የእኖር ወረዳ ን/ገ/ል/ ጽ/ቤት ሀላፊ
አቶ ነጃ አ/ባሲጥ
መግቢያ
ተቋሙ በአዋጅ ከተቋቋመበት 2010 ዓ.ም ጀምሮ በወረዳዉ ዉስጥ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ በማቀድ በሸማቹ ህ/ተሰብና በነጋዴዉ ማህ/ሰብ የተለያዩ የግንዛቤና የአመለካከት ስራዎችን በመስራት የንግዱ ዘርፍ ቀልጣፋ፣ዘመናዊ እና ፍትሃዊ የገበያ ስርዓት ለመዘርጋት ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛል፡፡ለዚህም የ10 ዓመት መሪ እቅድ አቅዶ ተፈፃሚነት እንዲያገኝ ሴክተሩ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በመቀናጀት ህገ-ወጥነትን በመከላከል የተለያዪ የግብርና ምርቶች ትስስር በመፍጠር የኑሮ ዉድነትን በመቀነስና ገበያን በማረጋጋት አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ከዚህም ባለፋ ለህ/ሰቡ ጤና ጎጂ የሆኑ የተለያዩ ጊዜ ያለፈባቸዉ ምርቶች ሰብስቦ በማስወገድ ከፍተኛ ስራ ይሰራል፡፡
በአሁኑ ወቅት የሴክተሩ የሰዉ ሃይል ወ10 ሴ 8 ድ 18 ሲሆን በ6 ዋና ዋና ስራ ሂደትና 4 ደጋፍ ስራ ሂደቶች ተደራጅቶ ይገኛል፡፡ የእቅድ የሪፓርት የግብረ-መልስ እንዲሁም የምዘና ስርዓት እና የድጋፍና ክትትል ሁኔታ በቼክ ሊስት አስደግፎ በአግባቡ የሚሰራ ሴክተር ነዉ፡፡
ስለ ንግድ ገበያ መረጃ
- የወረዳዉ የገበያ ማዕከላት ብዛት ሁለት ሲሆኑ አድራሻቸዉ፡-
- 1ኛዉ የኧገዜ የመጀመሪያ ደረጃ የቁም እንስሳት በረት/ማዕከል ፣2ተኛዉ የወርቃት የመንገድ ዳር ሼድ/የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከል
- ያሉ ሸማች ማህበራት ብዛት ሁለት ሲሆኑ አድራሻቸዉ ጉንችሬ ሆነዉ የነዋሪ ማህበረሰብና የመንግስ ሠራተኞች ሸማች ማ/ር ናቸዉ፡፡
- ገበያ ላይ የሚቀርቡ የምርት ዓይነቶች፡-
- የአገዳና የብርዕ ሰብሎች ፡- በቆሎ፣ጤፍ፣ስንዴ፣ገብስ፣አተርና ባቄላ
- አትክልትና ፍራፍሬዎች ፡- ቲማቲም፣ቀይ ሽንኩርት ፣ጥ/ጎመን ፣ ካሮት፣ቀይስር፣ ቃሪያና አበሻ ጎመንና አበባ ጎመን ሲሆኑ
- ከፍራፍሬ ፡- ማንጎ ፣አቨካዶ፣ሙዝ እና ፓፓያ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ( ሃብሃብ አልፎ አልፎ የቀረበ)
- ከስራስር ሰብሎች፡- ድንች፣ስኳር ድንች ፣ጎደሬና የእንሰት ዉጤቶች ናቸዉ፡፡
የሴክተሩ ዓላማ፣ ተልዕኮ፣ ራዕይ ና እሴቶች
ዓላማ
ፍትሃዊ የንግድ አሰራርና ዘመናዊ የግብይት ስርዓትን በመዘርጋትና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የንግዱ ማህበረሰብና ሸማቹን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እርካታ ደረጃቸውን ማሳደግ ነው፡፡
ራዕይ
በሀገሪቱ ተወዳዳሪና ህጋዊ የንግድና ግብይት ስርዓት በ2017 ዓ.ም ተፈጥሮ ማየት፡፡
ተልዕኮ
በወረዳዉ የነጻ ገበያ መርህ የተከተለ ንግድና ግብይት በማዘመን፣ በማስፋፋት፣ ህጋዊነትና ፍትሃዊነት በማስፈን የሸማቹን ህብረተሰብና የንግዱን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡
እሴቶች
- በዕቅድ እንመራለን፣
- ፍትሃዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነው፣
- በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን!
- ጊዜ እና የሰው ኃይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶቻችን ናቸው፣
- ኪራይ ሰብሳቢነትን እንፀየፋለን፣
- መረጃን ለልማት እናውላለን፣
- ውጤት ያሸልማል፣
- ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው!
- ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው!
ለህዝባችን ብልፅግና እንተጋለን፡፡
የተቋሙ ስልክ ቁጥር
0946848283
About Developer
mukeremsano@gmail.com
+251970847834