የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያንን ለመንከባከብ የሚሰሩ ስራዎችን ማገዝ የሁሉም ግዴታ መሆኑን የእኖር ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።

መጋቢት 3/2017 ዓ.ም
===============የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያንን ለመንከባከብ የሚሰሩ ስራዎችን ማገዝ የሁሉም ግዴታ መሆኑን የእኖር ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።
የአረጋውያን ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ፣ተካታችነትና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የአረጋውያን ማህበር ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ተጠቁሟል።
በአረጋውያን ማህበር በመደራጀት ዘርፈ ብዙ ተግባራት ላይ በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን በእኖር ወረዳ አበሩስ የአረጋውያን ማህበር የተደራጁ አባላት ይናገራሉ።
የእኖር ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ፈቀደ እንዳሉት የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያንን ለመንከባከብ የሚሰሩ ስራዎችን ማገዝ የሁሉም ግዴታ መሆኑን ገልፀዋል።
የወረዳው አበሩስ የአረጋውያን ማህበር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ተካታችነት ማጠናከር ያስችል ዘንድ በማህበሩ ስም ያለው መሬት በተገቢው እየተሰራበት መሆኑንም ያነሱት ሀላፊው የተደራጁ ማህበራት እንዲጠናከሩ ከመደገፍ ባለፈ ሀብት እንዲፈጥሩ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
አቶ ብርሀኑ አክለውም አረጋውያን የሚያጋጥማቸውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ሁሉም ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።
አቶ አለሙ በሻ የወረዳው የአበሩስ አረጋውያን ማህበር ሰብሳቢ ናቸው አገኝተን ባነጋርንበት ወቅት እንደገለፁት አረጋውያን በእድሜ ዘመናቸዉ ካካበቱት እውቀትና የህይወት ተሞክሮ በመነሳት የህብረተሰቡ ማህበራዊ የአኗኗር ስርዓት ቀጣይነት እንዲኖረው ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።
አበሩስ አረጋውያን ማህበር 50 አባላት ያሉት ሲሆን ማህበሩ ጠንካራ እንዲሆን የተለያዩ የገቢ አማራጮችን በመፈለግና በማስፋት፣ወርሀዊ መዋጮ በተገቢው በመክፈል እና አባላትን በማፍራት ሰፊ ስራዎች እየሰራ እንደሆም አመላክተዋል።
በመሆኑም በአሁን ሰዓት 3 ኩንታል ድንች በመግዛት ሩብ ሄ/ር መሬት ላይ ምርጥ ዘር ድንች እያመረቱ መሆኑን ያነሱት አቶ አለሙ በዚህም ከ20 ኩንታል በላይ ማግኘት እንደሚችሉም ገምተዋል።
ለዚህ ስራ መሳካት የወረዳው ሰ/ማ/ጉ/ጽ/ቤት እያደረገ ያለውን ሙያዊ ድጋፍና ክትትል በማህበሩ ስም ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *