የህብረተሰቡ ስርዓተ ምግብ አጠቃቀም በማሻሻል ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተገለፀ።

መጋቢት 2/2017 ዓ.ም
*********************የህብረተሰቡ ስርዓተ ምግብ አጠቃቀም በማሻሻል ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተገለፀ።
የእኖር ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት በFSRP ፕሮግራም የበጀት ድጋፍ የተግባር ተኮር ስርዓተ ምግብ አዘገጃጀት ሰርቶ ማሳያ ስልጠና በወረዳው ተርሆኘ ቀበሌ ሰጥቷል።
የወረዳው የስርዓተ ምግብ ማሻሻያና ማጠናከርያ (FSRP)ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ጌቱ ኮራ ስልጠናው በሰጡበት ወቅት እንደገለፁት
የፕሮግራሙ አላማና የአፈፃፀሙ አመላካቾች፣ተቋማዊ አደረጃጀት እንዲሁም በዘርፉ የሚጠበቁ ውጤቶች ዙርያ በመድረኩ ሰፋ ያለ ማብራርያ ሰጥተዋል።
እንደ አቶ ጌቱ ገለፃ ግብርናውን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ፣የእንስሳትና አሳ ሀብት ለማሻሻል፣አነስተኛ የመስኖ ውሃ ተቋማት ለማጠናከርና ለማስተዳደር ፣ለወጣቶች የስራ-ዕድል ለመፍጠር፣የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ሌሎችም በርካታ ተግባራት ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ፕሮግራሙ በዋናነት የምግብና የስርዓተ ምግብ ጥንካሬው እንዲጨምርና በምግብ እራስን ለመቻል አላማ አድርጎ እንደሚሰራ አቶ ጌቱ አመላክተዋል።
ይህንን ስራ ውጤታማ ለማድረግ የተመጣጠነና ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ ለመፍጠር ሁሉም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የእኖር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብድልመጅድ ጀማል እንደተናገሩት የግብርናው ዘርፍ ከድህነት መውጫ ዋነኛ መንገድ ነው ያሉ ሲሆን ከኋላ ቀር የግብርና አሰራርና ከዝናብ ጠባቂነት በመላቀቅ በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ በማምረት በቤተሰብ፣በማህበረሰብና በሀገር አቀፍ ደረጃ ድህነትን ለማሸነፍ እየተካሄደ ያለው ጥረት ስኬታማ ለማድረግ የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅም አንስተዋል።
ለዚህም የተመጣጠነ ስርዓተ ምግብን በማጠናከር የእናቶችና ህፃናት ጤና መጠበቅ ይገባል ሲል ሀላፊው አጽንዖት ሰጥተዋል።
ወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ፋንቱ ደምስ በበኩላቸው ሴቶች በጓሮ የተመጣጠነ ሀይልና ሙቀት ሰጪ ምግቦችን በማምረትና በመመገብ የራሳቸውና የቤተሰቦቻቸውን ጤና ለመጠበቅ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ወ/ሮ ፋንቱ አክለውም የህብረተሰቡ ስርዓተ ምግብ አጠቃቀም በማሻሻል ጤናው የተጠበቀና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
እናቶች በጓሯቸው የሚያመርቷቸውን አትክልቶችና የእንስሳት ተዋፅኦ ውጤቶች ገበያ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ለራሳቸው መመገብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የጉራጌ ዞን የኤክስቴንሽን ኮምንኬሽን ስራ ሂደት አስተባባሪ እና የገጠር ሴቶች (nutrition) ባለሙያ ወ/ሮ ሲሳይ ኮራ በበኩላቸው ወረዳው ለግብርና ልማት ምቹና ተመራጭ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የስርዓተ ምግብ ችግር ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ሀገራዊ አጀንዳ በመሆኑ የህብረተሰቡ፣የአጥቢ እናቶችና ህፃናት የአመጋገብ ስርዓት ማሻሻል እንደሚገባ አብራርተዋል።
አስተባባሪዋ አያይዘውም በዚህም በአመጋገብ ስርዓት የሚከሰቱ ችግሮችን በማስወገድ ጤናማ የአመጋገብ ስርዓትን በማጎልበት ጤናው የተጠበቀ አምራች ትውልድ መገንባት ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ያሉን ፀጋዎች በአግባቡና በተቀናጀ አሰራር በተለይም በጓሮ በማልማት የስርዓተ ምግብ አጠቃቀም ለማሻሻል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *