በወረዳው በካፒታል በጀት ሊሰሩ የታቀዱ ፕሮጀክቶችን ጥራትና በጊዜ በማከናወን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ፕላን ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።

በወረዳው በካፒታል በጀት ሊሰሩ የታቀዱ ፕሮጀክቶችን ጥራትና በጊዜ በማከናወን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ፕላን ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ መሀመድ ሀሰን እንደገለጹት በወረዳው በ2017 በጀት አመት 85 ሚልዮን 62 ሺ 3 መቶ 27 ብር በመበጀት ወደ ስራ መገባቱን አመላክተዋል።
እንደ ሀላፊው ገለጻ እስካሁን ባለው 30 ሚልዮን 74 ሺ 4 መቶ 40 ብር የእቅዱ 35.9% መፈጸሙን አብራርተዋል።
የዚሁ አካል የሆነው የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ግቢ 1ሚልዮን 60ሺ100ብር የፈጀው የግንብ አጥር በዛሬው እለት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ርክብክብ መደረጉን ገልጸዋል።
እንደ አቶ መሀመድ ገለጻ ወረዳው ባለው ውስን ሀብት የማህበረሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች በጥራትና በጊዜ እንዲጠናቀቁ መስራት ይገባል ብለዋል።
በርክብክብ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምትኩ ሀ/ማሪያም በበኩላቸው በወረዳው የማህበረሰብን ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ የካፒታል ፕሮጀክቶች በእቅዳቸው መሰረት እንዲሰሩ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።
አቶ መሀመድ በመጨረሻም ባለው ውስን ሀብት እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች በጊዜና በጥራት እንዲሰሩ በወረዳው ያሉ የኢንጅነሮች ቲም እያደረጉት ላለው ድጋፍና ክትትል አመስግነዋል ሲል የዘገበየወረዳው ። 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *