የካቲት 12/2018 ዓ.ም
================
በዛሬው ዕለት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገዶች ባለስልጠን ከ25 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው በእኖር ወረዳ ሻፋሞ ሴባደን መንደር በኩል ወደ ወርደነ አጣጥ ሆስፒታል የሚያሻግረው የዊንቀ ወንዝ ድልዲይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት እየተደረገ ይገኛል።
በክልል ገጠር መንገድ የተሰራውና 28 ሜትር የሚረዝመው የዊንቀ ወንዝ ድልድይ ከማህበራዊ ፋይዳው ባሻገር እኖርና ቸሃ ወረዳ በልማት ለማስተሳሰር የሚያስችል ፕሮጀክት እንደሆነም ተገልጿል።
በምረቃ ስነ- ስርአቱም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ፣የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገጠር መንገድ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ምስጋናው ማትዮስ፣
የክልሉ መንገድ ባለስልጣን የጉቡሬ ዲስትሪክት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ትዛዙ በርታ፣የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ ፣የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ፣የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሞሸዲን አህመድ፣የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ሐላፊዎች፣የወረዳው አስተባባሪ አመራሮችና የሴክተር ሐላፊዎችን ጨምሮ የአካባቢው ማህበረሰብና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።




