በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ከ102 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገጠር መንገዶች ባለስልጣንና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ የመንገድና ድልድይ ፕሮጀክቶች ምረቃ እየተከናወነ ነው።
የካቲት 19/2017 በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ ከ102 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገጠር መንገዶች ባለስልጣንና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ የመንገድና ድልድይ ፕሮጀክቶች ምረቃ ስነሥርዓት እየተከናወነ ይገኛል።
ከ102 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገጠር መንገዶች ባለስልጣንና በህብረተሰብ ተሳትፎ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ የተገነቡ የጢቁወ፣ የቁረጨ ናኳበ እና ጎጓረ ወንዝ ድልድዮች እና የአሞገራ አስጥር 21 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ ተጠናቆ ነው የምረቃ ስነስርዓት እየተካሄደ የሚገኘው።
የፕሮጀክቶቹ ጠቅላላ ወጪ 102 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ሲሆን የህብረተሰቡ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ በማቀላጠፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንደሚያስችልም ተመላክቷል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የወልቂጤ ክላስተር አስተባባሪና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ አቶ መዝረዲን ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የወረዳ የሰራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።




