ባለፉት ሰባት ወራት ከተለያዩ የገቢ ርዕሶች ከ112 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የእኖር ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ገለጸ። የጽ/ቤቱ ሐላፊ አቶ ተኸርቁ ይርጋ መንግስት ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በሚያከናውነው የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውስጥ ከግብር/ታክስ የሚሰበሰበው ገቢ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁሟል።

የካቲት 8/2017 ዓ.ም
============= ባለፉት ሰባት ወራት ከተለያዩ የገቢ ርዕሶች ከ112 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የእኖር ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ገለጸ።
የጽ/ቤቱ ሐላፊ አቶ ተኸርቁ ይርጋ መንግስት ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በሚያከናውነው የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ውስጥ ከግብር/ታክስ የሚሰበሰበው ገቢ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁሟል።
እንደ ሐላፊው ገለጻ በወረዳው ባለፉት ሰባት ወራት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ በአጠቃላይ128,413,731ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 112,856,760ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 87.89% መፈጸም ተችሏል።
አፈጻጸሙ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ47,894,103 ብር ብልጫ ማሳየቱንም አቶ ተኸርቁ አብራርቷል።
ገቢው የተሰበሰበው ከጫት ቀረጥ፣ከተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/፣ከተርን ኦቨር ታክስ ተመዝጋቢዎች፣ከቀጥታ ታክስ፣ከቀጥታ ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች፣ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች፣ከገጠር መሬት መጠቀሚያ ኪራይ ግብር እና ከእርሻ ስራ ገቢ ግብር ከመሳሰሉት የገቢ ርዕሶች እንደሆነም አስታውቋል።
የወረዳው ወጪ በራስ ገቢ ለመሸፈን ለተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ገቢው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑንም ሐላፊው አመላክቷል።
ወረዳው የሚያመነጨው ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ የመላው ህብረተሰብ ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ሐላፊው በተቋሙ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ያለው ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
ዘገባው የወረዳው መ/ኮ ነው።
May be an image of 5 people, people studying, hospital and text

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *