የእኖር ወረዳ ፕላን ኮሚሽን ሀላፊ

     አቶ መሀመድ ሀሰን

አጠቃላይ ሁኔታ

         የእ/ወ/ፕ/ል/ ጽ/ቤት ባለፉት ዓመታት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሴክተር ውስጥ ሲቪል ሰርቪሱ ለመልካም አስተዳደር፣ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፤ ለልማት እና የለውጥ አጋዥ ኃይል ብሎም ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን በሁሉም የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መዋቅር በመተግበር ተቋማዊ ለውጥ እንዲያመጣና ሴክተሩ ዘመናዊ፤ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ እንዲፈጠርበርካታ ተግባራትንሲያከናውን ቆይቷል። እስካሁን ባለው የለውጥ ሂደት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን ማየት የተቻለ ቢሆንም  ቀደም ሲል በተበጣጠሰ መልኩ ሲከናወኑ የነበሩ ተግባራት በቀጣይ በተደራጀ እና ሁሉ አቀፍ በሆነ መልኩ መከወን እንዲችል ራሱን አስችሎ በክልል ደረጃ እንዲሁም በወረዳናበከተማ አስ/ደረጃ  በጽ/ቤት  መቋቋምእንዳለበትክልሉ በአዋጅ ደንግጓል።በዚህም መሠረት ወደ ተግባር ለመግባት እንዲያስችል የቀጣይ ሰባት ዓመታት ዕቅድ ማቀድ ቅድሚያ የምሰጠው ተግባር  ነው።

መግቢያ

ፕላን ኮሚሽን የክልሉን አሰፈፃሚ አከላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ በቁጥር 180/2012 የተቋቋመ መሆኑን ይታወቃል። የኮሚሽኑን መቋቋም ተከትሎ የሴክተሩ የቀጣይ አስር ዓመት ማለትም 2015—2022 ዕቅድ አቅዶ ወደ ተግባር መግባት እንዳለበት ይታመናል። በመሆኑም ይህ የፕላን ኮሚሽን የቀጣይ አስር ዓመት መሪ የዕቅድ ሰነድ አምስት ክፍሎች ሲኖሩት ክፍል አንድ አጠቃላይ ሁኔታዎችን እና የወረዳዉን አጠቃላይ ገጽታ የሚዳስስ ሲሆን ክፍል ሁለት 3 ዓመቱ ዋና ዋና ግቦችና የትኩረት መስክሲያካትት፤ክፍል ሶስት ግብና የአፈጻጸም ትንተናናበአፈጻጸም ወቅት ያገጠሙ ችግሮችና መፍትሄዎቹን ያካተተ ሲሆን አራተኛው ክፍል በአፈጻጸም ሰንጠረዥ (የየዓመቱ ዝርዝር አፈጻጸም) የተመላከተበት ሲሆን በመጨረሻም የቀጣይ ሰባት ዓመታት የትኩረት አቅጣጫ በሁሉም ዋናዋና የስራ ሂደቶች ከሚጣሉ ዋና ዋና ግቦች አሁን የደረስንበት አፈፃፀም መነሻ በማድረግ የቀጣይ ሰባት ዓመታት ዕቅድ ማቀድ ነው።

እኖር ወረዳ ፕላንና ልማ ጽ/ቤት

የእኖር ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ከ2012ዓ.ም ጀምሮ በአዋጅ የተሰጡትን ተልዕኮ በተሳካ ሁኔታ ለመፈፀም ዕቅድ አቅዶ ወደ ስራ የገባ ተቋም ነው፡፡ በእቅድ አፈፃፀም ወቅት ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ተቋቁሞ ለማለፍ ጠንካራና ተከታይ የሆነ ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል፡፡

ጽ/ቤቱ የተሰጡት ዋናዋና ኃላፊነት ተግባራት

  • የወረዳው የረጅምና የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል አፈፃፀማቸው ይከታተልል፣ይገመግማል
  • የወረዳውን መንግስት የካፒታል ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ያካሂዳል፣ይገመግማል፣ያፀድቃል
  • የወረዳውን የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፣ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀት አግባብነት ላላቸው አካላት ያቀርባል፡፡
  • የወረዳውን አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚና የማህበራዊ ሁኔታዎችን በማጥናት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ አቅታጫዎች የማመላከት ስራ ይሰራል፡፡
  • የካፒታል ፕሮጀክት ተግባራት አፈፃፀም ከ2013ዓ.ም -2016ዓ.ም

ዓ.ም

ሥልጠና

ለግንባታ

ለግዢ

ለአገልግሎት

ለማዘጋጃ ቤቶች

ድምር

2013ዓ.ም

4,224,560

7,942,000

5,052,650

1,170,000

233,093

18,622,303

2014ዓ.ም

5,826,500

12,999,210

6,991,700

1,550,000

710,232

28,077,642

2015ዓ.ም

8,721,530

8,270,000

5,200,000

2,450,000

1,542,281

26,183,811

2016ዓ.ም

9,860,000

12,830,000

12,900,000

8,881,087

1,261,887

45,672,970

ድምር

28,632,590

42,41,210

30,144,350

14,051,087

3,744,493

118,556,730

የተቋሙ ስልክ ቁጥሮች

 የበላይ ኃላፊ  011 332 08 90
ልማት እቅድ  011 332 06 24
ሶሽዮ-ኢኮኖሚ   011 332 04 42

ራዕይ

ፍትሀዊ የሀብት ድልድልና አጠቃቀም በማረጋገጥ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን በማስፈን የደረዳው ህዝብ ከድህነት ተላቆ ማየት፡፡

ተልዕኮ

በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መለስተኛ ጥናቶች በማካሄድና የፖሊሲ ማሻሻያ ሀሳቦችን ለማመንጨት፣ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ በማዘጋጀት፣የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የህዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በወረዳው ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡

እሴቶች

  • ቆጣቢነት
  • ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ
  • ፍትሀዊነት
  • ውጤታማነት
  • ግልፀኝነት
  • ተቆርቋሪነት
  • ቀልጣፋ አገልግሎት
  • በእቅድ መመራት