እንደ ሀገር የገጠመውን የውጤት ስብራት ለመጠገን የመምህራን አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን የእኖር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የካቲት 13/2018 ዓ.ም
================
እንደ ሀገር የገጠመውን የውጤት ስብራት ለመጠገን የመምህራን አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን የእኖር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጽ/ቤቱ በመማር ማስተማር ሂደት እና በተከታታይ ምዘና አተገባበር ዙርያ ከ52ቱም ትምህርት ቤት ለተወጣጡ ሞዴል መምህራን፣ለሱፐርቫይዘሮችና ለርዕሳነ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ በሰዓቱ ብርጉ መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት እንደ ሀገር በትምህርት ልማት ዘርፍ የገጠመውን የውጤት ስብራት ለመጠገን የመምህራን አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
ስልጠናው የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ የመምህራን ልማት ባለሙያዎች በአቶ ባቂ ባሰማ፣በአቶ ደስታ በርጋ እና በወ/ሮ ሰናይት ደንቡ እየተሰጠ ይገኛል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *