የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ የ2017ዓ.ም የመስቀል በዓል አስመልክቶ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

መስከረም 14/2017ዓ.ም
===============
የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ የ2017ዓ.ም የመስቀል በዓል አስመልክቶ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው፥ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
አቶ መብራቴ አክለው እንዳሉት ህዝበ ክርስቲያኑ የመስቀልን በዓል ሲያከብር በየአካባቢው የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፣የታመሙትን በመጠየቅና መሰል የዕምነቱ መልካም ተግባራትን በመፈፀም ሊሆን ይገባል።
የመስቀል በዓል በማህበረሰቡ ዘንድ ለዘመናት የአብሮነት፣የመረዳዳትና የመተሳሰብ መገለጫ ነው ያሉት አስተዳዳሪው ምዕመኑም ይህንን ለዘመናት የቆየው የበዓሉ መልካም እሴቶች ሊጠብቅና ሊያጎለብት ይገባል ብለዋል።
በመስቀል በተለያዩ ምክንያቶች ከትውልድ ቀያቸው ርቀው ይኖሩ የነበሩ ተወላጆች በመሰባሰብ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በደስታ የሚገናኙበት እንደሆነ ያስታወሱት አስተዳዳሪው ተወላጆች ከበዓሉ ጎን ለጎን በአካባቢያቸው ልማት ላይ እንዲመክሩም ጥሪ አቅርቧል።
በዓሉ ከምንም በላይ የሰላም ፣ የአንድነትና የአብሮነት እንዲሆንም ዋና አስተዳዳሪው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።ወሄ ሙርኣ ኧህርመልካም የመስቀል በዓልየእኖር ወረዳ አስተዳደር!!መስከረም 2017ዓ.ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *