የእኖር ወረዳ ውሀ እና ማዕድን ጽ/ቤት ሀላፊ
አቶ ብሩክ ሀይሌ
መግቢያ
መንግስት የማህበረሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም በአሁኑ ተጨባጭ ሁኔታ ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽነት መሻሻል ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ በጀት በመመደቡና አጠቃላይ ባለድርሻ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ድርሻው ከፍ ማለቱ ይታወቃል፡፡እንዲሁም የወረዳው መንግስት ለዘርፉ የሚሰጠው ትኩረት በራስ አቅም የውሃ ፕሮጀክት ቀርፆ በዕቅድ ለመጨረስ በየዓመቱ የካፒታል በጀት በመመደብ የኩረት የተሰጠው መሆኑና የማህበረሰባችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ሽፋኑን ካለበት ዝቅተኛ ሽፋን ከፍ ለማድረግ ይሰራል ፡፡
የተቀናጀና ዘላቂ የውሃ ሀብት አጠቃቀም የሚያረጋግጥና የሀብት አስተዳደር ስርዓት በየተቋማቱ በመዘርጋት ቀበሌዎች የባለቤትነት ስሜት ተፈጥሮ ውጤታማ በማድረግ ላይ እያደረግን እንገኛለን፡፡
የፅ/ቤቱ አመሰራረት
-1999 ዓ ም በፊት ከግብርና ጽ/ቤት ስር ነበር
-1999 ዓ ም ጀምሮ እሰከ 2003 ዓም ድረስ በአስተዳደር ጽ/ቤት ስር ነበር
-2003 ዓ ም ጀምሮ በካቢኔ ደረጃ ውሃ ሀብት ፅ/ቤት ተብሎ እራሱ ችሎ ወጥቶዋል በወቅቱ የነበሩ ስራ ሂደቶች በውሃ ዘርፍ ፤በማዕድን ዘርፍ ፤ እና ኢነርጂ ዘርፍ በነዚ ዘርፎች ፅ/ቤቱ እየሰራ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ 2005 ጀምሮ የመስኖ ዘርፍ ስራ ሂደት ከግብርና ወደ ፅ/ቤታችን የመጣ ሲሆን በዚህም ዘርፍ ከአነስተኛ መካከለኛ እና ከፍተኛ የመስኖ ስራዎች ከፅ/ቤታችን ስር እየተሰሩ ይገኛሉ ፡፡
የወረዳው የውሃ አማራጮች
መረጃ በተመለከተ ፡- ምንጭ ከነ ማከፋፈያው ፤ የጥልቅ ውሃ ጉድጋድ ፤ መለስተኛ ጥልቅ ጉድጉድ፤ በቦታው የተገነቡ ምንጮች፤ የእጅ ጉድጉድ ፤የወንዝ ውሃ ፤የዝናብ ውሃ ፤የኩሬ ውሃዎች ናቸው ፡፡
የውሃ ማእከላት በተመለከተ ፡- የጉስ ባጃይ ጋርዳሼ ውሃ ተቋም ፤ የአጋታ ውሃ ተቋም፤ካናስ አዋስር ውሃ ተቋም፤እናገራ ውሃ ተቋም ፤ የሻንቃ ውሃ ተቋም ፤የወሸኧዘውያር የውሃ ተቋም፤ተርሆኝ የውሃ ተቋም፤ጠረደየውሃ ተቋም ፤ መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ (Shalwell) እና የእጅ ጉድጓድ ናቸው፡፡
የውሃ ሽፋን መረጃ በ2013 ዓ.ም 24.38%አሁን ያለበት 31%ነው፡፡
የውሃ ተቋማት ታሪክ፡-
የጋርዳሼ ውሃ ተቋሙ የሚገኝበት ቀበሌ ጋርዳሼ ተቋሙ የተቆፈረበት ቦታ ጉስባጃይ፤የውሀ ጉድጓድ ጥልቀት 214 ሜትር፤የፐምፑ መቀመጫ 138 ሜትር፤የኬዚነግ ስፋት 6፤የውሃ ታንከሩ አይነት ማሶኖሪ፤የውሃ ታንከሩ መጠን 100ሜትር ኪዩብ የውሃ ጉድጓድ ከታነከሩ ያላቸው ርቀት 350 ሜትር የፐምፑ ፓወር 30 ኪሎ ዋት የትራንስፎርመር ፓወር 100ኬ.ቪ፤የውሃው ዲስቻርጅ 6 ሊትር ፐር ሰከንድ ፤የጉድጓድ መነሻ ትቦ(pip) አይነት HDPE፤ጉድጓድ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት 2013 ዓ.ም ፤የሚያስጠቅመው ህዝብ ብዛት 8,000 3 ቀበሌ ቦኖ ብዛት 30 ጉድጓዱ የተቆፈረበት ዓመት 2009
–የአጋታ ውሃ ተቋሙ የሚገኝበት ቀበሌ አጋታ ተቋሙ የተቆፈረበት ቦታ መንደር አዶሼ፤የውሀ ጉድጓድ ጥልቀት 120 ሜትር፤የውሃው ዲስቻርጅ 5 ሊትር ፐር ሰከንድ ፤የኬዚነግ ስፋት 6፤የውሃ ታንከሩ አይነት ማሶኖሪ፤የውሃ ታንከሩ መጠን 50ሜትር ኪዩብ የውሃ ጉድጓድ ከታንከሩ ያላቸው ርቀት 200 ሜትር የፐምፑ ፓወር 18.5 ኪሎ ዋት የጄኔሬተር ፓወር 60ኬ.ቪ፤የጉድጓድ መነሻ ትቦ(pip) አይነት GI 3 ኢንች፤ጉድጓድ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት 2010ዓ.ም ፤የሚያስጠቅመው ህዝብ 3 ብዛት 8,000 ቀበሌ 18 ቦኖ ጉድጓዱ የተቆፈረበት ዓመት 2006
–የእናገራ ውሃ ፡- ተቋሙ የሚገኝበት ቀበሌ እናገራ ተቋሙ የተቆፈረበት ቦታ መንደር የደረባይ፤የውሀ ጉድጓድ ጥልቀት 158 ሜትር፤የውሃው ዲስቻርጅ 9 ሊትር ፐር ሰከንድ ፤የኬዚነግ ስፋት 6፤የውሃ ታንከሩ አይነት ማሶኖሪ፤የውሃ ታንከሩ መጠን 200ሜትር ኪዩብ የውሃ ጉድጓድ ከታንከሩ ያላቸው ርቀት 800 ሜትር የፐምፑ ፓወር 45 ኪሎ ዋት የጄኔሬተር ፓወር 150ኬ.ቪ፤የጉድጓድ መነሻ ትቦ(pip) አይነት GI 4 ኢንች፤ጉድጓድ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት 2010ዓ.ም ፤የሚያስጠቅመው ህዝብ ብዛት 9,000 3 ቀበሌ የሚያስጠቅም የቦኖ ብዛት 18 ጉድጓዱ የተቆፈረበት ዓመት 2009
የተርሆኝ ውሃ ፡- ተቋሙ የሚገኝበት ቀበሌ ተርሆኝ ተቋሙ የተቆፈረበት ቦታ ማረጓረባ፤የውሀ ጉድጓድ ጥልቀት 196 ሜትር፤የፐምፑ መቀመጫ 132 ሜትር፤የኬዚነግ ስፋት 4 ኢነች፤የውሃ ታንከሩ አይነት ማሶኖሪ፤የውሃ ታንከሩ መጠን 100ሜትር ኪዩብ የውሃ ጉድጓድ ከታነከሩ ያላቸው ርቀት 800 ሜትር የፐምፑ ፓወር 15 ኪሎ ዋት በሶላር የሚሰራ ሲሆን የሶላር ብዛት 108፤የውሃው ዲስቻርጅ 6 ሊትር ፐር ሰከንድ ፤የጉድጓድ መነሻ ትቦ(pip) አይነት HDPE፤ጉድጓድ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት 2015 ዓ.ም ፤የሚያስጠቅመው ህዝብ ብዛት 10,000 ቀበሌ ብዛት 3 የቦኖ ብዛት 13 እና ስከሌቶን 30 በድምሩ 43 ጉድጓዱ የተቆፈረበት ዓመት 2006
የጠረደ ውሃ፡- ተቋሙ የሚገኝበት ቀበሌ ካሳይ ተቋሙ የተቆፈረበት ቦታ ኧፋሞ፤የውሀ ጉድጓድ ጥልቀት 164 ሜትር፤የፐምፑ መቀመጫ 138 ሜትር፤የኬዚነግ ስፋት 6፤የውሃ ታንከሩ አይነት ማሶኖሪ፤የውሃ ታንከሩ መጠን 100ሜትር ኪዩብ የውሃ ጉድጓድ ከታነከሩ ያላቸው ርቀት 700 ሜትር የፐምፑ ፓወር 18.5 ኪሎ ዋት የትራነስፎርመር ፓወር 50ኬ.ቪ፤የውሃው ዲስቻርጅ 6.34 ሊትር ፐር ሰከንድ ፤የጉድጓድ መነሻ ትቦ(pip) አይነት HDPE 4 ኢንች፤ጉድጓድ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት 2013 ዓ.ም ፤የሚያስጠቅመው ህዝብ ብዛት 1 ቀበሌ ቦኖ ብዛት ቦኖ 6 ስክሌተን 20 የተጠቃሚ ህዝብ7500 ጉድጓዱ የተቆፈረበት ዓመት 2012ዓ.ም
