የእኖር ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ሁሉም የድርሻው ሊወጣ እንደሚገባ አስታወቀ።
ጽ/ቤቱ የትራፊክ አደጋ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰራ መሆኑንም ገለጸ።
የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ተመስገን ኑርጋ እንዳስታወቁት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራው በወረዳው የፌድራሉ የአስፓልት መንገድ ስራ እየተጠናቀቀ ከመሆኑ
ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ የትራፊክ አደጋዎች ለመቀነስ በእጅጉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
እንደ ሀላፊው ገለጻ በተለይም መንገድ ዳር ላይ ያሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ሲሄዱና ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የመንገዱ ግራ ጠርዝ ይዘው እንዲሂዱና ሲያቋርጡም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክረዋል።
አደጋው ለመቀነስም አስፓልት ዳር ላይ ያሉ ትምህርት ቤቶች የመግቢያ በራቸው ቀጣይ ከትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመሆን የመቀየር ስራ እንደሚሰራም ሀላፊው ጠቁመዋል።
ሌላው አሽከርካሪዎች በሰውና በንብረት ላይ አደጋ እንዳይፈጥሩና እራሳቸውና ቤተ ሰባቸው ካልተገባ እንግልት እንዲጠብቁም ፍጥነት ቀንሰው እንዲያሽከረክሩ አሳስበዋል።
የጽ/ቤቱ ምክትል ሀላፊ አቶ አስቻለው ጠንክር በበኩላቸው የተምህርት ቤት የትራፊክ ክበባት መምህራንና ተማሪዎች በማጠናከር የትራፊክ አደጋ እንዳይከሰ እየተሰራ ላለው ስራ የበኩላቸው እንዲወጡ ጠይቀዋል።
እግረኞች ላለምንም መዘናጋት የመንገዳቸው ግራ ጠርዝ ይዘው ሊጎዙ እንደሚገባ ምክትል ሀላፊው አመላክተዋል።
አቶ አስቻለው አክለውም መንገድ ላይ ከብቶች የሚነዱ ነጋዴዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።


