ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም
===============በእኖር ወረዳ የህብረት ስራ ማህበራት ሪፎርም በመደረጉ በዘርፉ ይስተዋል የነበረው የአሰራር፣የአደረጃጀትና የፋይናንስ ችግር መፍታት እንደተቻለ የወረዳው ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ገለጸ።
የጽ/ቤቱ ሐላፊ አቶ ልጅወርቅ ንጋቱ በበጀት አመቱ የመጀመሪያው አጋማሽ ተግባር አፈጻጸም አስመልክተው እንደተናገሩት ወረዳው በአሁኑ ወቅት ከማዳበሪያ ዕዳ ሙሉ በሙሉ ነጻ መደረጉን አመላክተዋል።
ከሪፎርም ንቅናቄ በሗላ በሸማች፣በቁጠባ፣በግብርና ነክና በንኡስ ተፋሰስ ስራ ላይ ለተደራጁ ማህበራት ሪፎርም በመደረጉ በዘርፉ ይስተዋል የነበረው የአሰራር፣የአደረጃጀትና የፋይናንስ ችግር መፍታት እንደተቻለም ሐላፊው ገልጸዋል።
ከአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት፣ስርጭትና ገንዘብ አስተዳደር ጋር ተያይዞ ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ መደረጉን የጠቀሱት አቶ ልጅወርቅ በ2015/16 ምርት ዘመን አካውንት ይነበብ የነበረና ኦሞ ተቋም በስህተት በ2014/15 ምርት ዘመን አካውንት ያስገባው 2ሚሊየን 2መቶ 30ሺ ብር ከ3አመት በሗላ ወደ ትክክለኛ አካውንት በማስገባት የወረዳው ዕዳ ሙሉ ለሙሉ ማሰረዝ እንደተቻለም አብራርተዋል።
በ2016/17 ምርት ዘመን ወለድ ጨምሮ የተሸጠ የአፈር ማዳበሪያ እዳ 46,812,978 ብር ሙሉ ለሙሉ መመለሱንም ሐላፊው አመላክተዋል።
በ2017/18 ምርት ዘመንም በቀረበውና በተሸጠው የአፈር ማዳበሪያ ብክነትና ሌብነትን ለመከላከል በ15 መጋዘኖች ላይ የቆጠራና የኦዲት ስራ በመስራት በኦዲት የተገኘ የ2 ኩ/ል ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ ገንዘብ ማስመለስ መቻሉንም ሐላፊው ጠቁመዋል።
የጽ/ቤቱ የማስፋፊያና ማደራጃ ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደጉ አብራር እንደገለጹት በመጀመሪያ ግማሽ ዓመት በወረዳው ውስጥ የሚገኙ 62 ማህበራት መልሶ በማጠናከር 1972 አዲስ አባላት ማፍራት ተችሏል።
በዚህ የማጠናከር ስራ 1ሚሊየን1መቶ 31ሺ ,2መቶ 60 ብር ካፒታል የማፍራት ተግባራ የተከናወነ መሆኑን የጠቆሙት አስተባባሪው 4 ሚሊየን ብር ብድር ለመስጠት ታቅዶ 4ሚሊየን 6 መቶ ሺ ብር መፈጸሙንም አመላክተዋል።
በግማሽ አመቱ በአጠቃላይ 7መቶ 45 ሺ ብር ለአባላት ትርፍ ክፍፍል የተደረገ ሲሆን ከነዚህም ከ75 ፐርሰንት በላይ የሚሆኑት ሴቶች ተጠቃሚ መሆናቸውንም አቶ ደጉ ተናግረዋል።
በወረዳው ጋሳውዴ ቀበሌ የተጠና ሮዝመሪ አምራች መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ ሳአዲያ ሀሰን በሰጠችው አስተያየት ማህበሩ ውጤታማ እንዲሆን የወረዳው ህ/ስራ ል/ጽ/ቤት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል ብላለች።
በመሆኑም ከተቋሙ በተደረገ የእዲት አገልግሎት መሠረት በበጀት አመቱ ከተገኘው 236ሺ ብር ትርፍ ላይ 70 ፐርሰንቱ ለአባላት ክፍፍል መደረጉና ቀሪው 30ፐርሰንት ለማህበሩ መጠባበቂያ ተቀማጭ መደረጉንም ገልጻለች።
አርሶ አደር ሙከረም በድሩ የአጋታ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን በወረዳው ህብረት ስራ ል/ጽ/ቤት አደራጅነት 55 አባላት ያሉት የአቨከሳ ንዑስ ተፋሰስ ህብረት ስራ ማህበር አባል መሆኑን ገልጿል።
የማህበሩ አባላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የወረዳው ህ/ስራ ልማት ጽ/ቤት ከካልም ፕሮግራም እና ከወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ጠቁሟል።
አባላቱ ከእርሻ ስራ ጎን ለጎን ንብ የማነብ ተግባር መጀመራቸውን የገለጸው አርሶ አደር ሙከረም 5መቶ 30ሺ ብር የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው እና የምርጥ ዘር፣የአፈር ማዳበሪያ በማግኘታቸው እንዲሁም አሲዳማ መሬታቸውን በኖራ ማከም በመቻላቸው ተጠቃሚነታቸው እየተሻሻለ መምጣቱንም ጠቁሟል።




