የእኖር ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት
አቶ አሰፋ በረከት
የእኖር ወረዳ ፍርድ ቤት
የቀድሞ የእነሞርና ኤነር ወረዳ ፍርድ ቤት የአሁን እኖር ወረዳ ፍርድ ቤት ታሪካዊ አመጣጡ እና ተግባርና ኃላፊነቱ በአጭሩ ሲዳሰስ፡፡
የቀድሞ የእነሞርና ኤነር ወረዳ ፍርድ ቤት የአሁን እኖር ወረዳ ፍርድ ቤት ሰይድ ኒቅባስ ሰይድ ቡደላ በተባሉ የእምነት አባት አካባቢውን እነንዲዳኙ ማህበረሰቡ እንደሾማቸው ይጠቀሳል፡፡ ከዚያም በኃላ አቶ ገብሬ አረጋዊ የተባሉ ዳኛ እየዳኙ እያለ አቶ በርጋ ደንድር በዳኝነት እና በሀላፊነት ሲያገለግሉ እንደቆዩ ያስረዳል፡፡ በወረዳው ካሉት ሶስት የመንግስት ስርዓት ውስጥ ህግ ተርጓሚ በመሆን የዳኝነት ስራውን በጉንችሬ ከተማ መቀመጫዉን መናሀሪ አካባቢ በማድረግ በአጋዝ ኮሬ ገብር በተባሉ በግለሰብ ቤት ዳኝነት እየሰጠ ከቆየ በኃላ ቤቱን ደርግ ወርሶት ወደ አይሰማ ቢሮ ከተሸጋገረ ከዛ በኃላ በደርግ ዘመነ መንግስት ከ1968 ዓም በፊት የተመሰረተና ከ72 ቀበሌዎች በላይ በመያዝ ማህበረሰቡን ሲያገለግል የቆየ ሲሆን ከ2010 ዓም በኃላ ወረዳው ለ3 ወረዳ በመካፈል በአሁን ሰዓት እኖር ወረዳ ፍርድ ቤት 43 ቀበሌ በመያዝ የእኖር ኤነር መገር ወረዳ ፍርድ ቤት እና ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት በመሆን የዳኝነቱን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የእኖር ወረዳ ፍ/ቤት በአንድ መደበኛ እና በ6 የተዘዋዋሪ ችሎት በማቋቋም ለህብረተሰባችን የዳኝነት አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን፡፡
የተቋሙ ስልክ ቁጥሮች
የበላይ ኃላፊ 011 332 0076
011 332 0487
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834