የእኖር ወረዳ አስተዳደር /ጽ/ቤት ሀላፊ

 አቶ ምትኩ ሀ/ማረያም

እኖር ወረዳ ከ 1983ዓ.ም ጀምሮ ያስተዳደሩት መሪዎች

አቶ መብራቱ ተክሌ እንግዳ (2015ዓ.ም - ዓ.ም)
አቶ ያዕቆብ ግርማ (መጋቢት 2012- ጥቅምት/2015 ዓ.ም)
አቶ የህያ ሱልጣን
አቶ ቴዎድሮስ አለሙ
አቶ ታደለ ግርማ
አቶ መኩ ደሊል
አቶ ባቂ በሰማ
አቶ ፍቃደ መርሻ
አቶ ከድር ያሲን (ከህዳር 1993 - የካቲት 1998)
አቶ መልስ ጸጋዬ
አቶ ታኖ ገብሬ (ከሃምሌ 1989 ዓ.ም -  ታህሳስ 1992 ዓ.ም)
አቶ ገ/ስላሴ በረዳ
አቶ ረሺድ መንግስቱ
አቶ ደምስ ማረጋ

             

መግቢያ

ኢንቨስትመንት በወረዳ ደረጃ

 

በወረዳችን ደረጃ በቁጥር 20 ኢንቨስትመቶች  ጸድቆላቸው 14ቱ ወደ ስራ ገቡ 2  ወደ ስራ ያልገቡ ሲሆኑ 4 በወረዳ ደረጃ ጸድቆ ወደ ክልል የተላኩ ያልተመለሱ ሲሆን እስካሁን ወደ ስራ የገቡ ኢንቨስትመንቶች የተረከቡት መሬት መጠን 8568 የለማ መሬት መጠን  5929፣ የተፈጠረ ስራ እድል በቋሚ ወ 104 ሴ 35 ድ 135 በጊዚያዊ ወ 418 ሴ 334 ድ 752 አጠቃላይ ወ 522 ሴ 369 ድ 891 ነው ፡፡

ወርቃት =1  ሻፋሞ =2  ተርሆኝ=1  ዳእምር=1  አንዳሆር=1  ካሳይ =1  ጎ/ሬጨ =2 ሰንዲቃይ =1 ኧገበኝ =1  አጫወደ =1  ጎምሸ =1  እኖር መና =7  

  1. በወረዳ ለኢንቨስትመንት የተዘጋጀ ምቹ ቦታ = እኖር መና

4 በወረዳ ኢንቨትትመንት ለሚደረግ የሚፈለጉ መስፈርቶች

  • ለህዝብና ለባለ ሃብቱ የሚጠቅም አዋጪ ቢዝነስ ፕላን ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  • ቀደም ሲል ያለዉ ታሪክና የስራ ልምድማወቅ ያስፈልጋል፡፡
  • በቂ ካፒታል ያለዉ መሆን አለበት ከመንግስት ብድር የማይጠብቅ ቢሆን ይመረጣል፡፡
  • የገቢ አቅም የሚያሳድግ፣ለአ/አደሩ የቴክኖሎጂ ሽግገግር የሚያደርግ፣ የመንግስት አቅጣጫ ተከትሎ ገበያ ማረጋጋት የሚችል እና የአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የሚላከኩ ሰብሎች ማምረት የሚችል ቢሆን ይመረጣል፡፡
  • ስራ አጥ ወጣት ስራ እድል መፍጠር የሚችል፡፡
  • በመሰረተ ልማት ስራዎች ዙሪያ ያሉ አ/አደር ማስተሳሰር የሚችል አቅም ያለዉ ኢንቨስትመንት ሲቀርብ በወረዳ ካቢኔ ይፀድቃል ቀጥሎ በዞን ካቢኒ ቀጥሎ በክልል ካቢኒ ፀድቆ ከመጣ በኃላ ወደ ስራ ይገባል፡፡

5 የመሰረተ ልማት ተደራሽነት አፈፃፀም

  • የዉሃ ሽፋን 30.64% የመብራት ሽፋን 27% የመንገድ 29%
  • ዋና ዓላማ (General Objective)

የሴክተሩን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችሉ ተግባራትን ስትራቴጂክ በሆነ መንገድ በመምራት በወረዳው ሁለንተናዊ እድገት በማምጣት እና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የወረዳውን ህዝብ ተጠቃሚነትና ብልፅግና ማረጋገጥ ነው፡፡

ራዕይ

  በወረዳው ሰላምና ፀጥታ ተረጋግጦ እና መልካም አስተዳደር ሰፍኖ ዘላቂ ልማት በማምጣት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፡፡

ተልዕኮ

በወረዳው ያሉትን ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ ሐብቶች አቀናጅቶ ቀጣይነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ እንዲዉሉ በመምራት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አጠናክሮ በማስቀጠል የወረዳውን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡

 

እሴቶች

  • የህግ የበላይነት መርሀችን ነው፡፡
  • ለተገልጋይ ፍላጎት ትልቅ ዋጋ እንሰጣለን፣
  • መቻቻል ባህላችን ነው፣
  • አሳታፊነት መለያችን ነው፡፡
  • ፍትሐዊነትና ሚዛናዊነት መመሪያችን ነው፡፡
  • ልዩነታችን ውበታችን፣ ውበታችን አንድነታችን ነው፡፡