የካቲት 27/2017 ዓ.ም
===============
በወረዳው የማህበረሰቡን የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ ለበርካታ የካፒታል ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የእኖር ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ብርሀኑ ታቅነዳ እንደገለጹት በወረዳው በግማሽ አመቱ ከ50% በላይ የካፒታል በጀት ተግባር ላይ ማዋል መቻሉን ገልጸዋል።
በመሆኑም በወረዳው እየተሰሩ ባሉ በርካታ የልማት ሰራዎች ላይ እሴት ሊጨምሩና የአገልግሎት አሰጣጥ ሊያጎለብቱ የሚችሉ የካፒታል ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
እንደ ሀላፊው ገለጻ በመጀመሪያው ግማሽ የበጀት አመት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በግንባታና በግዢ ዘርፍ በርካታ የካፒታል ስራዎችን መሰራታቸው አመላክተዋል።
በመንግስትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ለትራንስፈርመር፣ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሞተር ሳይክል፣ከ 2.5 ሚሊዮን በላይ የተቋማት ፈርኒቸርና ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ለተቋማት ግንባታና እድሳት ወጪ መደረጉንም ገልጸዋል።
እንዲሁም ለመንገድ ግንባታ ከ2 ሚሊዮን በላይ፣የትምህርት ቤቶች እድሣትና ጥገናና ብሎግራንት እንዲሁም የመጽሀፍ ህትመት ከ2 ሚሊዮን፣የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞች ጽ/ቤት 1.5 ሚሊዮን እና የግብርና ጽ/ቤት የአጥር ግንባታ 1 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደረጓልም ነው ያሉት።
በተጨማሪ የማህበረሠብ ጤና መድህን 4.5 ሚለዮን እና የሆሥፒታል የእራጅ ማሽን(x-ray)እና የመድሐኒት አቅርቦት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ድጋፍ መደረጉንም አቶ ብርሀኑ አብራርተዋል።
በአጠቃላይ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና በጥራት በመጨረስ የህዝቡ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ቅድሚያ በመስጠት ለካፒታል ከተያዘው በጀት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በግማሽ አመቱ ከ50% በላይ ማሳካት መቻሉን ጠቁሟል።