የጃቱ ውሃ፡- ተቋሙ የሚገኝበት ቀበሌ ጃቱ ተቋሙ የተቆፈረበት ቦታ ጃቱ ጤና ጣቢያ ፤የኬዚነግ ስፋት 4 ኢንች፤የውሃ ታንከሩ አይነት ማሶኖሪ፤የውሃ ታንከሩ መጠን 50ሜትር ኪዩብ የውሃ ጉድጓድ ከታነከሩ ያላቸው ርቀት 350 ሜትር የፐምፑ ፓወር 30 ኪሎ ዋት የጄኔሬተር ፓወር 10ኬ.ቪ፤የውሃው ዲስቻርጅ 2.5 ሊትር ፐር ሰከንድ ፤የጉድጓድ መነሻ ትቦ(pip) አይነት Gi 2.5 ኢንች፡፡
–የካናስ ውሃ ተቋሙ የሚገኝበት ቀበሌ ካናስ ተቋሙ የተቆፈረበት ቦታ ጢቆ ወንዝ አካባቢ፤የውሀ ጉድጓድ ጥልቀት 178 ሜትር፤የውሃው ዲስቻርጅ 17 ሊትር ፐር ሰከንድ ፤የኬዚነግ ስፋት 6፤የውሃ ታንከሩ አይነት ማሶኖሪ፤የውሃ ታንከሩ መጠን 200ሜትር ኪዩብ የውሃ ጉድጓድ ከታንከሩ ያላቸው ርቀት 2500 የትራነስፎርመር ፓወር 200ኬ.ቪ፤የጉድጓድ መነሻ ትቦ(pip) አይነት 6 HDPE ኢንች፤ጉድጓድ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት 2016ዓ.ም ፤የሚያስጠቅመው ህዝብ ብዛት 9,500 3 ቀበሌ 20 ቦኖ ብዛት 9,500 ጉድጓዱ የተቆፈረበት ዓመት 2012 ዓ.ም
የወሸዘውያር ውሃ ፡- ተቋሙ የሚገኝበት ቀበሌ ወሸዘውያር ተቋሙ የተቆፈረበት ቦታ ወሸ፤የውሃ ታንከሩ አይነት ማሶኖሪ፤የውሃ ታንከሩ መጠን 50ሜትር ኪዩብ የውሃ ጉድጓድ ከታንከሩ ያላቸው ርቀት 250 ሜትር የፐምፑ ፓወር 15 ኪሎ ዋት በሶላር የሚሰራ ሲሆን የሶላር ብዛት 120፤የውሃው ዲስቻርጅ 3 ሊትር ፐር ሰከንድ ፤የጉድጓድ መነሻ ትቦ(pip) አይነት HDPE፤ጉድጓድ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት 2010 ዓ.ም ፤የሚያስጠቅመው ህዝብ ብዛት 8,500 ሲሆን የሚያስጠቅመው 3 ቀበሌ የቦኖ 4 ደረጃው የጠበቀ ስክሌቶን 20
የእኖር ወረዳ መለስተኛ ጥልቅጉድጓድ (Shalwell) መረጃ
ተ/ቁ | ቀበሌ | ብዛት | ምርመራ |
1. | ጋርዳሼ | 6 |
|
2. | አጋሬ | 4 | አንዱ የጥራት ችግር አለበት |
3. | ኧገበኝ | 2 | አንዱ የጥራት ችግር አለበት |
4. | ተርሆኝ | 4 |
|
5. | ጠረደ | 5 |
|
6. | ጓንታና | 6 |
|
7. | ኢባራኝ | 5 | አንዱ የጥራት ችግር አለበት |
8. | ወርቃት | 7 |
|
9. | ጎመሸ | 2 |
|
10. | ወሸዘውያር | 1 |
|
11. | ወንጬ | 1 |
|
12 | ጡማነ | 2 |
|
13. | ኧሰኸር | 4 | 2 የሚሰሩ 2 የማይሰሩ |
14. | ጃቱ | 6 |
|
15. | ገረንቦ | 3 |
|
16. | ጎነቸቤቴ | 6 |
|
17. | ሰንዲቃይ | 1 | የጥራት ችግር አለበት |
18. | ወሸአዋስር | 1 |
|
19. | ሆርበትዚዞ | 6 |
|
