የካቲት 3/2017 ዓ.ም
================የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ይበልጥ ለማልማትና፣ለማስፋት እንደዚሁም የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ባለሙያዎችን ማብቃት እንደሚገባ የእኖር ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ጽ/ቤቱ በኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ፣በፈጠራ ስራዎች እና በዌብሳይት ዙርያ ለወረዳው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበብ ተጠሪ መምህራን እና ለሱፐርቫይዘሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዲንሰፋ ጀማል በስልጠናው ማስጀመርያ ላይ እንደገለፁት የመድረኩ ዋና አላማ ትምህርት ቤቶች ላይ ክበባት በማጠናከርና የተሻለ የፈጠራ ባለቤት በመፍጠር አለም የደረሰችበት ለመድረስና እና መምህራን የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ እንዲቀላቀሉ ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል።
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ይበልጥ ለማልማትና፣ለማስፋት እንደዚሁም የኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ባለሙያዎችን ማብቃት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ስልጠናው የጉራጌ ዞን የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምርያ የፈጠራ ስራ ሂደት አስተባባሪ በአቶ ታሪኩ ነዳ እንደዚሁም የጽ/ቤቱ የኔትወርክ አድሚኒስተርና ሶፍትዌር አስተባባሪ በወ/ሮ ሙሉ ሻፊ በኩል እየተሰጠ ይገኛል።
በመድረኩም የእኖር ወረዳ ም/ል አስተዳዳሪና የትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሽኩረታ አ/ከሪም፣የወረዳው ሳ/ኢ/ቴ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዲንሰፋ ጀማል፣የጉራጌ ዞን ሳ/ኢ/ቴ/መምሪያ የፈጠራ ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ታሪኩ ነዳን ጨምሮ፣የወረዳው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ከበብ ተጠሪ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።


