ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም
================የእኖር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የትምህርት አስተዳደር መረጃን ወደ ዲጂታል ስርዓት በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና፣የ6 ወራት ተግባር አፈፃፀም ግምገማ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማካሄድ ጀምሯል።
የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ በሰዓቱ ብርጉ መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት የስልጠናው ዋና ዓላማ ከትምህርት ቤት እስከ ትምህርት ቢሮ ድረስ ያለውን የትምህርት መረጃ አሰባሰብ፣ አደረጃጀት፣ ትንተና እና አጠቃቀም ሂደትን ቀልጣፋና ዘመናዊ (ዲጂታላይዝ) ማድረግ መሆኑን አመላክተዋል።
ስልጠናው የጽ/ቤቱ የትምህርት አስተዳደር መረጃ ስርዓት ስራ ሂደት አስተባባሪ በአቶ ዚያድ ወንድሙ እየተሰጠ ይገኛል።
በመድረኩ ሱፐርቫይዘሮች፣ርዕሳነ-መምህራን፣እና የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።