20. | ሻፋሞ | 6 |
|
21. | አጫወደ | 2 |
|
22. | ጎነደሬጨ | 7 |
|
- በእጅ ተቆ ፋሮ ፐምፕ የተገጠመለት ብዛት 1የሚገኝበት ቀበሌ አጫወደ
የጉድጓዱ ጥልቀት 21 ሜትር
የማዕድን መረጃ በተመለከተ
እንደ ፅ/ቤታችን ከሚሰሩ ተግባራት አንዱ ሲሆን የወረዳው አብዛኛው የማዕድን ምርት/ማለትም በነጭ ድንጋይ/ አለኝታ በመሰብሰብ እና ወጣቶች በዘርፉ በማህበር በማደራጀት በባህላዊ መልኩ የነጭ ድንጋይ ምርት በማምረት ለማህበረሰቡ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑ ከዚህም ከአምራች ማህበራት በደረሰኝ የሮያሊቲ ክፍያ እና የአመት ግብር ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑ ፡፡ነገር ግን ወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የማእድን ፖቴንሽያል መኖሩ በፅ/ቤታችን እና ከተለያዩ አጋር አካላት እና ድርጀቶች በተደረጉ ጥናቶች የተረጋገጡ ነው፡፡ እነዚህም ኦፓል ፤ የአንበር(ኮሰድ ቀበሌ)የሚገኙ ሲሆን፤ መና ደግሞ የግራናይት፤ የገረጋቲ ፤ የአሻዋ እና ሬድ አሽ ክምችት መኖሩ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎች በጥናት የተረጋገጠ ነው ፡፡
ከመስኖ ዘርፍ በተመለከተ፡-እንደ ተቋማችን የሚሰሩ አነስተኛና መካከለኛ እና ከፍተኛ የመስኖ ዘርፎች ናቸው እንደ ወረዳችን የሚገኘው የመስኖ ተቋም የወርቃት አነሰተኛ ና መካከለኛ የመስኖ ተቋም ሲሆን በዚህም በርካታ ስራ እየተሰራ መሆኑንን እሰከ 120 አስከ 150 ሄ/ር የሚያመርት መሆኑና ማህበረሰባችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡
ዋና ዋና ግቦች
- የንፁሁ መጠጥ ውሀ አቅርቦትን
- የአማራጭ ኤነርጂ የተሸሻሉ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ሽፋን ማሳደግ
- መካከለኛ መስኖ ዘርፍ አዲስ ጥናቶች በማድረግ ማደራጀት፡፡
- በማአድን ዘርፍ ስራ አጥ ወጣቶች በማደራጀት የስራ እድል መፍጠር
ራኢይ
ለወረዳው ማህበረሰብ የንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ማድረግ
ተልዕኮ
መ/ሰቡ የንፁህ ውሃ ተደራሽ በማድረግ ከተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች እራሱን እንዲከላከል ማደረግ፤
አላማ
ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት የወረዳው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ ችግር ፈቺ በማድረግ የህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው ፡፡
የተቋሙ ስልክ ቁጥሮች
የበላይ ኃላፊ 011 332 08 90
ልማት እቅድ 011 332 06 24
ሶሽዮ-ኢኮኖሚ 011 332 04 42
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834