በወረዳው የመብራት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየሰራ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታወቀ።

በወረዳው የመብራት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየሰራ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታወቀ።
በወረዳው የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡
የእኖር ወረዳ አስተዳደር የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች አማካሪ አቶ አድርስ ተረዳ ወረዳው ካለው የቆዳ ስፋትና የህዝብ ቁጥር አንፃር በብዛት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተናግረዋል ።
ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የህብረተሰቡን የመብራት አገልግሎት ችግር ለመቅረፍ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ አማካሪው አብራርተዋል።
በወረዳው አንዳንድ ቀበሌዎች በከተማም በገጠርም ከሚገኙ ነዋሪዎች ሀብት በማሰባብ የመብራት ትራንስፎርመር ግዢ ተፈጽሟል ብለዋል።
አቶ አድርስ አክለውም ግዢ የተፈፀባቸው ትራንስፎርመሮችም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋጋር ወደ ቀበሌዎች መግባታቸውን ጠቁመው በቀጣይም የመስመር ዝርጋታ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ በገንዘቡም ሆነ በጉልበቱ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ችግሮችን ለመቅረፍ እያደረገው ላለው ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በወረዳው ሻንቃ ቀበሌ አግኝተን ካነጋገርናቸው ነዋሪዎች መካከል አቶ ኑርሰፋ ቡሴር አቶ ብላቱ ዩጂና አቶ ጦልሀ አብድል ሽኩር በሰጡት አስተያየት መንግስት የህብረተሰቡ የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያደረገው ያለው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስረድተዋል።
አሁን ላይ በቀበሌው ያለውን የመብራት ችግር ለመቅረፍ እንዲችሉ በከተማም በገጠርም ከሚገኘው ነዋሪ ገንዘብ በማዋጣትና የተለያዩ የገቢ ማግኛ ዘዴዎችን በመፍጥር የትራንስፎረመር ግዢ ተፈፅሟል ብለዋል።
የመስመር ዝርጋታውን ለማከናወንም በቀበሌው ባሉት ሁሉም መንደሮች ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል የፓል ግዢ ማከናወናቸው ተናግረው በቀጣይም ወደ ቀዬአቻው እንዲቀርብላቸውና የመስመር ዝርጋታ ስራው ባጠረ ጊዜ እንዲከናወንላቸው ከሚመለከታቸው ባለድረሻ አካላት በመቀናጀት አስፈላጊውን ተግባር እያከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።
የወረዳው መንግስት ለጀመሩት የመብራት መስመር ዝርጋታ ስራ መሳካት እያደረገላቸው ላለው ድጋፍ ነዋሪዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *