኧቃራቃር የሴቶች ልማት በህብረት ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ዚያዳ አብደላ በድንች ዘር ብዜት ዘርፍ ላይ ተጠቃሚ መሆናቸውን ይናገራሉ።
ተጠቃሚ የመሆናቸው ምክንያትም ከህብረቱ የስራ ተነሳሽነትና ፍላጎት ባሻገር በወረዳው የሚገኘው የFSRP ፕሮገራም ከወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት የድንች ምርጥ ዘር ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ በወረዳው ጠረደ ቀበሌ በበጋ ስንዴ መስኖ ላይ የተሰማሩ ልማት በህብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ ብርጫ አወል በበኩላቸው እየተደረገላቸው ባለው የስንዴ ምርጥ ዘርና የማዳበሪያ ድጋፍ በዘርፉ ተጠቃሚ መሆናቸው አመላክተዋል።
ወ/ሮ ብርጫ በተጨማሪ የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት እና ግብርና ጽ/ቤት ህብረቱ ስኬታማ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ ድጋፍና ክትትል እያደረጉ እንደመሆነም ገልጸዋል።
ሌላው የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት በተደረገላቸው ድጋፍ በዘርፉ ዉጤታማ መሆናቸው በወረዳው ተርሆኘ ቀበሌ በዶሮ እርባታ የተደራጁ ሴቶች አስታውቀዋል።
የልማት በህብረት ሰብሳቢዎች በሰጡት አስተያየት የወረዳው መንግስት ሴቶችን በማገዝና በመደገፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራው ያለ ስራ አበረታች ነው ብለዋል።
በመጨረሻም የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጽ/ቤት ህብረቱ ከማደራጀትና ከመደገፍ ጀምሮ የቁጠባ ባህልን በማስተማር እንዲሁም የተለያዩ ምቹ ሁኔታዎች በመፍጠር ረገድ የአንበሳው ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ጠቁመዋል።
  

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *