እኖር ወረዳ የራሷ የሆነ አለም አቀፍ የመረጃ ትስስር መተግበሪያ ዌቭ ሳይት በማበልጸግ በዛሬው እለት አስመርቃ ለአገልግሎት ክፍት አድርጋለች።

መስከረም 4/2017 ዓ/ም
******************** እኖር ወረዳ የራሷ የሆነ አለም አቀፍ የመረጃ ትስስር መተግበሪያ ዌቭ ሳይት በማበልጸግ በዛሬው እለት አስመርቃ ለአገልግሎት ክፍት አድርጋለች።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ መተግበሪያውን በማስተዋወቅ አገልግሎቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት ወረዳው የራሱ የሆነ ዌቭ ሳይት መተግበሪያ ማበልጸጉ ለሰላም ፣ለእድገት፣ለባህልና ቱሪዝም ልማት ስራዎች ከፍታ ወሳኝ እርምጃ ላይ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።
ዌቭ ሳይት አንዱ የማህበራዊ ሚዲያ አካል እንደመሆኑ መጠን በተጠያቂነት መንፈስ ለበጎ ተግባር ማዋል የሚገባና ወቅቱን የሚመጥን ዘመናዊ የመረጃ መለዋወጫ የብልጽግና ትሩፋት እንደሆነም ገልጿል።
ከወረቀት ንኪኪ ነጻ የሆነ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በመሆኑ ሰራተኛው ከወቅቱ ጋራ ለመራመድ ከቴክኖሎጂ ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንዳለበትም አመላክቷል።
የወረዳው መንግስት የልማትና የመ/አስተዳዳር ስራዎች፣ባህላዊ ዕሴቶች እንዲሁም ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መስህቦች በአለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ በመረጃ የበለጸገና ተጠቃሚ የሆነ ህብረተሰብ ለመፍጠር ፋይዳው የጎላ እንደሆነም አብራርቷል።
አቶ መብራቴ ተግባሩ እንዲሳካ ለተባበሩ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም መተግበሪውን ላበለጸጉ ለወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋም ባለሙያዎች በተለይም ለወ/ሮ ሙሉ ሻፊና ለአቶ ሙከረም ሳኖ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
የወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሐላፊ አቶ ዲንሰፋ ጀማል በበኩላቸው መረጃ የእድገት መሠረት በመሆኑ በዘመነ ግሎባላይዜሽን አለም በመረጃ ተሳስሮ ወደ አንድ መንደር መጠጋቱን ገልጿል።
በመሆኑም የወረዳው ሴክተር መስሪያ ቤቶቸ ለዌቭ ሳይቱ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን በመመገብ የወረዳው በጎ ገጽታ ከመገንባት ጎን ለጎን በዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሐላፊው አስረድቷል።
ለጥናትና ምርምር ስራዎች፣ለኢንቨስትመንት ልማት በአጠቃላይ ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የሚያስችል የመረጃ ማስቀመጫ ቋት መሆኑንም አቶ ዲንሰፋ አመላክቷል።
ዌቭ ሳይታችን በመረጃው ዘርፍ እኖርን አንድ ደረጃ ከፍ አድርጎ ከአለም ጋር እንዲቀላቀል አስችሏል ብለዋል።
በየትኛውም የአለም ክፍል ስለ እኖር መረጃ ለሚፈልግ አካልም ሆነ ድርጅት WWW.enoreguraghe.gov.et ላይ በመግባት የተሟላ መረጃ ማግኘት እንደሚችልም ሐላፊው ጠቁሟል።
ይህንን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ላደረጉ ለጽ/ቤቱ ባለሙያዎችና ባለድርሻ ተቋማት የላቀ ምስጋናም አቅርበዋል።
የጽ/ቤቱ ባለሙያ ወ/ሮ ሙሉ ሻፊ መተግበሪያውን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ለአጠቃቀም ቀላል የውስጥ አቅም በመጠቀም መረጃዎችን ለማዘመን የሚያስችል ዳይናሚክ መሆኑን አስረድቷል።
አንዳንድ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ወረዳው ለመጀመሪያ ጊዜ በተቋም ባለሙያዎች አማካኝነት ዌቭ ሳይት ማበልጸግ በመቻሉ መደሰታቸውን ጠቁመው ከቴክኖሎጂው ጋር ተቀራርቦ በመስራት ትክክለኛ መረጃ በመመገብ አገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማዘመን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የወረዳው አመራሮች፣የሴክተር መስሪያ ቤቶች ማኔጅመንት አባላትና የዞን ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በመጨረሻም የዌቭ ሳይት መተግበሪያውን ያበለጸጉ ለጽ/ቤቱ ባለሙያዎችና ለተባበሩ ባለድርሻ ተቋማት የዕውቅና /የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *